|
|
|
የአስተዳደርና
ፋይናንስ መምሪያ
በዳይሬክተር የሚመራ
ሲሆን በውስጡም
የፋይናንስ ዩኒት፣
የሰው ኃይልና ስልጠና
ዩኒት፣ የንብረት
አስትዳደርና ጠቅላላ
አገልግሎት ዩኒት እና
የኢንፎርሜሽን
ቴክኖሎጂ ዩኒትን
ይይዛል፡፡ መምሪያው
ከዳይሬክተር
በተጨማሪ ምክትል
ዳይሬክተር አለው፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩም
በዋነኛነት የንብረት
አስተዳደርና ጠቅላላ
አገልግሎት ዩኒትን
በበላይነት
ይመራል፡፡ መምሪያው
በአራቱም ዩኒቶች ወደ
ሰባ የሚጠጋ የሰው
ኃይል አለው፡፡ እያንዳንዱ
ዩኒት በዋነኛነት
የሚያከናውነውን
ተግባር ለመዘርዘር
ያህል የመምሪያው
የፋይናንስ ዩኒት
በተለይ ከፋይናንስ
አስተዳደርና ከበጀት
ጋር የተያያዙ
ጉዳዮችን ያደራጃል
በዚህ መሠረት
የኮሚሽኑን የተለያዩ
መሣሪያዎችና
አገልግሎቶች በጀት
በማዘጋጀት
የኮሚሽኑን አጠቃላይ
የገንዘብ አጠቃቀምና
አያያዝ
ይቆጣጠራል፡፡ የሰው
ኃይልና ስልጠና ዩኒት
የኮሚሽኑን ሠራተኞች
አስተዳደር ደንብ
በመከተል ለኮሚሽኑ
የሚያስፈልጉ
ሠራተኞችን በቅጥር፣
በዝውውርና በእድገት
እንዲሟሉ
ያደርጋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የኮሚሽኑ
ሠራተኞች ተገቢውን
ሥልጠና እንዲያገኙ
በየጊዜው ክትትል
በማድረግ
የሚያስፈፅም ሲሆን
በተጨማሪም
የሠራተኞችን
የጡረታ፣ የሥራ
መልቀቂያ፣ የፈቃድ
እና ሌሎች ጉዳዮችን
ያስፈፅማል፡፡ የንብረት
አስተዳደርና ጠቅላላ
አገልግሎት ዩኒት
ደግሞ ለኮሚሽኑ
አስፈላጊ የሆኑ ቋሚና
አላቂ ዕቃዎችንና
አገልግሎቶችን
በመግዛት ያሠራጫል፣
ያስተዳድራል፣
የጥገና ጉዳዮችንም
ተከታትሎ
ያስፈፅማል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የኮሚሽኑን
ተሽከርካሪዎች
የማስተዳደር፣
የማሰማራት
የማስጠገን እና
የኢንሹራንስ
ጉዳዮችን የመከታተል
ኃላፊነት የተሰጠው
ለዚህ ዩኒት ነው፡፡
የኮሚሽኑን ሕንፃ
የማስተዳደር፣ ልዩ
ልዩ ጥገናዎችን
የማስፈፀም፣
የአገልግሎት
ክፍያዎችን የመፍቀድ
እና ሌሎች ተመሳሳይ
ጉዳዮችን ማከናወን
የዚህ ዩኒት የሥራ
ድርሻ ነው፡፡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዩኒትም ተጠሪነቱ ለአስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ሲሆን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለኮሚሽኑ የሚያስፈልገውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያከናውነው ይህ የሥራ ክፍል ነው፡፡ |