( 6 Votes ) 

የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት

አድራሻ

 

ዳይሬክተር: አቶ አክሊሉ ሙሉጌታ
ስልክ: +251 011-552-77-87
ፋክስ: +251 011-553 69 09
ኢሜይል: ይህ የኢሜይል አድራሻ ከ spambots እየተጠበቀ ነው፡፡ ለመማየት JavaScript enabled መሆን አለበት

 

ተልዕኮ፡-

አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ጥናት በማካሄድ፣ የምክር አልግሎት በመስጠት እንዲሁም
ለተግባራዊነቱ ድጋፍና እገዛ በማድረግ በመንግሥትና በህዝባዊ ድርጅቶች አሠራር  ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ

ዋና ዋና ተግባራት፡-

ዳይሬክቶሬቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሙስናና ብልሹ አሰራርን አስቀድሞ በመከላከል ተግባር ላይ የተሰማራ ነው፡፡ ይህን ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ

መንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ መንግሥት የልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ድርጅቶች የአሰራር ስርዓቶች በማጥናትና በመፈተሽ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮች የሚወገዱበትን መንገድ ማመላከት እንዲሁም አሰራሮቹ እንዲሻሻሉ እገዛና ክትትል ማድረግ ዋና ዋና ተግባሮቹ ናቸው፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በሙስና መከላከል ዙሪያ የምክር አገልግሎትም ይሰጣል፡፡ በአንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶችና የህዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ለሙስና በተጋለጠና ግልፅነት በጎደለው ሁኔታ ስራዎች (ለምሳሌ በጨረታ አካሄድና አፈፃፀም ላይ) እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ጥቆማ ከደረሰው ፈጣን ክትትሎችን በማድረግ ሙስናን የመከላከል ተግባር ያከናውናል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ አዳዲስ ህጎች ሲወጡ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ዝግ መሆናቸውን የማረጋገጥ፣ በዚህም ዙሪያ ምክር የመለገስ ተግባር ያከናውናል፡፡ የተለያዩ አካላት የስነምግባር ደንብ ሲያዘጋጁ ምክር መስጠትም ሌላው ተግባሩ ነው፡፡ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት ከሚያገኙ ድርጅቶች መካከል የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የክልል የፀረ-ሙስና ተቋማት፣ የስነምግባር መኮንኖች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ይገኙበታል፡፡


በስራ ሂደቱ ሥር የሚገኙ ቡድኖች ብዛት 6
አሁን ያለው የሰው ኃይል ብዛት 30

945105
ዛሬዛሬ85
በዚህ ሳምንትበዚህ ሳምንት207
በዚህ ወርበዚህ ወር1647
በጠቅላላ ቀናትበጠቅላላ ቀናት945105
Powered by AFRICOM Technologies PLC