( 3 Votes ) 

ዕቅድ ፣ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት

አድራሻ

 

ዳይሬክተርወ/ሮ ፍሬሕይወት ተረፈ

 

ስልክ: +251115-52-91-00

       +251115-52-77-83

ፋክስ: +25111-555—69-02

ፖ.ሳ.ቁ.: 34798/34799
ኢሜይል: ይህ የኢሜይል አድራሻ ከ spambots እየተጠበቀ ነው፡፡ ለመማየት JavaScript enabled መሆን አለበት

 

 

 ተልዕኮ፣

የተቀናጀ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የዕቅድ ½ ግዝና ፋይናንስ  አገልግሎት በመስጠት እና የንብረት አያያዝ እና አጠቃቀም በአግባቡ እንዲሆኑ በማድረግ የኮሚሽኑ አላማና ተልዕኮ እንዲሳካ ድጋፍ ማድረግ፡፡

የእቅድ፣ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የኮሚሽኑን የፋይናንስና የበጀት ጉዳዮች የማቀድ፣ የማደራጀት፣ የማቀናጀትና የመምራት ኃላፊነት የተጣለበት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ እንዲሁም የእቅዶችን አፈፃፀም የመከታተልና የመገምገም፣ የልዩ ፕሮጀክቶችን መፃኢ አቀራረፅና አፈፃፀም ካለፈው አፈፃፀማቸው በመነሳት የመንደፍ ኃላፊነቶችም አሉበት፡፡ የግዥ አፈፃፀምና የንብረት አስተዳደር ስራዎችም የዚሁ ዳይሬክቶሬት ተግባራት ናቸው፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በተጨማሪም ፕሮጀክቶችን ያዘጋጃል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል እንዲሁም የአፈፃፀም ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፡፡ የግዥ እቅዶችን የመንደፍ፣ የአቅርቦቶችን መኖር የማረጋጥ እንዲሁም አጠቃቀማቸውን የመቆጣጠርና የማስተዳደር ተግባራትንም ያከናውናል፡፡ የንብረት አጠቃቀምንና አያያዝን፣ የፕሮጀት አፈፃፀምንና እቅድ አወጣጥን በተመለከተ ለሌሎች የስራ ሂደቶችና ክፍሎች ዳይሬክቶሬቶች ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በየስራ ክፍሎቹ አግባብ ያለው የሂሳብ አያያዝ ስለመኖሩ እንዲሁም በተገቢው ወቅት ኦዲት ስለመደረጉ ክትትል ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የኮሚሽኑን የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጅካዊ እቅድና የእቅዱን የድርጊት መርሐ ግብር እያዘጋጀ በኮሚሽኑ የበላይ የስራ ኃላፊዎች ካስፀደቀ በኋላ እንዲተገበር ያደርጋል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ ለኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊዎችና የተለያዩ የስራ ሒደቶችና ክፍሎች በበጀትና ፋይናንስ አጠቃቀም፣ እቅድ አዘገጃጀትና አፈፃፀም፣ ንብረት አስተዳደር፣ ግዥ፣ እንዲሁም ፕሮጀክት አዘገጃጀት፣ አፈፃፀምና ግምገማ ዙሪያ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በሙሉ አቅሙ ሲንቀሳቀስ 16 ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡

የስራ ሂደቱ ሶስት ቡድኖች ያሉት ሲሆን እነሱም፡-
• የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ቡድን
• የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
• የፋይናንስ ቡድን ናቸው

945106
ዛሬዛሬ86
በዚህ ሳምንትበዚህ ሳምንት208
በዚህ ወርበዚህ ወር1648
በጠቅላላ ቀናትበጠቅላላ ቀናት945106
Powered by AFRICOM Technologies PLC