( 9 Votes ) 

የሀብት ማሳወቂያ እና ምዝገባ  ዳይሬክቶሬት

አድራሻ

 

ዳይሬክተር: አቶ ግርማ ወርቁ
ስልክ:  +251115-52-91-00

        +251 011 553 6905

ፋክስ: +251 011 515 1432

ኢ-ሜይል: ይህ የኢሜይል አድራሻ ከ spambots እየተጠበቀ ነው፡፡ ለመማየት JavaScript enabled መሆን አለበት
 

 

የዳይሬክቶሬቱ ተልዕኮ፡-


አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የተመራጮችን፣ የተሿሚዎችንና የመንግሥት ሠራተኞችን ሀብት በመመዝገብ፣ በማረጋገጥ፣ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና የጥቅም ግጭትን በማስተዳደር የግልፅነትናተጠያቂነትን አሰራር መዘርጋት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ሙስናን መከላከል፡፡

የሀብት ማሳወቅና ምዝገባን በተመለከተ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት፡
• የተሿሚዎችን፣ የተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞችን እና የቤተሰባቸውን ሀብት እና የገቢ ምንጭ ይመዘግባል፣
• አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የተሿሚዎችን፣ የተመራጮችን ወይም የመንግስት ሠራተኛውን ሀብት እንዲመዘግብ እንደሁኔታው በሙሉ ወይም በከፊል የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍልን ሊወክል ይችላል፣
• የሀብት ምዝገባ ሰነዶች ጠባቂ ሆኖ ያገለግላል፣
• የሀብት ምዝገባ ቅጾችና የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያዘጋጃል፣
• ሀብታቸውን ላስመዘገቡ ተሿሚዎች፣ ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች የምዝገባ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
• የምዝገባ ጊዜ እንዲራዘምለት ለሚጠይቅ ሰው የቀረበለት ጥያቄ በበቂ ምክንያት የተደገፈ ሆኖ ሲያገኘው የምዝገባውን ጊዜ ለአንድ ጊዜ እስከ 3ዐ ቀናት ሊያረዝም ይችላል፣
• በተሿሚ፣ በተመራጭ ወይም በመንግስት ሠራተኛ በተሞላ መረጃ ያልተሟላ፣ ትክክል ያልሆነ ወይም የሀሰት መረጃ ያየዘ መሆኑን ለመጠርጠር በቂ ምክንያት ሲኖረው ወይም ሀብቱ በትክክል አልተመዘገበም የሚል ጥቆማ ሲቀርብ ወይም በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት ምርመራ ሲጀመር የምዝገባውን ትክክለኛነት የማጣራት ተግባር ያከናውናል፣
• ያልተሟላ፣ ትክክል ያልሆነ ወይም የሀሰት መረጃ መቅረቡን በማስረጃ ሲያረጋግጥ ጥፋት በፈጸመው ሰው ላይ በህጉ መሠረት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድበት ያደርጋል፣
• በኮሚሽኑ እጅ የሚገኝን የተሿሚ፣ የተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፣
• በየሁለት ዓመቱ ስላከናወነው የሀብት ምዝገባ አጠቃላይ መረጃ በሪፖርት መልክ ያወጣል፣
• ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ በመንግስት የሥራ ኃላፊነቱ እና በራሱ ወይም በቅርብ ዘመዱ የግል ጥቅም መካከል ግጭት ሊያስከትል የሚችል ጉዳይ ማጋጠሙን ሲገልጽ የጥቅም ግጭትን ለማስወገድ እርምጃ ይወስዳል፣
• በቀረበ ጥቆማ መሰረት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ እንዲወረስ (የወንጀል ህግ 419(2)) በፍ/ቤት ሲወሰን ለጠቋሚው የተወረሰው ሀብት 25% እንዲከፈል ያደርጋል፣
• አዋጁን ለማስፈጸም የሚያግዙ ደንቦች እንዲወጡ ያደርጋል፤ የሰደቁትን ሥራ ላይ ያውላል፣
• አዋጁንና ደንቦችን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን አውጥቶ ሥራ ላይ ያውላል፡፡


ሥልጣንና ተግባር፡-


ሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 668/2002 ለኮሚሽኑ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለማከናወን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት በ2003 ዓ.ም በኮሚሽኑ ሥር በዳይሬክቶሬት እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡


የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባራትም የሚከተሉት ናቸው፡-

• ስለሃብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ ህግ ጠቀሜታ፣ ዓላማ እና አፈጻጸም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ለምዝገባ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
• የተሿሚዎችን፣ የተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞችን እና የቤተሰባቸውን ሀብት እና የገቢ ምንጭ ምዝገባ ማከናወን፣
• የጥቅም ግጭትን መከላከል፣
• የሀብት ምዝገባ መረጃን ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ፣
• የምዝገባ ሥራ ውክልና በተሰጣቸው አካላት/የሥነ-ምግባር መኮንኖች/ ሲሠራ ድጋፍና እገዛ መስጠት፣
• የምዝገባን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣
• በሀብት ማሳወቅና ምዝገባው ረገድ ያለውን ልምድና ተሞክሮ ለክልል ፀረ-ሙስና ተቋማት ማካፈልና ከሌሎች አገሮች ተመሳሳይ ተቋማት ደግሞ ልምዶችን መቅሰም ናቸው፡፡

የዳይሬክቶሬቱ አደረጃጀት፡

ከላይ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ለማከናወን ዳይሬክቶሬቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አራት ቡድኖች እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

1. የተመራጮች ሃብት ማሳወቅ ምዝገባ፣ የምዝገባ ትክክለኛነት ማረጋገጥና የምዝገባ መረጃ ተደራሽነት ቡድን፣
2. የተሿሚዎች ሃብት ማሳወቅ ምዝገባ፣ የምዝገባ ትክክለኛነት ማረጋገጥና የምዝገባ መረጃ ተደራሽነት ቡድን፣
3. የመንግሥት ሠራተኞች ሃብት ማሳወቅ ምዝገባ፣ የምዝገባ ትክክለኛነት ማረጋገጥና የምዝገባ መረጃ ተደራሽነት ቡድን፣
4. የጥቅም ግጭት መከላከል ድጋፍና እገዛ ሰጪ ቡድን ናቸው፡፡

የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት 19 ሠራተኞች አሉት፡፡

945109
ዛሬዛሬ89
በዚህ ሳምንትበዚህ ሳምንት211
በዚህ ወርበዚህ ወር1651
በጠቅላላ ቀናትበጠቅላላ ቀናት945109
Powered by AFRICOM Technologies PLC