የኮሚሽኑ ዓላማዎች

ኮሚሽኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

  1.   አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ትምህርቶችን በማስፋፋት የነቃ እና ሙስናን ሊሸከም የማይችል ሕብረተሰብ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፣  

2.      አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የሙስና ወንጀልን እና ብልሹ አሠራርን መከላከል፣

       የሙስና ወንጀልን እና ብልሹ አሠራርን ማጋለጥ፣  

       መመርመር እና መክሰስ፣    

    

  2        የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባር

ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

1.      አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ስለሙስና ጎጂነት የህዝቡ ንቃተ ህሊና እንዲጎለብት በማስተማር እና መልካም ሥነምግባር በሕዝብ አገልግሎት እና በኀኀብረተሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ በማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፣

2.      አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በመንግስት መ/ቤቶች እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሰራር ሥርአቶችን በማጥናት ወይም እንዲጠኑ በማድረግ እንዲሻሻሉ ማማከርና ማሳሰብ፣ የአሰራር ስርአቶቹ የተሻሻሉ መሆናቸውን መከታተል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ተገቢ  የሆነው እርምጃ እንዲወሰድ ወይም ውሳኔ እንዲሰጥ አግባብ ላለው አካል በማሳወቅ ወይም በማሳሰብ ሙስናን የመከላከል፣ በሌሎች ሰዎች ሲጠየቅ ተመሳሳይ ምክርና ድጋፍ የመስጠት፣

3.      በመንግስት መ/ቤቶች እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ከባድ የሥነምግባር መጣስ ስለመፈጸሙ ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው የማጣራት ወይም እንዲጣራ የማድረግ እና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ የመከታተል፣

4.      በመንግስት መ/ቤቶች ወይም በመንግስት ልማት ድርጅቶች ወይም ፌዴራል መንግስቱ ለክልሎች ከሚሰጠው ድጎማ ጋር በተያያዘ በክልል መ/ቤቶች በወንጀል ህግ እና በሌሎች ሕጎች ውስጥ የተመለከቱት የሙስና ወንጀሎች በመንግስት ሰራተኞች ወይም ባለስልጣኖች ወይም በሌሎች ሰዎች ስለመፈጸማቸው ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው የመመርመርና የመክሰስ ወይም እንዲመረመር ወይም እንዲከሰስ የማድረግ፣

5.      ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው  በማናቸውም ባንክ የሚገኝ የተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ በኮሚሽነሩ ትእዛዝ እንዲመረመር የማድረግ፣ መረጃ የማግኘት እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲከበር የማድረግ፣

6.      ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በምርመራ ላይ ያሉ ሰዎች ሀብት በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳይንቀሳቀስ የማድረግ፣ በሙስና ወንጀል የተገኘ ለመሆኑ የተረጋገጠን ወይም በሙስና ወንጀሉ ከተገኘው ጥቅም ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ማናቸውንም ንብረት ወይም ሀብት በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲወረስና በሐራጅ ተሸጦ ወይም ሳይሸጥ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን የማድረግ፣

7.      አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በህግ በሚደነገገው መሰረት የመንግስት ባለስልጣኖችን እና በህግ ሀብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ያለባቸውን የመንግስት ሰራተኞች ሀብትና የገንዘብ ጥቅሞች መዝግቦ የመያዝ ወይም ተመዝግበው እንዲያዙ የማድረግ፣

8.      አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ለሙስና ወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች የአካልና የሥራ ዋስትና ጥበቃ የሚሰጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ በህግ በሚወሰን መሰረት ጥበቃ የመስጠት፣

9.      ሙስናን በመታገል እና በመከላከል ረገድ ጥሩ ውጤት ያስገኙ ሰዎችን እና መ/ቤቶችን አወዳድሮ ለሽልማት የሚበቁበትን ሥርአትና መለኪያ የመዘርጋት፣ ሲጸድቅም ተግባራዊ የማድረግ፣

10.  የሕግ አውጪና የዳኘነት አካላትን ሳይጨምር ለመንግስት መስሪያ ቤቶችና ለመንግስት ልማት ድርጅቶች የሚያገለግሉ የሥነምግባር ደንቦች መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ ወይም ማዘጋጀት እና አፈጻጸማቸውን የመከታተል፣ ከሕግ አውጭ እና ከዳኝነት አካላት ጥያቄ ሲቀርብለት በሥነምግባር ደንብ አዘገጃጀት ረገድ ምክር የመስጠት፣

11.  አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የሥነምግባር አውታሮችን የማስተባበር፣

12.  አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ሥነምግባርን እና ሙስናን በተመለከተ ጥናትና ምርምር የማድረግ እና ተመሳሳይ ሥራዎችን የመደገፍ፣ የኮሚሽኑን አላማዎች ለማራመድ የሚረዱ ሪፖርቶችን እና ቴክኒካዊ ጥናቶችን አሳትሞ የማሰራጨት፣

13.  አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የጸረ ሙስና ህጎች መከበራቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ስለአፈጻጸማቸው የምክር አገልግሎት የመስጠት፣

14.  በመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውስጥ የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲቋቋም ድጋፍ የማድረግ፣

15.  ለክልሎች አስፈላጊውን የምክርና የድጋፍ አገልግሎት የመስጠት፣

16.  ተመሳሳይ አላማ ካላቸው አገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አካላት ጋር ግንኙነትና ትብብር የመፍጠር፣

17.  የንብረት ባለቤት የመሆን፣ ውል የመዋዋል፣ በራሱ ስም የመክሰስና የመከሰስ፣

18.  በሕግ የሚሰጡትን እና ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን የማከናወን፡፡