( 13 Votes ) 

የሥነምግባር መከታተያ ክፍል

አድራሻ

የሥነምግባር መኮንን፡ አቶ ሃረጎት አብርሃ
ስልክ፡ +251115516592
ፋክስ፡+251115527767
ፖስታ ሣ.ቁ፡34798/99
ኢ.ሜይል፡ ይህ የኢሜይል አድራሻ ከ spambots እየተጠበቀ ነው፡፡ ለመማየት JavaScript enabled መሆን አለበት

 

  የሥነምግባር መከታተያ ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራት

የኮሚሽኑ ሰራተኞች በስነምግባራቸው የተመሰገኑ እና የታነፁ እንዲሆኑ በመልካም ስነምግባር ፤በሙስና አስከፊነት፣ በፀረ-ሙስና ፖሊሲዎች እና በተለያዩ የፀረ-ሙስና  ህጎች  ዙሪያ ግንዛቤያቸው እንዲዳብር ማስተማር፤ 

የኮሚሽኑ አዋጆች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎች፣ አሰራሮች እና ሌሎች የኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ህጎች መከበራቸውን ዘወትር ክትትል ማድረግ፣ ስለአፈፃፀማቸው በየጊዜው የኮሚሽኑን የበላይ ሃላፊ ማማከር፤

አግባብነት ካላቸው የኮሚሽኑ የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር የኮሚሽኑን ሰራተኞችና የስራ መሪዎች የስነምግባር መመሪያ ማዘጋጀት፣ ማስፀደቅ ፣ማሻሻል ፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤

የኮሚሽኑን የሙስና መከላከል ዳሬክቶሬት በማማከር በኮሚሽኑ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ማጥናት ፣ የተጠናውን የመፍትሔ ሃሳብ ለኮሚሽነሩ ማቅረብ ፣ ሲወሰንም ተግባራዊነቱን  መከታተል፤

በራሱ ጥርጣሬ ወይም ከሌላ ወገን የቀረበለትን የስነምግባር ጥሰት ጥቆማ በመመዝገብ ለኮሚሽኑ የበላይ ሃላፊ ማሳወቅና ጉዳዩ የደረሰበትን ሁኔታ መከታተል፤

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከውጭ ተገልጋዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በማጣራት  እንዲፈቱ ክትትል ማደረግ ናቸው፡፡


945106
ዛሬዛሬ86
በዚህ ሳምንትበዚህ ሳምንት208
በዚህ ወርበዚህ ወር1648
በጠቅላላ ቀናትበጠቅላላ ቀናት945106
Powered by AFRICOM Technologies PLC