የፌደራል
የሥነምግባርና
የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን ሕግ
አገልግሎት
ተጠሪነቱ
ለኮሚሽነሩ ሲሆን
የአገልግሎት
ኃላፊና አንድ
የሕግ አማካሪ
ይዞ
የተደራጀ ነው፡፡
አገልግሎቱ
ከሚያከናውናቸው
ዋና ዋና ተግባራት
መካከል
ˇ
ከኮሚሽኑ
በሚቀርቡለት
ጉዳዮች ላይ የህግ
ምክር መስጠት፣
ˇ
የህግ
ሰነዶችን
ማዘጋጀት
እንዲሁም በሌሎች
መምሪያዎችና
አገልግሎቶች
በሚዘጋጁ
ደንቦችና
መመሪያዎች ላይ
አስተያየት
መስጠት፣ በሥራ
ላይ ያሉ
ደንቦችንና
መመሪያዎችን
ችግር እያጠና
የማሻሻያ
ሀሳቦችን
ማቅረብ፣
ˇ
ኮሚሽኑን
በሕግ ክርክር/
ጉዳይ/ መወከል፣
ˇ
በኮሚሽኑ
ማቋቋሚያ አዋጅ
ላይ በመመስረት
ደንብና
መመሪያዎችን
ማዘጋጀት
እንዲሁም በሌሎች
ተዘጋጅቶ ሲቀርብ
በማዳበር
ማጠናቀቅ፣
ˇ
የቅጥርና
የግዥ ውል
ማዘጋጀት
ይገኙበታል፡፡
ባለፉት
ሦስት ዓመታት
አገልግሎቱ
የተለያዩ
ተግባራትን
ያከናወነ ሲሆን
በተለይም
በኮሚሽኑ ተፈፃሚ
ሲሆን በቆየው
የሲቪል ሰርቪስ
ማሻሻያ ኘሮግራም
ላይ በመሳተፍና
የኮሚሽኑ
የተለያዩ
መምሪያዎችና
አገልግሎቶች
ማሻሻያ
ኘሮግራሙን
ተፈፃሚ
እንዲያደርጉ
በመርዳት እገዛ
አድርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ
የ2ዐ መመሪያዎች
ዝግጅት
የተከናወነ ሲሆን
ከቅሬታ ጋር
በተያያዘና
በሌሎችም
ምክንያቶች
ለቀረቡ ከ15ዐ በላይ
በሆኑ ሕግ ነክ
ጉዳዮች ላይ የሕግ
አስተያየት
ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል
አገልግሎቱ ለልዩ
ልዩ ጉዳዮች 1ዐዐ
የሚሆኑ ረቂቅ
የኮንትራት
ስምምነቶችን
በማዘጋጀት
ኮሚሽኑ
ከሚመለከታቸው
ወገኖች ጋር
የሕግ ውል
እንዲገባ ድጋፍ
አድርጓል፡፡