የፀረ-ሙስና
ዐቃቤ ሕግ መምሪያ
በፌደራሉ
የሥነምግባርና
ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ሥር ከተደራጁት
ዓላማ አስፈፃሚ
መምሪያዎች አንዱ
ነው፡፡ መምሪያው
የተጣለበትን
ተግባርና ኃላፊነት
ለመወጣት
እንዲያስችለው በቂ
ባለሙያዎች
እንዲኖሩት ሆኖ
የተቋቋመ ነው፡፡
ይሁንና
በአሁኑ ጊዜ
የተወሰኑ ዐቃቢያነ
ሕጐች ብቻ ያሉት
በመሆኑ የሰው ኃይል
እጥረት የሚታይበት
ነው፡፡
መምሪያው
የተደራጀበት ዋና
ዓላማ በሙስና
ወንጀል ተጠርጥረው
ምርመራ
የተጣራባቸውን
ፋይሎች መርምሮ
ወንጀል ፈፃሚ
ተጠርጣሪዎችን
ስልጣን ባለው ፍ/ቤት
ክስ መስርቶ
ተገቢውን ቅጣት
እንዲያገኙ ማድረግ
እና በሙስና ወንጀል
የተገኘን ንብረት
በማሳገድ እና
እንዲወርስ
በማድረግ
በፀረ-ሙስና ትግሉ
ጉልህ የሙስና
ወንጀል የመከላከል
ተግባርን ውጤታማ
ማድረግ ነው፡፡
ይህን
ዓላማ ተፈፃሚ
ለማድረግ መምሪያው
ከሚያከናውናቸው
ተግባራት መካከል
ዋና ዋናዎቹ፡-
·
በወንጀል
ሕግ እና በሌሎች
ሕጐች የሙስና
ወንጀሎች ፈፅመዋል
ተብለው በተጠረጠሩ
ግለሰቦች ላይ
ምርመራ
የተጣራባቸው
የምርመራ መዛግብት
ሲደርሱት
በማጥናትና
በመመርመር በቂ
ማስረጃ
ያልተገኘባቸውን
ክስ ሊቀርብባቸው
አይገባም የሚል
ውሣኔ በመስጠት
ይዘጋል፣ ተጨማሪ
ምርመራ
የሚያስፈልጋቸውን
የምርመራ መዝገቦች
ተጨማሪ ምርመራ
ተደርጐ ምርመራው
ተጠናክሮ ውጤቱ
እንዲቀርብለት
ለመርማሪው አካል
ይመልሳል፣ ክስ
ለመመስረት
የሚያስችል በቂ
ማስረጃ
በተሰባሰበባቸው
የሙስና ወንጀል
ምርመራ መዝገቦች
ላይ የወንጀል ክስ
በፍ/ቤት መስርቶ
ተገቢውን በመፈፀም
የመፋረድ፣
·
በሙስና
ወንጀል ድርጊት
ከተገኘ ንብረት ጋር
በተያያዘ በምርመራ
ላይ ያሉ ሰዎች ሀብት
በፍ/ቤት ትዕዛዝ
እንዳይንቀሳቀስ
የማሳገድ፣
·
በሙስና
ወንጀል የተገኘ
ለመሆኑ
የተረጋገጠን
ማንኛውንም ንብረት
ወይም ሀብት በፍ/ቤት
ትዕዛዝ
እንዲወረስና
በሀራጅ ተሸጦ ወይም
ሳይሸጥ ለመንግሥት
ገቢ እንዲሆን
የማድረግና
·
ስለመመርመርና
ስለመክሰስ
በወንጀለኛ መቅጫ
ሕግ ሥነሥርዓትና
በሌሎች ሕጐች
ለዐቃቤ ሕግ በተሰጠ
ሥልጣን መሠረት
ኮሚሽኑን
በሚመለከቱ የሙስና
ወንጀል ጉዳዮች ላይ
ተገቢውን የመፈፀም
ተግባራትን
ያከናውናል፡፡
የፀረ-ሙስና
ዐቃቤ ሕግ
መምሪያ ከሌሎች
የፍትህ አካላት ጋር
ያለው ግንኙነት