( 3 Votes ) 

የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

አድራሻ

 

ዳይሬክተር: አቶ መኮንን ዘሪሁን

ስልክ: +251115-15-15-06
ፋክስ: +251 011-515—14-92
ኢሜይል: ይህ የኢሜይል አድራሻ ከ spambots እየተጠበቀ ነው፡፡ ለመማየት JavaScript enabled መሆን አለበት

 

1. ተልእኮ

አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የሥነምግባር-ዓውታሮችን የማስተባበር፣ ለዚህ ዓላማ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የፀረ-ሙስና አደረጃጀቶች እንዲቋቋሙ ማድረግ፣  የፊትለፊት የስነምግባር ትምህርትን እና ስልጠናዎችን በህብረተሰብ ውስጥ ማሰራጨት

2. ዋና ዋና ተግባራት

  • በሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዙሪያ የሚቀርቡ የምክር አገልግሎት ጥያቄዎችን መቀበል እና ግብረ መልስ መስጠት፣
  • የሥነምግባር አውታሮች የሚያቀርቧቸውን ችግሮች መፍታት ወይም እንዲፈቱ የሚመለከታቸውን አካላት ማሳወቅ፣
  • የሥነምግባር አውታሮች ዓመታዊ ዕቅዶችና የየሩብ አመት ሪፖርቶች እንዲልኩ ማድረግና በተላከው ዕቅድና ሪፖርት ግብረ መልስ መስጠት፣
  • የሥነምግባር አውታሮች ሙስናን የመታገልና መልካም ሥነምግባርን የማስፋፋት አቅማቸው እንዲያድግ የተለያዩ የፊትለፊት የግንዛቤ ማስጨበጫ ት/ቶችን እና የክህሎት ስልጠናዎችን ማዘጋጀት እና መስጠት፣

  • የሥነምግባር አውታሮች ልምድ የሚለዋወጡበትን መድረክ ማዘጋጀት፣
  • የፊትለፊት የስነምግባር ትምህርትን እና ስልጠናዎችን በህብረተሰብ ውስጥ ማሰራጨት
  • የሥነምግባር አውታሮች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የፋይናንስ፣ የባለሙያ እና የማቴሪያል ድጋፍ መስጠት፣
  • የሥነምግባር አውታሮችን በአካል በመጎብኘት እንቅስቃሲያቸውን መገምገም ይገኙበታል፡፡

ይህ ዳይሬክቶሬት የተቋቋመው ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በፀረ-ሙስና ትግሉ ዙሪያ የሚያደርገውን ትብብር እንዲመራና እንዲያስተባብር ነው፡፡ በዚህም መሰረት ዳይሬክቶሬቱ በእስካሁን እንቅስቃሴው ኮሚሽኑ ከሚዲያ ተቋማትና ማህበራት፣ ከሐይማኖት ድርጅቶች፣ ብዙሐን ማህበራት፣ ንግድና ዘርፍ ማህበራት፣ በህግ ልዕልና ዙሪያ ከሚሰሩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች፣ ሙስናን መዋጋትን እንደ አንድ አላማቸው አድርገው ከያዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የሙያ ማህበራት ጋር የጋራ መድረክ እንዲመሰርት አስፈላጊውን ሁሉ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያቀፈ አንድ አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ይመሰረት ዘንድ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል፡፡

 

945105
ዛሬዛሬ85
በዚህ ሳምንትበዚህ ሳምንት207
በዚህ ወርበዚህ ወር1647
በጠቅላላ ቀናትበጠቅላላ ቀናት945105
Powered by AFRICOM Technologies PLC