ከጥቅምት 16-17 ቀን 2013 . በአርባ ምንጭ ከተማ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት አባላቱ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እራሱን በአደረጃጀትና በአሰራር በማጠናከር የጀመረውን እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ እንዲሻሻል ለምክር ቤቱ የቀረበው ጥያቄ መዘግየቱን የጠቀሱት የምክር ቤቱ አባላት ለአዋጁ መሻሻል እንደ ሰብዓዊ መብትና የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋማት ሁሉ ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥም ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል፡፡No comments yet. Be the first.