|
6 መቶ ሺህ ጉቦ ጠይቆ ፣ ቅድመ ክፍያ 50 ሺህ ብር የተቀበለው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዳኛቸው ገመዳ አያንሳ 6 መቶ ሺህ ብር ጎቦ ጠይቆ ቅደመ ክፍያ 50 ሺህ ብር ሲቀበል በፌደራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ነሐሴ 17 ቀን 2002 ዓ.ም እጅ ከፍንጅ ተያዘ፡፡ አቶ ዳኛቸው በመንግስት የተሰጠውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በከፍተኛ ግብር ከፋይነት የተመዘገበን አንድ የግል ድርጅት በወጭነት ሊመዘገብለት የሚገበውን የድርጅቱን ወጭ በማሳነስና ገቢውን ያለአግባብ ከፍ አድርጎ በማስላት የግብር ከፋዩን ግብር መጠን 2.8 ሚሊዮን እንዲሆን አድርጓል፡፡ በዚህም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በሁኔታው ግራ በመጋባት መረጃው እነዲስተካከልላቸው ግለሰቡን ሲጠይቁት በመጀመሪያ 7 መቶ ሺህ ብር ጉቦ እንዲከፈለው እና እንደሚያስተካክል በመንገር በመጨረሻም ከ 6 መቶ ሺህ ያነሰ ብር እንደማይቀበል በማሳወቅ ከተበዳዩ የቅድመ ክፍያ ብር 50 ሺህ ሲቀበል ኮሚሽኑ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ ሊያዝ መቻሉን ለማወቅ ተችሏሎ፡፡ የመንግስትን ሃላፊነት ያለአገባብ በመጠቀም በህበረሰቡ ላይ በደል የሚያደርሱ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ መብቱን ሳይሸጥ ወደ ኮሚሽኑ ቀርቦ አስፈላጊውን ጥቆማ እንዲያቀርብ ኮሚሽኑ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ |
|
|
የሁለት
የትብብርና
የምክክር መድረኮች
መደበኛ ስብሰባዎች
ተካሄዱ የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙኃን እና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር የመሰረታቸው ሁለት የትብብርና የምክክር መድረኮች መደበኛ ስብሰባዎች ተካሄዱ፡፡ የኮሚሽኑ እና የመገናኛ ብዙኃን የትብብርና የምክክር መድረክ ጠቅላላ ጉባዔ 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ነሀሴ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. እንዲሁም የኮሚሽኑ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የጋራ የትብብርና የምክክር መድረክ 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነሀሴ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. በራስ ሆቴል በተካሄደበት ወቅት በጋራ መድረኮቹ የ2002 በጀት አመት እቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም በ2003 በጀት ዓመት ረቂቅ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የኮሚሽኑ እና የመገናኛ ብዙኃን የጋራ የትብብርና የምክክር መድረክ በ2002 በጀት ዓመት እቅድ ክንውን ሪፖርት በተመለከተ በተካሄደው ውይይት የጋራ መድረኩ በስልጠናና በልምድ ልውውጥ፣ በሥነምግባር ደንብ ዝግጅት፣ በኤሌክትሮኒክስ እና በህትመት ውጤቶች የመልካም ሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ትምህርትን በመስጠት፣ የሥነምግባር ሁኔታን የሚከታተል ባለሙያ በመመደብ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በተከናወኑ ተግባራትን እና በዚህ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ጠቅላላ ጉባዔው ውይይት አካሂዷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የስብሰባው ተሳታፊዎች በ2003 በጀት አመት ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ቀጣይነት ያለው የፀረ-ሙስና ትምህርት እና ስልጠና በሚሰጥበት፣ የመድረኩ አባላት ልምድ ልውውጥ በሚያደርጉበት፣ አሰራራቸው ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት በሚሆንበት እንዲሁም የሥነምግባር ደንብ የሌላቸው በሚያዘጋጁበት እና ያላቸው ደግሞ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በሚያጣጥሙበት ሁኔታ ላይ የሚያተኩረው ዕቅድ ተፈጻሚ እንዲሆን ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በተመሳሳይም የኮሚሽኑ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የጋራ የትብብርና የምክክር መድረክ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2002 በጀት አመት የሀብት ብክነትና የሥራ ድግግሞሽ ከማስቀረት ባሻገር በሙስና ላይ አንድ ወጥ አቋም በመያዝ ውጤታማ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡ የጋራ መድረኩ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች እንዲሁም በድሬዳዋ እና በአዲስ አበባ አስተዳደሮች መልካም ሥነምግባርን ለማስፋፋት እና ሙስናን ለመከላከል በሶስት አመታት ጊዜ 265 የቀበሌ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ክበባትን ለማቋቋም በቀረጸው ፕሮጀክት መሠረት በ2002 በጀት ዓመት በተጠቀሱት አካባቢዎች 100 የቀበሌ ክበባት ለማቋቋም ታቅዶ 63 የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ክበባት መቋቋማቸው በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በበጀት
ዓመቱ ፕሮጀክቱን
ተፈጻሚ በማድረግ
ረገድ ያጋጠሙ
ችግሮች እና
ለችግሮቹ የተሰጡ
የመፍትሄ
አቅጣጫዎችም
ቀርበው ውይይት
ተደርጎባቸዋል፡፡ በሁለቱ የጋራ መድረክ ስብሰባዎች ላይ ኮሚሽኑ ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ተግባራዊ በሚያደርገው ስትራተጂክ እቅድ ላይ የፍትህ ሥርዓት፣ የመሬት አስተዳደር፣ ከፍተኛ የመንግስት ግዢና ሽያጭ፣ የመንግሥት ገቢ አሰባሰብ እንዲሁም የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ የኮሚሽኑ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ ለግንዛቤ እንዲረዳም መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም. በጸደቀው የሀብት ማሳወቂያ እና ማስመዝገቢያ አዋጅ እና በአዋጁ አፈጻጸም ዙሪያ በኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ለተሰብሳቢዎቹ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ |
|
|
የሙስና ወንጀል በፈጸሙ ሦስት ግለሰቦች ላይ ቅጣት ተላለፈ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 26 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሙስና ወንጀል በፈጸሙ ሦስት ግለሰቦች ላይ እስከ 7 አመት ከ6 ወር በሚደርስ የእስር እና እስከ 20 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው ሳምራዊት ግዛቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅርንጫፍ ባንኮች ማስተባበሪያ መምሪያ የጽህፈት ሠራተኛ ሆና ስትሰራ ባንኩን ከማንኛውም ሕገወጥ ድርጊት መከላከል ሲገባት የህዝብና የመንግሥት ጥቅም በሚጎዳ አኳኋን በግል ሥራ ከሚተዳደሩትና በቅደም ተከተል 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ከሆኑት ሳምሶን ተፈራ ባዩ እና መስፍን ወልዴ ዜና ጋር በመመሳጠር የመንግስት ሥራን በማያመች አኳኋን በምራት የሙስና ወንጀል መፈጸሟን ይገልጻል፡፡ በተመሳሳይም ስማቸው ከላይ የተጠቀሰው 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ሀሰተኛ ስም በመጠቀም ከሁለተኛዋ ተከሳሽ ከሳምራዊት ግዛቸው ጋር በመመሳጠር በተግባር የሌለን #አክሽን ኤይድ ኢንተርናሽናል ሪሰርች ኤንድ ዴቨሎፕመንት; የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደተቋቋመ በማስመሰልና ታህሳስ 20 ቀን 1997 ዓ.ም. የመፈረም ስልጣናቸው የተነሳውን የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊን ስምና ፊርማ በሀሰት በመጠቀም መንግስታዊ ሰነድን በሀሰት ፈጥረው በማዘጋጀትና በመገልገል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ እንደከፈቱ የክስ መዝገባቸው ያስረዳል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ተከሳሾች ከ2ኛ ተከሳሽ ሳምራዊት ግዛቸው ጋር በመመሳጠር የባንክ ሂሳቡ እንዲከፈት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ በሌላ ግለሰብ ስም በ124 ብር በተዘጋጀ ሲፒኦ ላይ ቁጥሮችን በመጨመርና 124 ሺህ ብር አድርጎ በሀሰተኛ መንገድ በማዘጋጀት 3ኛ ተከሳሽ በሆነው በሳምሶን ተፈራ ስም ገንዘቡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ እንዲገባ አድርገዋል፡፡ ሶስተኛ
ተከሳሽ ሳምሶን
ተፈራ እ.ኤ.አ. በጁን 21
ቀን 2005 ዓ.ም. ባንኩን
በማታለል ወጪ
ካደረገው ብር 91,283.74
በተጨማሪ ሰኔ 29 ቀን
1997 ዓ.ም ብር 29,837.46
ሊያወጣ ሲሞክር እጅ
ከፍንጅ መያዙን
ኮሚሽኑ የመሰረተው
ክስ ጨምሮ
ያስረዳል፡፡ በሌላ በኩል አራተኛ ተከሳሽ የሆነው መስፍን ወልዴ ዜና በሐምሌ ወር 1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በብር 50.00 የቁጠባ ሂሳብ ከከፈተ በኋላ ከሌላው ግብረአበሩ ጋር በሀሰተኛ ስም ካቋቋሙት ድርጅት ሂሳብ ላይ ብር 1,500.00 እንዲተላለፍለት ማድረጉም በክሱ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት፣ ለሌሎች ለማስገኘት እና በመንግስት እና በህዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረስ በመላ ሀሳባቸውና አድራጎታቸው በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት በዋና ወንጀል አድራጊነት ሙሉ ተካፋዮች በመሆን የመንግስትን ሥራ በማያመች አኳኋን መምራት የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ሶሰተኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ በተጨማሪነት መንግስታዊ ሰነዶችን አስመስሎ በሀሰት በማዘጋጀት እና በመገልገል የተመሰረተባቸውን የሙስና ወንጀል ክስ ሊከላከሉ ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቀን በዋለው ችሎት ሳምራዊት ግዛቸው የተባለችው 2ኛ ተከሳሽ በ1ኛው ክስ ብቻ በ2 አመት ከ6 ወር እስራት እና በብር 16,700.00 እንዲሁም ሳምሶን ተፈራ እና መስፍን ወልዴ የተባሉት 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በሁለቱም ክሶች ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው በ7 አመት ከ6 ወር እስራት እና በብር 20,000.00 እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
በ2ዐዐ2 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ኮሚሽኑ ውጤታማ ተግባራትን አከናወነ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2ዐዐ2 በጀት ዓመት መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት በማጥራት፣ የሥነምግባር ትምሕርትን በማስፋፋት፣ የሙስና ወንጀልን በመከላከል፣ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በመቀበል፣ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማካሄድና የሙስና ወንጀል ለመፈጸማቸው በቂ ማስረጃ በተገኘባቸው ግለሰቦች ላይ በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ አጥፊዎችን በማስቀጣት ረገድ ለበጀት ዓመቱ የያዘውን ዕቅድ ከሞላ ጐደል በማሳካት ውጤታማ ተግባራትን አከናወነ፡፡ ኮሚሽኑ ከሚያዝያ ወር 1999 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየውን መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት የማጥራት ሥራ በበጀት ዓመቱ በማጠናቀቅ ተግባራዊ ለማድረግ እንደቁልፍ ተግባር በተያዘው ዕቅድ መሠረት ከየካቲት ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ ሲካሄድ የቆየውን ጥናት በበጀት ዓመቱ በማጠናቀቅና አዲሱን አሠራር በሁሉም የሥራ ሂደቶች ለመተግበር የሚያስችሉ መመሪያዎችን፣ ቅጾችን እና የቲም ቻርተር ሥራ ላይ በማዋል ጥናቱ ከሚያዝያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ወደሙሉ ትግበራ ተሸጋግሯል፡፡ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ትምህርትን በማስፋፋት በመልካም ሥነምግባር የታነፀና ሙስናን የሚፀየፍ ሕብረተሰብ ለመፍጠር በተያዘው ዕቅድ መሠረት በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ 5412 የሕብረተሰብ ክፍሎች በሥነምግባር እና በሙስና ጽንሰ ሐሳብ፣ በሙስና ወንጀል ሕጐች፣ በሙስና መከላከያ ስትራተጂዎችና ተያያዥነት ባላቸው ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአሰልጣኞች ሥልጠና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይም ‹‹ሥነምግባር›› በሚል ስያሜ በየሦስት ወሩ በሚዘጋጅ መጽሄትን፣ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የተዘጋጁ 6 ፖስተሮችን፣ ስቲከሮችን፣ የ2ዐዐ1 በጀት ዓመት ሪፖርትን፣ የኮሚሽኑን ኘሮፋይል፣ ብሮሸሮችን፣ ኢንሳይት ኒውስሌተርን፣ የፀረ-ሙስና ሞጁሎችን እና ለሌሎችም የሕትመት ውጤቶች ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በማሰራጨት እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት በማስተላለፍ ሕብረተሰቡ በመልካም ሥነምግባር እንዲታነፅና ሙስናን እንዲጠየፍ የማድረግ ሰፊ ሥራ መከናወኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የሥነምግባር አውታሮችን በማጠናከር ረገድ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ያላቋቋሙ ወይም የሥነምግባር መኮንን በጎደለባቸው 76 የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተለይተው ድጋፍና ክትትል የተደረገላቸው ከመሆኑም በላይ 29 መከታተያ ክፍሎች በአዲስ መልክ እንዲቋቋሙና ወይም አዲስ የሥነምግባር መኮንን እንዲተካባቸው ተደርገዋል፡፡ የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የሥልጠና፣ የልምድ ልውውጥ፣ የጥናትና የምርምር ውጤቶች የሚያገኙበትንና በባለሙያ ድጋፍ የሚታገዙበት ሁኔታም ተመቻችቷል፡፡ የሙስና ወንጀልንና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ዙሪያ መረጃዎችን መሠረት ባደረገ መልኩ በመንግሥት መ/ቤቶችና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች በተመረጡ ተግባራት ላይ የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያ ጥናት ለማካሄድ በተደረገው እንቅስቃሴ በ2ዐ ተግባራት ላይ ጥናት በማካሄድ ሪፖርቱ ለየተቋማቱ መላኩ ታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በቋሚነት ክትትል በሚያደርግባቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ስድስት ተግባራት ላይ የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያ ጥናት ለማካሄድ አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቦ ሪፖርቱ የተዘጋጀ ሲሆን በሁለት ተግባራት ላይ የተካሄደውን ጥናት አስመልክቶ ሪፖርት በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል የሙስና መከላከል የአሰራር ሥርዓት ጥናት በተካሄደባቸው ተግባራት ላይ የተመላከቱ ችግሮችን ለመቅረፍ ለየተቋማቱ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦችን ተግባራዊነትና ያስገኙትንም ውጤት ለመገምገም የሚረዳ የትግበራ ክትትል ሥራ ለማከናወን በተደረገው እንቅስቃሴ በተለያዩ መ/ቤቶች የአሠራር ሥርዓት ጥናት በተካሄደባቸው 26 ተግባራት ላይ የተጀመረው የትግበራ ክትትል ሥራ መጠናቀቁንና በሁለቱ ላይ ሪፖርት የማዘጋጀት ሥራው እየተከናወነ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ ዓመታዊ ሪፖርት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተጠረጠሩ የሙስና ወንጀሎች ላይ ምርመራ በማካሄድ በቂ መረጃ በተሰባሰበባቸው ጉዳዮች ላይ በፍ/ቤት ክስ ለመመስረት በተደረገው እንቅስቃሴ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቀረቡ 2915 ጥቆማዎችን ተቀብሏል፡፡ ከእነዚህ ጥቆማዎች፣ አቤቱታዎችና መረጃዎች መካከል 1584 ያህሉ በኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል የሚወድቁ በመሆናቸው የተለያየ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ ከኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ውጪ መሆናቸውም ተለይቷል፡፡ የሙስና ወንጀሎችን በመመርመር ረገድም ካለፈው በጀት ዓመት የተሸጋገሩትን ጨምሮ በጠቅላላው በ615 የምርመራ መዝገቦች ላይ ምርመራ ተደርጎ የ371 ጉዳዮች ምርመራ ተጠናቅቋል፡፡ በሌላ በኩል በ45 የምርመራ መዝገቦች ላይ የቀረበው ጥቆማ አስተማማኝ ባለመሆኑ ምክንያት ምርመራቸው እንዲቋረጥ ሲደረግ ምርመራቸው በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኝ የ362 የምርመራ መዛግብት ወደ 2003 በጀት ዓመት ተሸጋግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ በዐቃቤ ሕግ ተጠንተው ክስ ተመሠረተባቸው የምርመራ መዝገቦችብዛት 362 ሲሆን፣ በዐቃቤ ሕግ ውሳኔ በሙሉና በከፊል የተዘጉ መዝገቦች ብዛት ደግሞ 165 መሆናቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይም ለተጨማሪ ምርመራ የተላኩ መዝገቦች ብዛት 355፣ በኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ስር የማይወድቁ በመሆናቸው ምክንያት ለሌላ ዐቃቤ ሕግ መ/ቤት የተላኩ መዝገቦች ብዛት 85፣ በውክልና እንዲፈፀሙ ለውጭ ዐቃቤ ሕግ የተላኩ 17፣ ወደ 2003 በጀት ዓመት የተላለፉ የምርመራ መዝገቦች ብዛት 250 መሆኑን ከዓመታዊ ሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በበጀት ዓመቱ ፍርድ ከተሰጠባቸው 88 መዝገቦች ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉባቸው መዝገቦች ብዛት 85 ሲሆን በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾች ብዛት 213 መሆናቸውንና በነጻ የተሰናበቱ ተከሳሾች ደግሞ 21 መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህም ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ በፍ/ቤት ጥፋተኛ የማሰኘት አቅሙ (Conviction Rate) 96.6 በመቶ መሆኑን ያመለክታል፡፡ |
|
|
የሙስና ወንጀል በፈጸሙ ሦስት ግለሰቦች ላይ ቅጣት ተላለፈ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ሦስት ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በፈጸሙት የሙስና ወንጀል ተከሰው ማስረጃ የቀረበባቸው አቶ ታዲዎስ ራጅ እና አቶ ግሩም አብርሃም እያንዳንዳቸው በ4ዓመት፣ እንዲሁም አቶ ፈቃዱ ተክሌ በ3 አመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የባዮ ዳታ ሰራተኛ የነበረው ታዲዎስ ራጅ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ሥልጣን ሳይኖረው አጋጣሚ በመጠቀም #የስም;፣ #የትውልድ ቦታ;፣ #የሥራ ቦታ; ለማስተካከል በሚል ሀሰተኛ ምክንያት የ12 ግለሰቦችን ዕድሜ በመቀየር ሀሰተኛ ፓስፖርት እንዲያገኙ ማድረጉ በማስረጃ በመረጋገጡ ውሳኔው ተላልፎበታል፡፡ እንዲሁም የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ አፅዳቂ (ተቆጣጣሪ) የነበረው ግሩም አብርሃም ፓስፖርታቸው ከተቀየረላቸው 12 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በ1ኛ ተከሳሽ ታዲዎስ ራጅ አማካይነት ፓስፖርታቸው ላይ የተጠቀሰው ዕድሜ እንዲለወጥ ለማድረግ #ፓስፖርታችን ጠፍቶብናል; በሚል ሀሰተኛ ምክንያት ማመልከቻ እንዲያቀርቡ በመርዳት እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ፓስፓርት ላይ በሰፈረው እድሜ ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ግሩም አብርሃ የተባለው እና ስህተቱን ተመልክቶ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ሲገባው በፓስፖርቱ ላይ ማስተካከያው እንዲደረግ ወደ ህትመት ክፍል ማሳለፉ በማስረጃ በመረጋገጡ ቅጣቱ ተወስኖበታል፡፡ ፈቃዱ ተክሌ የተባለው በድለላ ሥራ የተሰማራ 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከ12ቱ ግለሰቦች ላይ ፓስፖርታቸውን በመቀበል እና ገንዘብ በመውሰድ የሁለት ግለሰቦች ፓስፖርት እንዲቀየር ለማድረግ አገናኝ ሆኖ መስራቱ በመረጋገጡ ውሳኔው የተላለፈበት ሲሆን ሶስቱም ተከሳሾች በግብረ አበርነት በፈጸሙት መንግስታዊ ሰነድን ወደ ሐሰት የመለወጥ የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የእስር ቅጣት እንደወሰነባቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
ለኮሚሽኑ ምስክር በሆነ ሰው ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል የተከሰሱ ተቀጡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመንግስት ገቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ባስከተለ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ በፍርድ ቤት ለመሰረተው ክስ ለኮሚሽኑ ምስክር ሆኖ በቀረበ ግለሰብ ላይ ጉዳት ያደረሱ አራት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በሰባት ዓመት ጽኑ እሥራት እና በብር 6ዐዐዐ.ዐዐ (ስድስት ሺህ ብር) እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት ቅጣቱን ያስተላለፈው ጀማል መሀመድ ሁሴን፣ ነጃ በዳዊ አህመድ፣ ስፍቱ ሙዘይን ኢሳ እና ም/ኢንስፔክተር ሠኢድ ሁሴን በተባሉ ተከሳሾች ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም አራቱ ግለሰቦች ለሁለት ዓመታት ያህል ከማንኛውም ህዝባዊ መብቶች ታግደው እንዲቆዩ የተወሰነባቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተከሳሾቹ ቅጣቱ የተላለፈባቸው በወንጀል ህግ ቁጥር 32 (1) (ሀ) እና በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 433/97 አንቀፅ 27 (1) መሠረት ኮሚሽኑ በመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ እንደሆነ ከፍርድ ውሳኔው ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
የኮሚሽኑ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት ውሳኔዎችን አስወሰነ በአስራ ሁለት የክስ መዝገቦች ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 18 ተከሳሾች እስከ 10 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በፍርድ ቤት የተወሰነባቸው መሆኑን የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በላከው ሪፖርት አስታወቀ፡፡ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ስምንት ወራት ባከናወናቸው ተግባራት በተለያዩ የክስ መዝገቦች ጥፋተኝነታቸው በተረጋገጠባቸው በእነዚህ ተከሳሾች ላይ እስከ 10 አመት የሚደርሱ የጽኑ እስራት ውሳኔዎችን ጨምሮ ከስድስት ወር እስከ ሶስት አመት የቀላል እስራት እና ከአንድ ሺህ እስከ አስር ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ማስወሰኑን በሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ምርመራ አጠናቆ ወደ ፍርድ ቤት ካቀረባቸው ከእነዚህ የክስ መዝገቦች መካከል አምስቱ የጽኑ እስራት እና አራቱ የቀላል እስራት ውሳኔ የተሰጣቸው ሲሆኑ የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ያገኙት ደግሞ አምስት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ የመንግስት ገንዘብ በማስመለስ ረገድ ጽህፈት ቤቱ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል በልማት ምክንያት ለሚነሱ ቤቶች መሰጠት የነበረበትና በመንግስት ቤት ለሚኖር ግለሰብ ተሰጥቶ የነበረ የ256 ሺህ 300 ብር ካሳ እንዲሁም በእምነት ማጉደል ወንጀል የተዘረፈ 48 ሺህ 734 ብር በፍርድ ቤት ውሳኔ ለመንግስት ተመላሽ ማስደረጉን ገልጿል፡፡ የንብረት እግድና ውርስን አስመልክቶ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል ደግሞ እያንዳንዳቸው ከ40 ሺህ እስከ 170 ሺህ ብር የሚገመቱ ሶስት መኪኖችን ጨምሮ 79 ሺህ 976 ብር ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን፣ ሌሎች ሶስት ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስፋታቸው በድምሩ 42 ሺህ 837 ካሬ ሜትር የሆነ አምስት የመሬት ይዞታዎችም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታገዳቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ጽህፈት ቤቱ በማስተማርና በሙስና መከላከል ዙሪያ የተለያዩ ጅምር እንቅስቃሴዎችን ያከናወነ ሲሆን በዚህ መሠረት በከተማዋ አስተዳደር ለሚገኙ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች በመልካም ሥነምግባር እና በሙስና ፅንሰ-ሐሳብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠቱም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿÿል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተቋሙን ዓላማ፣ የጥቆማ አቀራረብ፣ የሙስና ወንጀሎች መንስኤና ጉዳት እንዲሁም ተቋሙ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በኤፍ.ኤም ድሬ ሬዲዮ ጣቢያ የቀጥታ መስመር የስልክ ውይይት የተካሄደ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
የሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ሙስናን በመዋጋት ተስፋ ሰጪ ተግባራትን ማከናወኑ ተገለጸ የሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ባለፈው አንድ አመት ሙስናን በመዋጋት ዙሪያ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እንዳከናወነ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ሐምሌ 13, 2002 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡ በኮሚሽኑ የሥነምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ በርሄ የጥምረቱን የ 2002 የበጀት አመት የስራ ክንውን ሪፖርት ለስብሰባው ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ጥምረቱ ከተመሰረተ ገና አንድ አመት ቢሆንም ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን በማመዝገብ ላይ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ለመልካም ሥነምግባር የተለየ ክብር እና ትኩረት መስጠቱ፣ሙስና በመላው ህብረተሰብ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማሳየት የተደረገው ጥረት፣የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የሙያ ማህበራት አመራር አካላት ሙስናን ለመታገል ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ኮሚሽኑ ለስራው የሰጠው ትኩረት ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋፅኦ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ዳይሬክተሩ እንዳሉት ሁሉም የጥምረቱ አባላት በሙሉ አቅም ወደ ፀረ-ሙስና ትግሉ በመግባት ለበለጠ ውጤት ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ጥምረቱ የሚጠበቅበትን የሀገር አቀፉን የፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ ዓላማ ከዳር ለማድረስ የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል፡፡ ስብሰባው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አጽድቆታል፡፡ በተጨማሪም በ 2002 ዓ.ም የጥምረቱ የስራ ክንውን ሪፖርት፣ የጥምረቱን ቀጣይ መደበኛ ስብሰባ አጀንዳ፣ ቦታና አካሄድ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይም ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ከግሉ ዘርፍ፣ከተለያዩ ማህበራትና ከሚዲያ የተውጣጡ 15 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ሙስናን በተቀናጀና በተባበረ መንገድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመዋጋት ታልሞ ሰኔ 26-27, 2001 ዓ.ም በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሄደ ጉባዔ የመንግስት አካላት፣ የግሉ ዘርፍ እና የሲቪል ማህበረሰቡ ተወካዮች አባል የሆኑበት ሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት መቋቋሙ ይታወቃል፡፡ |
|
|
ለከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሠኔ 26 እስከ 30 2002 ዓ.ም. ከ1ሺ5መቶ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና ሰጠ፡፡ በኮሚሽኑ የፊት ለፊት ትምህርት ቡድን ዋና አማካሪ አቶ ከበደ ሲማ እንደገለፁት ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ስልጠና የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በሥነምግባርና በሙስና ፅንሰ ሀሳብ እንዲሁም በሙስና ወንጀል ሕጎች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡ ከሀሮማያ እና ከሐረር ካምፓሶች ለተውጣጡት ተመራቂ ተማሪዎች የተሰጠው ስልጠና ተማሪዎች ተመርቀው በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ለሥራ በሚሰማሩበት ወቅት ከሥነምግባር ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን፣ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመዋጋት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እንደሚያስጨብጣቸው ዋና አማካሪው ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ዙሪያ በቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ጠቁመው በቀጣይ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ቢካተት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ከተማሪዎቹ ከቀረቡ አስተያየቶች ለመረዳት መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጤና ሳይንስን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች በስልጠናው መሳተፋቸውን ገልጸው በቀጣይም በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች ተመሳሳይ ስልጠናዎችን ለመስጠት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡ |
|
|
በተባበሩት
መንግሥታት ድርጅት
የአደገኛ እጾችና
የወንጀል መከላከል
ቢሮ (UNODC) ያዘጋጀው
ስብሰባ ተካሄደ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደገኛ እጾችና የወንጀል መከላከያ ቢሮ (UNODC) ያዘጋጀውና አገሮች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን እንዴት እየተገበሩት እንደሚገኙ ለመገምገም የሚያስችል የእርስ በርስ የመገማገሚያ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚረዳ የሥራ መመሪያ (guideline) ኦስትሪያ-ቪየና በተካሄደ ስብሰባ ፀደቀ፡፡ እ.ኤ.አ ከጁን 28 - ጁላይ 2/2ዐ1ዐ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ አገራችንን በመወከል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ አዲሱ መንግሥቱ እና በኦስትሪያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው ላይ አገሮች ሙስናን ለመከላከል የፈረሙትን ኮንቬንሽን ምን ያህል በሥራ ላይ እያዋሉት እንደሚገኙ ለመገምገም እንዲቻል የተዘጋጀውን ረቂቅ መመሪያ (guideline) ለማጽደቅ ከተደረገው ውይይት በተጨማሪ የገምጋሚና የተገምጋሚ አገሮች እጣ እንደወጣም ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት አገራችን እ.ኤ.አ በ2ዐ13 ዓ.ም እንድትገመገምና በያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት ደግሞ ሳኦቶሜንና ኘሪንሲፔን ከሞንጐሊያ ጋር በመሆን እንድትገመግም ዕጣ እንደወጣላት ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮንቬንሽኑ አባል አገሮች የእርስ በርስ የመገማገሚያ ሥርዓቱን ተፈፃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ የደረሱበት የሥራ መዘርዘር (Terms of Reference) የኮንቬንሽኑ ፈራሚ አገሮች እ.ኤ.አ በታህሳስ ወር 2ዐዐ9 ዓ.ም በዶሐ-ኳታር ባደረጉት ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ እንደፀደቀ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል በመገማገሚያ ሥርዓቱ የሥራ መመሪያ (guideline) ላይ በወቅቱ የተደረገው ውይይት ስምምነት ላይ ሳይደረሰበት በመቅረቱ አሁን ቪየና በተደረገው የመጀመሪያው የገምጋሚ ቡድኑ (review group) ስብሰባ ላይ ረጅም ውይይት ተደርጎበት የጸደቀ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ አገራችን እ.ኤ.አ በ2ዐዐ3 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታትን የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን ፈርማ እ.ኤ.አ በ2ዐዐ7 ዓ.ም በማፅደቅ ኮንቬንሽኑን የተቀበሉ 145 አገሮችን ጎራ የተቀላቀለች መሆኗ ይታወቃል፡፡ |
|
|
ሁለት የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በታንዛኒያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሁለት የሥራ ኃላፊዎች ከሰኔ 14-19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በታንዛኒያ ኤቲክስ ሴክሬታሪያት የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ የሥራ ጉብኝቱ ዓላማ የመንግሥትን አሠራር በተጠያቂነትና በግልፅነት ላይ በመመሥረት ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ ተቀሜታ እንደሚኖረው ታምኖበት መጋቢት 21 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተወካዮች ም/ቤት የፀደቀውን የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚረዳ ግንዛቤ ለማግኘት መሆኑ ታውቋል፡፡ የሥራ ጉብኝቱ የተካሄደው የመንግሥት ተሿሚዎችን፣ የሕዝብ ተመራጮችንና የተወሰኑ የመንግሥት ሠራተኞችን ሀብት ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 668/2ዐዐ2 ለማስፈፀም ኮሚሽኑ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በቅድመ ሀብት ምዝገባና በምዝግባ ሂደት፣ የምዝገባ ትክክለኛነትን ከማረጋገጥ ጀምሮ ሪፖርት እስከማዘጋጀትና ማጠናቀር ባሉ ሂደቶች የሌሎች ሀገሮችን ልምድ ለማግኘት በተያዘው ዕቅድ መሠረት ተመሳሳይ ሥራ የሚያከናውነውን የታንዛንያ ተቋም ልምድ ለመቅሰም መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በልምድ ልውውጡ ሂደት ሁለቱ የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በታንዛኒያው ኢቲክስ ሴክሬታሪያት ዋና መ/ቤትና በአንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት ሴክሬታሪያቱ የሀብት ምዝገባውን ሥራ ሲጀምር አንስቶ አሁን ወደሚገኝበት የዕድገት ደረጃ ለመድረስ ባደረጋቸው ክንውኖች፣ ባስመዘገባቸው ስኬቶችና ባጋጠሙት ችግሮች እንዲሁም ችግሮቹን ለመቅረፍ በወሰዳቸውና ሊወስዳቸው ባቀዳቸው ተግባራት ላይ ልምድ ቀስመው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡ የታንዛኒያው የኤቲክስ ሴክሬታሪያት የ15 ዓመታት ዕድሜ ያለውና በአገሪቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት የሥነምግባር ሁኔታ ላይ አተኩሮ የሚሠራ ተቋም መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡ |
|
|
የሙስና ወንጀል በፈጸሙ አራት ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተለያየ የሙስና ወንጀል ክስ በመሠረተባቸው አራት ግለሰቦች ላይ ከስድስት ወር እስከ ሶስት ዓመት የሚደርስ እስራት እና እስከ ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ክፍሉ ገብሬ በአራዳ ክፍለ ከተማ ከሚገኘው የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ውስጥ በግምጃ ቤት ኃላፊነት እየሰራ በነበረበት ወቅት የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከግምጃ ቤት ተረክቦት ከነበረው የውሃ ቆጣሪ መካከል መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ግምቱ ብር 47‚736.00 /አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር/ የሆነ 180 የውሃ ቆጣሪ አጉድሎ በተከሰሰበት በስራ ተግባር ላይ የሚፈጸም የመውሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 3 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት የ3 ዓመት ከሶስት ወር እስራትና የ2000.00 ብር የገንዘብ ቅጣት ወስኖበታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት መ/ቤት ሾፌር የነበረው እንዳወቀ አየነው የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት እና በሥራ አጋጣሚ በእጁ በገባው የመንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ህዳር 10 ቀን 2002 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ ከሚያሽከረክረው የመ/ቤቱ መኪና የነዳጅ ታንከር ላይ ነዳጅ በቱቦ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ በመያዙ በግለሰቡ ላይ ኮሚሽኑ የመሠረተው ክስ በሰውና በኤግዝቢት ማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 4 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ በሁለት አመት ገደብ በ1 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዋና መምሪያ አባላት ሆነው በጎንደር ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል መምሪያ በጥበቃ ሥራ ላይ ተመድበው በሚሰሩበት ወቅት የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ ከተረከቡትና በሥራ አጋጣሚ ምክንያት በእጃቸው ሊገባ ከቻለው ትጥቅና የጦር መሣሪያ ውስጥ አጉድለው ለግል ጥቅሙ ያዋሉ የፖሊስ ባልደረቦች ኮሚሽኑ በመሰረተባቸው በሥራ ተግባር ላይ የመውሰድ እና የመሰወር የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ከስድስት ወር እስከ ዘጠኝ ወር በሚደርስ ቀላል እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡ የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል አንደኛ ተከሳሽ ረዳት ሳጅን መሐመድ ሀሰን ጥቅምት 9 2002 ዓ.ም ከተረከበው እና በሥራው አጋጣሚ ምክንያት በእጁ ሊገባ ከቻለው ትጥቅና የጦር መሣሪያ ውስጥ አንድ ኮቭ ክላሽ ጠመንጃ ከአምስት መጋዘኑ እና አንድ መቶ አምሳ ጥይቱ ጋር አጉድሎ ለግለሰቦች በመሸጥ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ፣ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ቻይና መንግስቱ ጥቅምት 20 ቀን 2002 ዓ.ም. ከተረከበው እና በሥራው አጋጣሚ በእጁ ሊገባ ከቻለው ትጥቅና የጦር መሣሪያ ውስጥ ስልሳ ጥይት አጉድሎ ለግል ጥቅሙ ያዋለው መሆኑን ኮሚሽኑ የመሰረተው ክስ ያስረዳል፡ ሁለቱም ተከሳሾች በተመሰረተባቸው ክስ ላይ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ሊከላከሉ ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሽ በቅደም ተከተል በስድስት እና በዘጠኝ ወር ቀላል እስራት እንዲቀጡ በመወሰንና ለሁለት ወር በእስር የቆዩበት ጊዜ ወደፊት ወንጀል ከመፈጸም ያስጠነቅቃቸዋል ብሎ በማመን ቀሪው የእስራት ጊዜያቸው በሁለት ዓመት ተገድቦላቸው ተከሳሾቹ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከእስር እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
በሥርዓተ ፆታ ዙሪያ አበረታች እንቅስቃሴ መኖሩ ተጠቆመ /ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ/ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት አጠናቆ ተግባራዊ ከማድረጉ ጎን ለጎን ሥርዓተ ፆታ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት አበረታች ጅምሮች መታየታቸውን የኮሚሽኑ የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ የሴቶች እና የህፃናት ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪ ወ/ት ሰላማዊት ፍርዲሳ የቢሮውን የሶስት ወራት እንቅስቃሴ አስመልክተው እንደገለጹት በኮሚሽኑ የተዋቀሩ አብዛኛዎቹ የሥራ ክፍሎች ፆታን በተመለከተ የሥራ አካል አድርገው (mainstream) ያስቀመጧቸውን እቅዶች ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የኮሚሽኑ አስተዳደር ደንብ እና ሌሎች መመሪያዎች ሲከለሱ የሥርዓተ ፆታ ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝና እንዲካተት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው፣ በሂደት ላይ ባለው የባላንስድ ስኮር ካርድ ሥራ ውስጥም አስፈላጊው ትኩረት ተሰጥቶት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ #የሴቶች ሚና በፀረ-ሙስና ትግል እና በሥነምግባር ችግሮች ምክንያት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች; በሚል ርዕስ አንድ የቴሌቭዥን ፓናል ውይይትና አንድ የሬድዮ ቴሌኮንፍረንስ ተዘጋጅቶ አየር ላይ መዋሉን የገለጹት አስተባባሪዋ፣ ኮሚሽኑ እያዘጋጀ በሚያሰራጫቸው መፅሄቶች፣ ኒውስ ሌተሮች፣ ብሮሸሮች እና በራሪ ወረቀቶች በፆታ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች ታትመው ለህብረተሰቡ እና ለኮሚሽኑ ሰራተኞች እንዲሰራጩ መደረጋቸው ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በኮሚሽኑ የተዋቀሩት የሥራ ክፍሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳዩ ያለውን አበረታች ጅምር አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ወ/ት ሰላማዊት ጠቁመው በጉዳዩ ዙሪያ አስፈላጊውን መረጃ እና ድጋፍ ለማድረግ የህፃናትና የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ |
|
|
በሦስት
ወራት ውስጥ በ11ዐ
የሙስና ወንጀል
ፈፃሚዎች ላይ
የቅጣት ውሳኔ
ተላለፈ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ክስ መስርቶባቸው ከነበሩ ተጠርጣሪዎች መካከል በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ጥፋተኛነታቸው በፍ/ቤት የተረጋገጠባቸው 11ዐ ተከሳሾች የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው፡፡ ከየካቲት - ሚያዝያ ወር 2ዐዐ2 ዓ.ም በነበረው ጊዜ በ31 የክስ መዝገቦች ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ ካስተላለፈባቸው ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል ዝቅተኛው የእስራት ቅጣት የአንድ ዓመት፣ ከፍተኛው የ21 ዓመት ሲሆን በገንዘብ ደግሞ ከብር 3ዐዐዐ እስከ ብር 5ዐ,ዐዐዐ የሚደርስ ቅጣት የተወሰነባቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ የቅጣት ውሳኔው በግለሰቦቹ ላይ የተወሰነው በሥልጣን አላግባብ በመገልገል፣ የመንግሥት ሠነድ በመሠረዝና በመደለዝ፣ በሥልጣን በመነገድ፣ የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን በመምራት፣ የማይገባ ጥቅም በመቀበል፣ ጉቦ በመቀበልና እምነት በማጉደል የሙስና ወንጀሎች ሲሆን ከነዚህ መካከል 91 ወንዶችና 19 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ የፍርድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ተከሳሾች መካከል በኮልፌ-ቀራንዮ ክ/ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ የነበረው ወንድወሰን አለሙ በቀለ እና በፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የሂሳብ ሠራተኛና የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ተወካይ ሆኖ ይሰራ የነበረው ጐሹ አንዱዓለም ልመንህ በተለያዩ የክስ መዝገቦች በተመሰረቱባቸው የሙስና ወንጀል ክሶች ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው የ21 ዓመታት የእስራት ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ወንድወሰን አለሙ በቀለ በሌሎች የክስ መዝገቦችም ተጨማሪ ክስ ተመስርቶበት የክስ ሂደቱን እየተከታተለ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ በአሶሳ ከተማ ተካሄደ የፌደራል እና የክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እና አግባብነት ያላቸው አካላት የጋራ ጉባዔ ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ ከሰኔ 9-1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው ላይ የጋራ ጉባዔውን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎችን አፈፃፀም የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ የተደመጠ ከመሆኑም በላይ የ2ዐዐ2 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት ሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ ሪፖርትን መሠረት ያደረገ ግምገማ እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይም ‹‹በውጭ ዕርዳታ አጠቃቀም የፀረ-ሙስና ተቋማት ሚና›› በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ጉባዔው እንደተነጋገረም ለመረዳት ተችሏል፡፡ በጉባዔው ላይ የትግራይ፣ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች በፍትሕና በፀጥታ አካላት የተወከሉ ሲሆን፣ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያቋቋሙ የቀሪዎቹ ክልሎች ደግሞ በየኮሚሽኖቻቸው የሥራ ኃላፊዎች መወከላቸው ታውቋል፡፡ የጋራ ጉባዔው በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን፣ ሰባተኛው መደበኛ ጉባዔ ከጥር 6-7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ |
|
|
ኮሚሽኑ ያካሄደው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ወደሙሉ ትግበራ መሸጋገሩን የተመለከተ ዝግጅት ተካሄደ የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከየካቲት ወር 2ዐዐ1 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየው የመሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ጥናት ከሚያዝያ 1 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ጀምሮ ወደሙሉ ትግበራ መሸጋገሩን ለማብሰር የተዘጋጀና ሁሉንም የኮሚሽኑን ሠራተኞች ያሳተፈ ዝግጅት ተካሄደ፡፡ በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ግንቦት 21 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ለግማሽ ቀን የተካሄደው ዝግጅት ዓላማ በአንድ በኩል በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እየሆነ በሚገኘው የሥራ ሂደት ለውጥ ላይ ሁሉም የኮሚሽኑ ሠራተኞች የጋራ ግንዛቤ ይዘው ወደሙሉ ትግበራ እንዲገቡ ለማስቻል ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኮሚሽኑ ሠራተኞች ለውጡ ወደ ሙሉ ትግበራ መሸጋገሩን በይፋ አውቀው የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት ጠንክረው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡ በዚሁ ዝግጅት ላይ ከታህሳስ ወር አጋማሽ እስከ መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የቆየውን የመሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ለውጥ የሙከራ ጊዜና ከሚያዝያ 1 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የሙሉ ትግበራ ወቅት አስመልክቶ በኮሚሽኑ የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ ከኮሚሽኑ ሠራተኞች በተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል ከየካቲት ወር 2ዐዐ1 ዓ.ም ጀምሮ ከኮሚሽኑ የተለያዩ መምሪያዎችና አገልግሎቶች በተውጣጣ የሰው ኃይል አማካኝነት በተደራጁ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ግብረኃይሎች ውስጥ በመሳተፍ በኮሚሽኑ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን ለማረምና ኮሚሽኑን ወደተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ለማድረስ በተካሄደው መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ጥናት ውስጥ ለተሳተፉ 37 የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በጥናቱ ወቅት በአሰልጣኝነትና በአማካሪነት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሦስት የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ |
|
|
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሁለት ጋዜጠኞች ክስ ተመሰረተባቸው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ሚያዚያ 13 እና 14 ቀን 2002 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር ውለው በነበሩት ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ ወርቁ እና አብዱልሰመድ መሐመድ ላይ ግንቦት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ክስ መሰረተ፡፡ ኮሚሽኑ የመሰረተው ክስ እንደሚያረዳው ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ ወርቁ በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ፕሮግራሞቸ ኤዲተር ፣አብዱልሰመድ መሐመድ ደግሞ የመዝናኛ ፐሮግራሞቸ ከፍተኛ ሪፖርተር ሆነው በመስራት ላይ እንዳሉ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት እና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ ለሥራ ብለው ከድርጅቱ የተረከቧቸን 19 የተለያዩ የኦዲዮና የኦዶዮቪዡዋል መረጃዎችን ከድርጅቱ እውቅና እና ፍቃድ ውጭ እና የድርጅቱን የኦዲዮና ኦዲዮቪዡዋል ላይብራሪዎች አጠቃቀም መመሪያና የኢዲቶሪያል ፖሊሲን በመጣስ በሳውዲ አረቢያ አልኢቅራ ለተባለ ለግል ቴሌቪዥን ጣቢያ በወንጀል ግብረአበሮቻቻው አማካኝነት አሳልፈው በመስጠታቸው በፈፀሙት በስልጣን ያለአግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ ወርቁ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2002 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ ለጊዜው ያልተያዙ የወንጀል ግብረአበሮቹ የሆኑትን አሚን እና ሃኒ የተባሉ የአልኢቅራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞችን በአቶ ኪያር መሐመድ አማካይነት በመተዋወቅ ኢማን የተባለው ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀረጻቸው ሥራዎች እንዳሉት ለኃይለየሱስ በመንገር ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲተረጎምለትና ለዚህም እንደሚከፈለው የተስማሙ መሆኑን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡ ኃይለየሱስ በዚሁ ሁኔታ በክፍያው ከተስማማ በኋላ ከኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የተረከባቸውንና ንብረትነታቸው የድርጅቱ የሆኑትን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀውልቶችን፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአክሱም እስከ ህዳሴ፣ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶችን፣ ዶክመንተሪ ቱሪዝምን፣ የኢትዮ-አሜሪካ ወዳጅነት አጀማመርን፣ ሐረር እና ታሪካዊ ባህሏን፣ የሰሜን ወሎ ላስታ ላሊበላን እና የኢህአዴግን እና የደርግን ጦርነት የሚያሳዩ 10 ፕሮግራሞችን ከጋዜጠኛው በተቀበለው ሃርድ ዲስክ ላይ መገልበጡ በክስ ላይ ተመልክቷል፡፡ አብዱልሰመድ በበኩሉ "ለሥራ" በሚል ከድርጅቱ የተረከባቸውን፣ የጥምቀት አከባበርነና የቱሪስት መስብህነቱን የሚያሳይ እና ‹‹The ancient Axum in Rome and to return it>> በሚል በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም፣ የጥምቀት በዓል አከባበርን (ለብቻው) ፣ የሶፍዑመርን ዋሻ፣ የድሬ ሼህ ሁሴንን ታሪክ፣ የአፋር ባህልን፣ የኮንሶ የርችት ምስልን፣ በአዲስ አበባ ስታዲዩም የዒድ በዓል አከባበርን ፣በደቡብ ክልል የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በዓል አከባበርን እና የንጉሥ ኃይለ ሥላሴን የቀብር ሥነ ስርዓት የሚያሳዩ 9 ፕሮግራሞችን፣ ሁለቱ ተከሳሾች በድምሩ 19 ፕሮግራሞችን ከድርጅቱ ፍቃድና ዕውቅና ውጭ በሃርድ ዲስክ መገልበጣቸውን ክሱ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ ኃይለየሱስ ለእነዚህ መረጃዎች የውጭ ጋዜጠኞቹ ብር 50,000 እንዲከፍሉዋቸው መጠየቁንና በመጨረሻም በብር 30,000 ተስማምተው በአቶ ኪያር መሐመድ አማካኝነት ቀብድ ብር 5,000 መቀበሉንና የውጭ ጋዜጠኞቹ በሃርድ ዲስክ ከወሰዱት 19 ፐሮግራሞች መሃከል የተወሰኑት ችግር ስለነበረባቸው በድጋሜ ተስተካክለው እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት ጋዜጠኛ ኃይለየሱስ የተበላሹትን(አልከፈት ያሉትን) እንደገና ካስተካካለ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ከፍለው እንዲወስዱ በመንገር ለዚህም ብር 10,000 ተቀብሎ የውጭ ጋዜጠኞቹ የተስተካከለውን ሃርድ ዲስክ እንዲወስዱ ካስቀመጠላቸው ቦታ ሳይወስዱ መያዛቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡ በሁለቱ ጋዜጠኞች ላይ ሁለት ክሶች የተመሰረቱ ሲሆን ሁለቱም ተከሳሾች በፈጸሙት የወንጀል ድርጊት በመንግስት ድርጅት ላይ ግምቱ ከ207 ሺህ ብር ያላነሰ ጉዳት ያደረሱ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት እና ተባባሪነት በፈጸሙት የቅጅና ተዛማች መብቶችን የማጣስ ወንጀል መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ |
|
|
በሙስና መከላከያ ስተራቴጂዎች ዙሪያ የአሰልጠኞች ስልጠና ተሰጠ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ ግብር ሰብሳቢ እና ፍቃድ ሰጭ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች እንዲሁም ከብዙሃንና ሙያ ማህበራት ለተውጣጡ የመድረክ አባላት፣ በሙስና መከላከያ ስትራቴጂዎች ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡ ይህ በኮሚሽኑ የሥነምግባር ትምህርት ባለሙያዎች በራስ ሆቴል ከግንቦት 2 እስከ 6 ቀን 2002 ዓ.ም ከግብር ሰብሳቢ እና ከፍቃድ ሰጭ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች እንዲሁም ከግንቦት 9 እስከ 11 ቀን 2002 ዓ.ም ኮሚሽኑ ከብዙሃንና ከሙያ ማህበራት ጋር ከመሰረታቸው የጋራ የትብብር እና የመክክር መድረኮች ለተውጣጡ ሰልጣኞች የተሰጠው ስልጠና በሥነምግባር እና በሙስና ጽንሰ-ሃሳብ እንዲሁም በሙስና ወንጀል ህጎች ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስልጠናው 35 የየተቋማቱ ባለሙያዎች እና 32 የጋራ መድረኮቹ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በስልጠናው ያገኙት ግንዛቤ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ እንዲሁም እንደ አንድ ዜጋ የሚጠበቅባቸውን የፀረ-ሙስና ትግል ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም ለመወጣት እንደሚያስችላቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
ተደራራቢ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተፈረደባቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 2 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተደራረቢ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ ሦስት ግለሰቦች እና በወንጀሉ በተባበሩ 6 ግለሰቦች ላይ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተከሰው ከተፈረደባቸው ግለሰቦች መካከል ‹‹ሻላ›› እና ‹‹ቦጋለ›› ከተባሉ ህገወጥ የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማህበራት ጋር በተያየዘ ሚያዚያ 14 ቀን 2002 ዓ.ም ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ በሃይሉ ለማ ድንቁ ፣ ወ/ሮ ደሃብ ገ/ሕይወት ብሩ እና አቶ ተክለድንግል ገ/ሚካኤል ማህረ እንዲሁም የወንጀሉ ታባባሪ የሆኑት እቴነሽ ዘርፉ ያደቴ ፣ ነጋሳ ፈየራ ሰንበቶ ፣ አወቀ ጫኔ አልማው ፣ ዘሪሁን በቀለ ፣ እንግዳ ዲና እና እየሩሳሌም ገ/ወልድ ይገኙበታል፡፡ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው በሃይሉ ለማ የተባለው ተከሳሽ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሃንዲስነት ተቀጥሮ ይሰራ በነበረበት ወቅት ‹‹ምሥራቅ ፀሃይ›› የሚባል ህገ-ወጥ የመኖሪያ ሕብረት ሥራ ማህበር በማቋቋም ማህበሩ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በህጋዊ መንገድ ተደራጅቶ ቦታ ያገኘ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን ፈጥሮ 162 የማህበሩ አባላት በህገ-ወጥ መንገድ 175 ካ.ሜ ቦታ የሊዝ ግምቱ ብር 59,815,000 የሆነ መሬት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ደሃብ ገ/ሕይወት የተባለችው ተከሳሽ ደግሞ በየካ ክ/ከተማ የማህበራት በድን መሪ ሆነ በምትሰራበት ወቅት በህገወጥ መንገድ የተደራጀውን ይህን ማህበር ሕጋዊ በማስመሰል ሃሰተኛ ደብዳቤ ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በመጻፍ ሕገወጡ ማህበር ውጤት እንዲያኝ ስታደርግ እቴነሽ ዘርፉ በበኩሏ ሀሰተኛው ማህበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ እንዲስተናገድ ማድረጓን ክሱ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ በተመሳሳይም ነጋሳ ፈየራ ፣ አወቀ ጫኔ ፣ ዘሪሁን በቀለ ፣ እንግዳ ዲና ፣ እየሩሳሌም ገ/ወልድ እና ተክለድንግል ገ/ሚካኤል ‹‹የምስራቅ ፀሃይ›› ማህበር አመራር አካላት ሆነው በመስራት በህገወጥ ሰነድ ሀሰተኛ ማህበር አቋቁመው ህገወጥ ጥቅም አግኝተዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረባበቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ፍ/ቤቱ በሃይሉ ለማን በ4 ዓመት እና በብር 10,000 ፣ ደሃብ ገ/ሕይወትን በ 7 ዓመት እና በብር 1,000 ፣ ተክለድንግል ገ/ሚካኤልን በ 7 ዓመትና በብር 8,000፣ እቴነሽ ዘርፉን በ 6 ዓመትና በብር 1,000 እንዲሁም ነጋሳ ፈየራ ፣ አወቀ ጫኔ ፣ ዙሪሁን በቀለ ፣ እንግዳ ዲና ፣ እና እየሩሳሌም ገ/ወልድ እያንዳንዳቸው በ 7 ዓመት እና በብር 8,000 እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ፍ/ቤቱ ሚያዝያ 14 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ‹‹ሻላ›› እና ‹‹ቦጋላ›› ከተባሉ ህገወጥ ማህበራት ጋር በተያየዘ በሃይሉ ለማን በ 11 ዓመት እና በብር 20,000 ፣ ደሃብ ገ/ሕይወትን በ15 ዓመት እና በብር 20,000 እንዲሁም ተክለድንግል ገ/ሚካኤልን በ5 ዓመት እና በብር 5,000 መቅጣቱን ሚያዝያ 15 ቀን 2002 በዜና መግለጫ መላካችን ይታወሳል፡፡ |
|
|
ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ 3 ግለሰቦች ተፈረደባቸው አዲስ አበባ/ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ/፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 6 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከባድ የአታላይነት የሙስና ወንጀል በመፈፀም ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥትን ገንዘብ በመዘበሩ 3 ግለሰቦች ላይ ከ5 እስከ 21 ዓመት እስራትና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው 1ኛ ተከሳሽ አቶ ጎሹ አንዱአለም ልመንህ በፌዴራል ፍርድቤቶች የፍርድ አፈጻጸም መምሪያ የሂሳብ ሰራተኛ እና የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ተወካይ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ስልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም በመንግስት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም አግኝቷል፡፡ አቶ ጎሹ አንዱአለም የፍርድ ባለመብት የሆነውን አቶ መኮንን ጥሩነህ እና የፍርድ ባለዕዳ በሆነው ጭላሎ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ መካከል በነበረው የፍርድ አፈጻጸም ክርክር ጉዳይ መነሻነት ለአቶ መኮንን ጥሩነህ ብር 756 666.66 (ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት 66/100 ብር) እንዲከፈላቸው በፍርድ ቤቱ በተወሰነው መሠረት ለፍርድ ባለመብቱ በፍርድ አፈጻጸም መምሪያ በተዘጋጁት ሶስት የተለያዩ ቼኮች መሰረት ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ተከፍሏቸው እያለ እንዳልተከፈላቸው በማስመሰል ተከሳሹ ለዚህ ወንጀል ማስፈጸሚያ የሚሆን የባንክ ሂሳብ በመክፈትና ደብዳቤ በማዘጋጀት የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ኃላፊውን አሳስቶ በማስፈረም 756666.67(ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት 67/100 ብር) የያዘ ቼክ ለአቶ መኮንን ጥሩነህ የሚከፈል በማስመሰል በሀሰተኛ ስም ባዘጋጀው ለበርሄ ገ/ሚካኤል እንዲሰጥ በማስተላለፍ ወደ ዳሽን ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ ገቢ እንዲሆን በማድረግና ከዚሁ ባንክ በሀሰት ባዘጋጀው ስም 775 342.81(ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ አርባ ሁለት ብር ከሰማንያ አንድ ሳንቲም) ወጪ አድርጎ መውሰዱ ተረጋግጦበታል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሹ ለአቶ መኮንን ጥሩነህ እና ለአቶ በርሄ ገ/ሚካኤል የሚከፈል በማስመሰል በተጭበረበረ መንገድ ሃሰተኛ ቼኮችን አዘጋጅቶ በር 1,025,267.81(አንድ ሚሊዮን ሃያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰልሳ ሰባት 81/100 ብር) ከመንግስት ሳጥን ወጪ አድርጎ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ በፈጸመው መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስሎ በማዘጋጀትና በመገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ የሆኑት የ1ኛ ተከሳሽ ባለቤት ወ/ሮ አስቴር አዘዘ ከ1ኛ እና ከ3ኛ ተከሳሽ ም/ኢንስፔክተር አብረሃም አያሌው ጋር በመመሳጠር በሙስና ወንጀል ከተገኘው ከዚህ ገንዘብ በስማቸው የተገዛውን አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ 1ኛ ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር ሀሰተኛ የሽያጭ ውል በማድረግ ለ3ኛ ተከሳሽ በማስተላለፍ ወንጀሉ ፍፃሜ እንዲያገኝ በማድረጋቸው ኮሚሽኑ ክስ ልመሰርትባቸው ችሏል፡፡ 3ኛ ተከሳሽ ም/ኢንስፔክተር አብርሃም አያሌው በበኩሉ ከ1ኛ እና ከ2ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር በወንጀል ፍሬ የተገዛውን ተሸከርካሪ ሕጋዊ ለማድረግ በማሰብ በሀሰተኛ የሽያጭ ውል ግዢ በመፈፀምና በምስራቅ ጎጃም ተሸከርካሪው ተዛውሮ በሥራ ላይ እንዲሰማራ በማድረግ የወንጀሉ ተባባሪ በመሆኑ ተከሶ ልፈረድበት ችሏል፡፡ ተከሳሾቹም በፍርድ ሂደቱ ኮሚሽኑ ያቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መከላከል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ በ1ኛ ተከሳሽ አቶ ጎሹ አንዱአለም ልመንህ ላይ በተለያየ መዝገብ የ21 ዓመት እስራት እና የብር 35,000.00 ቅጣት፣ በ2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አስቴር አዘዘ ኃይሌ ላይ የ5 ዓመት እስራትና የብር 5,000.00 ቅጣት እንዲሁም በ3ኛ ተከሳሽ ም/ኢንስፔክተር አብርሃም አያሌው ልመንህ ላይ የ7 ዓመት እስራትና የብር 10,000.00 የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
መንግስታዊ ሰነዶችን ወደ ሀሰት የመለወጥ የሙስና ወንጀል የፈፀመው ተፈረደበት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 25 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት መንግስታዊ ሰነዶችን ወደ ሀሰት በመለወጥ ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ ያዋለው ብርሃኔ አብርሃ ሐጎስ በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ፡፡ በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተከሶ የተፈረደበት ይህ ግለሰብ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ሪጅን ምዕራብ ዲስትሪክት ከሐምሌ 1 ቀን 1997 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም የዕቃ ግምጃቤት ፀሓፊ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት ለራሱ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት አስቦ የዲስትሪክቱ የዕቃ ግምጃቤት ይገለገልባቸው በነበሩት ኦሪጅናል የመጠየቂያ ሰነዶች ላይ ከፊትና ከኃላ ቁጥር በመጨመር እንዲሁም ቁጥሮችን በመሰረዝ እና በመደለዝ ግምታቸው ብር 1,216,213.82 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አሥራ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ሦስት 82/100) የሚሆኑ የኤልክትሪክ ዕቃዎችን ለግል ጥቅሙ አውሏል፡፡ በመሆኑም ተከሳሹ በኮሚሽኑ የቀረበበትን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ ከላይ የተጠቀሰውን የቅጣት ውሳኔ ሊያስተላልፍ ችሏል፡፡ |
|
|
የሁለት
የጋራ የትብብርና
የምክክር መድረኮች
መደበኛ ስብሰባዎች
ተካሄዱ የኮሚሽኑና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የትብብርና የምክክር መድረክ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ታህሳስ 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ውይይት ተደርጐበት የፀደቀውን ብሔራዊ የፀረ-ሙስና ቻርተርን መሠረት በማድረግ ተሻሽሎ በቀረበው የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ማሕበራት የትብብርና የምክክር የማቋቋማያና የሥራ መመሪያ ላይ በመወያየትና የተወሰኑ ማስተካከያዎችን በማድረግ አፅድቆታል፡፡ በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም የጋራ መድረኩን አደረጃጀት ለማስተካከል በተካሄደ የስምንት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ መሠረት በኮሚሽኑ እንዲያዙ መመሪያው ከሚደነግጋቸው የሰብሳቢነትና የፀሐፊነት ኃላፊነቶች ውጭ ከመንግሥትና ከግል የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም ከመገናኛ ብዙኃን ማሕበራትስድስት አባላት ተመርጠዋል፡፡ በተመሳሳይም የመገናኛ ብዙኃንን በመወከል ለአገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሚሆኑ ሦስት ተወካዮችን ለመምረጥ በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሥነሥርዓት ሬድዮ ፋና፣ የአዲስ አበባ የመገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ እና ካፒታል ጋዜጣ ተመርጠዋል፡፡ በተጨማሪም ሬድዮ ፋና የጋራ የትብብርና የምክክር መድረኩ ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ እንዲያገለግል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በሌላ በኩል የኮሚሽኑ እና የንግድና ዘርፍ ማሕበራት የትብብር እና የምክክር መድረክ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ሚያዝያ 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በማካሄድ በጋራ መድረኩ የማቋቋሚያና የሥራ መመሪያ ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡ ስምንት አባላት የሚኖሩት የጋራ የትብብር እና የምክክር መድረኩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ኮሚሽኑን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ማሕበራት ም/ቤት፣ ከኢትዮጵያ አገር አቀፍ ዘርፍ ማሕበራት ም/ቤት እና ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ም/ቤት በቅርብ ቀን የሚዋቀርበት ሁኔታ እንዲመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ |
|
|
የኮሚሽኑ
የውጤት ተኮር
አስራር ሥርዓት
ጥናት ተጀመረ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተግባራዊ ያደረገውን መሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት ውጤትን ተከትሎ ከሚያዝያ ወር አጋማሽ 2ዐዐ2 ዓ.ም ጀምሮ የውጤት ተኮር አሰራር ሥርዓት (Balance score card/ BSC) ጥናት ተጀመረ፡፡ ጥናቱ የተጀመረው ቀደም ብሎ ስለ ጥናቱ ስልጠና በወሰዱ 9 የኮሚሽኑ አባላትን በያዘ የቴክኒክ ኮሚቴ ሲሆን የኮሚቴው አባላት ከተለያዩ የኮሚሽኑ የሥራ ሂደቶች የተውጣጡና በኮሚሽኑ የማኔጅመንት ውሳኔ የተሰየሙ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከአቅም ግንባታ ሚኒስቴር የተመደቡ ባለሙያዎች በጥናቱ ዙሪያ ለኮሚቴው እገዛ የሚያደርጉ በመሆኑ ጥናቱን በተሟላ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማጥናት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ጥናቱ አላማ ያደረገው ኮሚሽኑ ተግባራዊ እያደረገ ያለው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራ ውጤት ተኮር የእቅድ አፈፃፀም ሥርዓት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ተግባራትን ቆጥረው ለፈፃሚ አካላት ለመስጠትና የአፈፃፀም ውጤትን ቆጥሮ በመቀበል ረገድ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያስችላል፡፡ ጥናቱ ሲጠናቀቅም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የኮሚሽኑን ተልዕኮ ለማስፈፀምና ሠራተኞች በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ ይዞ ከእለት ተእለት ተግባራቸው ጋር እንዲያስተሳስሯቸው ለማስቻል እንዲሁም የግለሰቡንና የቡድን ውጤት ሊለካ የሚችል የምዘና ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል፡፡ በቀጣይነትም ውጤታማ አፈፃፀምን ለማረጋገጥ የውጤት ተኮር አሰራር ዕቅድ ዝግጅትን በተመለከተ ለሁሉም የኮሚሽኑ ሠራተኞች ስልጠና እንደሚሰጥና ሁሉም የሥራ ሂደቶች በየደረጃቸው ያሉትን ሠራተኞች ባሳተፈ መልኩ የራሳቸውን የውጤት ተኮር ዕቅድ እንደሚያዘጋጁ ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በዱከም ከተማ የልምድ ልውውጥ አደረጉ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን እና አደረጃጀትን ጥቅም ላይ በማዋል ከከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚፈፀምን ሙስና መግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ በድሬዳዋ እና በዱከም ከተማ አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎች መካከል ሚያዝያ 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዱከም ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ተካሄደ፡፡ የልምድ ልውውጡ የተካሄደው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን በመክፈት በከተማው የመሬት ልማትና አስተዳደር የሚታዩ የሙስና ወንጀሎችን ለመግታት ከሚያደርገው ጥረት ጋር በተያያዘ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በዱከም ከተማ ተገኝተው የልምድ ልውውጡን እንዲያደርጉ ባመቻቸው ኘሮግራም መሠረት ነው፡፡ በዱከም ከተማ አስተዳደር ጂ.አይ.ኤስን መሠረት ያደረገ የካዴስትራል ሥርዓትን (GIS based cadastral System) የቢሮ የዳታቤዝ ሥርዓትን፣ የኮምፒዩተር መረብን፣ ድረገፅን እና ለሕብረተሰቡ ነፃ የስልክ መስመር መዘርጋትን ጨምሮ የተጠናከረ የሕዝብ ግንኙነት ሥርዓትን በማጣመር ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ እና ከሙስና እና ከብልሹ አሠራር የፀዳ አገልግሎት ለሕብረተሰቡ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በልምድ ልውውጡ ወቅት ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሬት ልማትና አስተዳደርን ተፈፃሚ ለማድረግ በዘረጋችው ቀልጣፋና ዘመናዊ ሥርዓት በአርአያነት እየተጠቀሰች የምትገኘው በዱከም ከተማና አካባቢዋ ለመኖሪያም ሆነ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ ቦታዎች በቅድሚያ ተለይተውና የቦታዎቹ ተፈላጊ መረጃዎች ተቀምረው በከተማው አስተዳደር የኮምፒዩተር ዳታ ቤዝ ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉ በመሆናቸውና በኢንፎርሜሽን መረጃ ሥርዓቱ አማካኝነት ክትትል ለማድረግ አመቺ ሁኔታ በመፈጠሩ የከተማው ቦታዎች ለተገልጋዮች የሚሰጡበት አሠራር ሥርዓትን በተከተለና ከአድልኦ ነፃ በሆነ መንገድ እንደሚከናወን በባለሙያዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡ የዱከም ከተማና አካባቢው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንዳየሁ ደጀኔ በወቅቱ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና አስተዳደሩን ዘመናዊ ለማድረግ ተግባራዊ ባደረገው አሠራር መሠረት ሕዝቡ በመስተዳድሩ ላይ ያለው አመኔታ ማደጉንና ይህም በአካባቢው ልማት ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጐለብት አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የተዘረጋው የአሠራር ሥርዓት በሙያተኛው ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠሩ ምክንያት የባለሙያዎች የሥራ ተነሳሽነት እንዲያድግ ከማድረጉም በላይ ከከተማ መሬት ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሕገወጥነትን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም እንዳስቻለ ገልፀዋል፡፡ ከልምድ ልውውጡ በኋላ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን የልዑካን ቡድን በመወከል የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና አስተዳደር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ አሊ እንደገለፁት፣ ኮሚሽኑ ከዱከም ከተማና አካባቢው አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ያደረገውን ጥረት አድንቀው፣ የድሬዳዋ ከተማ እስካሁን ድረስ ለልማቱ ብቻ ትኩረት ስትሰጥ መቆየትዋን ጠቅሰው በጉብኝቱ የመሬት መረጃ ሥርዓትን የማስተካከል ሥራ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ መገንዘባቸውን አስረድተዋል፡፡ ከድሬዳዋ
ከተማ አስተዳደር
የልምድ ልውውጡን
ለማድረግ ወደ ዱከም
ከተማና አካባቢው
አስተዳደር
የከንቲባውን
አማካሪ፣ የሥራ
አስኪያጅ አማካሪ
እና የመሬት ልማትና
አስተዳደር ም/ሥራ
አስኪያጅን ጨምሮ
ሰባት የከተማ
አስተዳደሩ የሥራ
ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች
የተሳተፉ መሆኑን
ለመገንዘብ
ተችሏል፡፡ |
|
|
ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግስት መሬት ልግል ጥቅም የዋሉ ተፈረደባቸው፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ ማህበር ሥም የሊዝ ግምቱ ብር 51,335,575.20 የሚሆን የከተማ ቦታ በመውሰድ የሙስና ወንጅል የፈፀሙ ሰባት ግለሰቦች ከ 2 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ500 እስከ 2000 ብር በሚደርስ ገንዘብ እንዲቀጡ ወሰነባቸው፡፡ በፌደራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተከሰው ከተፈረደባቸው ተከሳሾች መካከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ውስጥ ሥራ አስኪያጅ የነበረው ወንድወሰን አለሙ በቀለ፣የመሬት ልማት አስተዳደር የቡድን መሪ የነበረው ዮሴፍ ከበደ መርኔ ፣ የመሬት አስተዳደር የሊዝ አፈጻጸምና ክትትል ቡድን መሪ የነበረችው ገነት ማሞ ተምትሜ ፣ የመሬት ልማት አስተዳደር የቅየሳ ሠራተኛ የነበረው ሳምሶን በቀለ ቅጣው እና በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት አላዊ ሱሩር ቡሴር ፣ መሀመድ ሱሩር አብደላ እና ሙክታር ኑሪ ይገኙበታል፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ የመሰረተው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው በተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊነቶችና በባለሙያነት ተመድበው ይሰሩ የነበሩ እነዚህ ተከሳሾች የማይገባ ጥቅም ለማግኘት እና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ በሀሰተኛ ማህበር ስም በህገወጥ ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት(ኮንዶሚኒያም) መሥሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ለጠየቁ ነጋዴ ግለሰቦች ህገወጥ ትብብር በማድረግ እንዲሁም ዘመዶቻቸዉ የህገወጡ ማህበር አባል እንዲሆኑ በማድረግ በስልጣናቸው ያለአግባብ ተጥቅመዋል፡፡ በተመሳሳይም በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ግለሰቦች አግራው የመኖሪያ ቤቶች ሕብረት ሥራ ማኅበር የሚል ሀሰተኛ ማህበር በራሳቸው፣ በሚስቶቻቸው እና በዘመዶቻቸው ስም በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ አመራርና ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆን ተንቀሳቅሰው ለኮንዶሚኒየም መሥሪያ በሚውል መልኩ በንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያ ተከሳሾች አማካይነት ከ51 ሚሎዮን ብር በላይ የሚገመት መሬት ያለ አግባብ ወስደዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ፍ/ቤቱ መያዝያ 18 ቀን 2002 በዋለው ችሎት ወንድወሰን አለሙ በቀለ ፣ ዮሴፍ ከበደ መርኔ እና ገነት ማሞ ተምትሜ እያንዳንዳቸው በ 7 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 2000 ፣ አላዊ ሱሩር ቡሴር ፣ መሀመድ ሱሩር አብደላ እና ሙክታር ኑሪ ደግሞ እያንዳንዳቸው በ 3 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 2000 ፣ እንዲሁም ሳምሶን በቀለ ቅጣው በሁለት ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 500 እንዲቀጡ ወኗል፡፡ |
|
|
ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሬት በመሸጥ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ 7 ግለሰቦች ተፈረደባቸው አዲስ አበባ (ፌ.ሥ.ሙ.ኮ)፡- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎች ሚያዝያ 14 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሬት በህገ ወጥ መንገድ በመሸጥ ለራሳቸውና ለሌሎች ግለሰቦች የማይገባ ጥቅም በማስገኘት የሙስና ወንጀል በመፈጸም የተከሰሱ 7 ግለሰቦች ከ2-15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ከ500 ብር እስከ 20 ሽህ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው እነዚህ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በከተማው ክፍለ ከተሞች ተቀጥረው በሚሰሩበት ወቅት ከ1998-1999 ዓ.ም በህግ ወጥ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማህበራትን በማደራጀትና በስራ አጋጣሚ ያገኙትን ሚስጥር በመጠቀም ህገ ወጥ የሆነ ጥቅም ለራሳቸውና ለሌሎች ለማስገኘት አስበው በመንግስትና በህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት በማድረሳቸው ኮሚሽኑ ክስ የመሰረተባቸው ናቸው፡፡ ኮሚሽኑ በመሰረተው ክስ መሰረት 1ኛ ተከሳሽ በሃይሉ ለማ ድንቁ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦታና ቤት አስተዳደር መምሪያ ቴክኒሽያን ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በስራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ከኮምፒውተር ወደ ሲዲ ገልብጦ በመውሰድና ከስራው ከታገደ በኃላ ይህን በሕገወጥ መንገድ በሲዲ ያወጣውን ማስተር ፕላን መሠረት በማድረግና በኮሚፒውተር በመታገዝ በከተማው ያሉ ክፍት ቦታዎችን ለይቶ በማውጣት በወቅቱ ለማህበራት ይፈቀድ የነበረውን የቤቶች ፕላን እያዘጋጀ "ሻላ" እና "ቦጋለ" የተባሉ ሁለት ሕገወጥ የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማህበራትን በሙስና ወንጀሉ ተባባሪ ከሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ጋር በመተባበር አደራጅቷል፡፡ በዚህ መሠረት በእነዚህ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት የታቀፉ 468 አባላት ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው መሬት ያገኙ ለማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን፤ ደብዳቤዎችን፤ የመ/ቤቶችን ማህተሞች እና ሳይት ፕላኖችን መጠቀሙ በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡ በተመሳሳይም በቅደም ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደሀብ ገብረህይወት በየካ ክፍለ ከተማ የማህበራት ቡድን መሪ እና አባይ ለገሰ ወልዴ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሊዝ አፈጻጸም ውል አጣሪ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት በመንግሥት የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት መሠረት በማድረግና ከ1ኛ ተከሳሽ ከሃይሉ ለማ ድንቁ ጋር በጥቅም በመመሳጠር በሀሰተኛ መንገድ የመሰረቱትን "ቦጋለ" እና "ሻላ" የተባሉ ማህበራት ሀሰተኛ ፋይሎች በ1998 እና በ1999 ዓ.ም. ወደ ክፍለ ከተሞች መዝገብ ቤቶች በሕገወጥ መንገድ እንዲገቡ በማድረግ እና የማህበሩ አባላት እያንዳንዳቸው ለ1ኛ ተከሳሽ ብር 3 ሺህ እንዲከፍሉ በማስደረግ በግብረአበርነት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ ተክለድንግል ገ/ሚካኤል የተባለ 6ኛ ተከሳሽም ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር "ሻላ" የተባለውን ሀሰተኛ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር በመመስረትና በሀሰተኛ መንገድ የተዘጋጀውን የማህበሩን ፋይል በ1998 ዓ.ም በ2ኛ ተከሳሽ በደሐብ ገብረ ሕይወት አማካኝነት ወደየካ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤት እንዲገባ በማድረግ 248 የማህበር አባላት በህገወጥ መንገድ መሬት እንዲገኙ አድርጓል፡፡ በዚህም ለራሱና ለማህበራቱ ሕገወጥ ጥቅም በማስገኘት በመንግሥትና በህዝብ ላይ ጉዳት ማድረሱን የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ክስ ይዘረዝራል፡፡ በሌላ በኩል በቅደም ተከተል 7ኛ፣ 8ኛ እና 9ኛ ተከሳሽ የሆኑት መከተ ታደሰ፣ ዳንኤል በላይ እና ሀብታሙ መኳንንት በበኩላቸው በ1999 ዓ.ም. ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ተመሳጥረው በሕገወጥ መንገድ የጥቅሙ ተካፋይ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ክስ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በወንጀሉ ሥራ እና በተገኘው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የሊዝ ግምቱ ብር ከ205 ሚሊዮን 540 ሺህ ብር (ከሁለት መቶ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ሺህ ብር) በላይ የሚያወጣ የመንግሥት መሬት ለራሳቸው እና በሕገወጥ መንገድ ላደራጇቸው ማህበራት አባላት አከፋፍለው በመስጠት በሙሉ ሀሳባቸው እና አድራጎታቸው በግብረአበርነት በፈጸሙት በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ኮሚሽኑ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ በክሱ ሂደትም ኮሚሽኑ ያቀረበባቸውን የሰውና የሠነድ ማስረጃዎችን ለመከላከል ባለመቻላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ በኃይሉ ለማ ድንቁ በ11 ዓመት ፅኑ እስራትና በ 20 ሺህ ብር እንዲቀጣ ሲወስን፣ በ2ኛ ተከሳሽ ደሀብ ገብረ ህይወት በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር እንድትቀጣ ወስኗል፡፡ በተመሳሳይም 3ኛ ተከሳሽ አባይ ለገሰ ወልዴ እና 6ኛ ተከሳሽ የሆነው ተክለድንግል ገ/ሚካኤል እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡና በቅደም ተከተል የአንድ ሺህ ብር እና የአምስት ሺህ ብር ቅጣት አስተላልፎባቸዋል፡፡ በሌላ
በኩል ጉዳያቸው
በሌሉበት የታየው
በቅደም ተከተል
7ኛ፣ 8ኛ እና 9ኛ
ተከሳሽ የሆኑት መከተ
ታደሰ፣ ዳንኤል
በላይ እና ሀብታሙ
መኳንንት
እያንዳንዳቸው በ2
ዓመት እስራትና በ 500
ብር እንዲቀጡ
ወስኗል፡፡ |
|
|
ኮሚሽኑ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን በተዘጋጀ አውደ-ጥናት ላይ ተሳተፈ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመንግሥት የፋይናንስ ወጪ አስተዳደር ውስጥ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን በተጠራውና በደቡብ አፍሪካ- ጆሀንስበርግ ከመጋቢት 28 - ሚያዝያ 1 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተካሄደው የአፍሪካ አካባቢያዊ አውደ-ጥናት ላይ ተሳተፈ፡፡ በአውደ-ጥናቱ ላይ የተሳተፉት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ አዲሱ መንግሥቱ እንደገለፁት የአውደ-ጥናቱ ዓላማ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር ዘርፍ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚረዱ መንግሥታዊ አሰራሮችን፣ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን በተመለከተ ተሳታፊዎቹ ልምድ እንዲለዋወጡ ለማስቻል እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም አውደ-ጥናቱ በግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በፋይናንስ ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ ተቋማት በዓይነቱ አዲስ በሆነና በተጠናከረ መንገድ በብሔራዊና በአካባቢያዊ ደረጃ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ተግባራዊ የሚያደርጉበትን አሠራር ተፈፃሚ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር የተጠራ መሆኑን ም/ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል፡፡ በአውደ-ጥናቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አገራት ተወካዮች በፀረ-ሙስና ትግል ዙሪያ እና የዜጐቻቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚረዱ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ቃል የገቡ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይም በአውደ-ጥናቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የተለያዩ አገራት የኦዲት ቢሮዎች ተወካዮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት የፋይናንስ እና የሰው ኃይል ሥራ አመራርን መሠረት ባደረገና ሕጋዊ አሠራርን በተከተለ መልኩ ማከናወን የሚቻልበትን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ ም/ኮሚሽነሩ አክለውም በአውደ-ጥናቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የተለያዩ አገራት የፀረ-ሙስና ተቋማት ተወካዮች ከሕብረተሰቡና ከሲቪክ ማሕበራት ጋር ተባብረው ለመስራት የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡ ተወካዮቹ በተጨማሪም የከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሐብትና ንብረታቸውን የሚያስመዘግቡበት አሠራር እንዲሁም ለሙስና ወንጀል ጠቋሚዎች እና ለምስክሮች ከለላ የሚሰጥበት ሕግ በሁሉም ተሳታፊ አገራት ተግባራዊ የሚሆንበት አሠራር የሚዘረጋበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ከዚህ ጐን ለጐን የሙስና ወንጀሎችን በተለየ ሁኔታ የሚያዩ ችሎቶች ተደራጅተው የሙስና ክስ ጉዳዮች በፍጥነት እየታዩ ውሳኔ እንዲያገኙ ለማድረግ የበኩላቸውን ጥረት ለማድረግም መስማማታቸው ታውቋል፡፡ ለአራት
ቀናት በቆየው
አውደ-ጥናት ላይ
እንግሊዝኛ፣
ፈረንሳይኛና
ፖርቹጋልኛ ተናጋሪ
ከሆኑ 17 የአፍሪካ
አገራት ውስጥ
በሚገኙ በተለያዩ
ተቋማት ላይ
ክትትልና ቁጥጥር
እንዲያደርጉ
ከተቋቋሙ
ድርጅቶችና
ከፀረ-ሙስና ተቋማት
የተውጣጡ
ተሳታፊዎች
እንደተገኙ
ለመረዳት
ተችሏል፡፡
|
|
|
ከባድ
የሙስና ወንጀል
የፈፀሙ ግለሰቦች
ተፈረደባቸው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ በግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው ኤልያስ ስኑር መሐመድ የተባለው 1ኛ ተከሳሽ በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጄንሲ የመጠባበቂያና ምግብ ክምችት አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ለራሱ እና በንግድ ስራ ለሚተዳደረው ለ2ኛ ተከሳሽ አበበ ወልደሃና የማይገባ ብልፅግና ለማስገኘት በማሰብ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ በወንጀሉ ግብረአበር በመሆን ከባድ የአታላይነት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ የሆነው ኤልያስ ስኑር መሐመድ በኤጄንሲው ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት መስሪያ ቤቱ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ እንዲያወጣ የሰጠውን ውክልና በመጠቀም የመስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን የአቶ ሲራክ ሃይሉን እና በዚያው መስሪያ ቤት የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑትን የአቶ አለሙ ወልዴን ስም እና ፊርማ አስመስሎ በመስሪያ ቤቱ ቼኮች ላይ በመፈረም ከብሔራዊ ባንክ በተለያየ ጊዜ በድምሩ ከ6.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2ኛ ተከሳሽ ስም በተከፈተ አካውንት እንዲዛወር በማድረግ ከባድ አታላይነትና መንግስታዊ ሰነዶችን ወደ ሀሰት የመለወጥ የሙስና ወንጀል ፈፅሟል፡፡ አበበ ወልደሃና የተባለው ሁለተኛው ተከሳሽም በሙሉ ዕውቀቱና ፍቃዱ ተስማምቶ በኤልያስ ስኑር መሐመድ አማካኝነት ወደግል አካውንቱ ገቢ የሆነለትን ገንዘብ አውጥቶ በመጠቀሙ ከአንደኛው ተከሳሽ ጋር በግብርአበርነት በፈፀመው የሙስና ወንጀል ኮሚሽኑ ክስ ሊመሰርትበት ችሏል፡፡ አበበ ወልደሃና የተባለው ይህ 2ኛው ተከሳሽም የሙስና ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ተሰውሮ ከቆየበት ከሱዳን ሀገር ተይዞ በመምጣት ለፍርድ መቅረቡም ታውቋል፡፡ በፍርድ ሂደቱም ተከሳሾቹ ኮሚሽኑ ያቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቀን በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ኤልያስ ስኑር መሐመድ በ18 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 50,000.00 እንዲቀጣ ሲወስን፣ 2ኛ ተከሳሽ አበበ ወልደሃና ላይ ደግሞ የ10 ዓመት ፅኑ እስራትና የብር 45,000.00 የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
የ #ኮስት; የአፍሪካ ሻምፒዮኖችና የዓለም አቀፍ የአማካሪዎች ቡድን ስብሰባ ተካሔደ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚከሰተውን ሙስና እና ብልሹ አሠራር ለመከላከል እንዲቻል በተለይ መንግሥታት በሚያካሒዷቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ስምንት አገሮችን በማቀፍ የሚንቀሳቀሰውና #ኮስት; በሚል ስያሜ የሚታወቀው ኢኒሸቲቭ የአፍሪካ የ#ኮስት; ሻምፒዮኖች እና የዓለም አቀፍ የአማካሪዎች ቡድን ስብሰባ ከመጋቢት 28 - ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተካሔደ፡፡ ከአፍሪካ የኢትዮጵያ፣ የማላዊ፣ የታንዛኒያና የዛምቢያ የ#ኮስት; (Construction Sector Transparency Initiative “COST”) ሻምፒዮኖችን፣ ኢኒሸቲቩን በፋይናንስና በቴክኒክ የሚደግፉ ተቋማት እና የባለድርሻ አካላት ተወካዮችን ባካተተው እና መጋቢት 28 ቀን 2002 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተካሔደው ስብሰባ የየአገራቱ የ#ኮስት; ሻምፒዮኖች ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ያጋጠሟቸውን ችግሮች እንዲሁም ችግሮቹን ለመፍታት የተከተሉትን ስልት በተመለከተ ማብራሪያ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይም የኢንሺየቲቩ ዓለም አቀፍ የአማካሪዎች ቡድን አባላት ከመጋቢት 29 - ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ባካሔዱትና የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነርና በኢትዮጵያ የኮስት ሻምፒዮን ክቡር አቶ አሊ ሱለይማን በንግግር በከፈቱት ስብሰባ ላይ የኢኒሸቲቩ የስድስት ወራት የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሒዶበታል፡፡ በ"ኮስት" ዓለም አቀፍ የአማካሪዎች ቡድን ሰብሳቢ በመመራት የኢኒሸቲቩ ዓለም አቀፍ ሴክሬታሪያት፣ በኢኒሸቲቩ ታቅፈው ሙከራ በሚካሔድባቸው ስምንት አገራት የተወከሉ የዓለም አቀፍ አማካሪ ቡድኑ አባላት፣ ብሔራዊ የባለድርሻ አካላት ሊቀመናብርት እንዲሁም ኢኒሸቲቩን በፋይናንስ የሚደግፉ ተቋማት እና ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚያደርገው የዓለም ባንክ ተወካዮች በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ አገራቱ በኢኒሸቲቩ ማዕቀፍ ሥር ያከናወኑትን ተግባርና ያጋጠሟቸውን ችግሮች የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ የሐሳብ ልውውጥ ተደርጎበታል፡፡ ይህን ተከትሎም አባል አገራት ግንባታቸው ያለቀ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ጥናት (baseline study) ስለሚያካሂዱበት ሁኔታ እንዲሁም ግንባታቸው በሒደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከተያዘላቸው በጀት፣ ጊዜና ጥራት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ግምገማ ማካሔድ ስለሚቻልበት አሠራር (Assurance Process) በዓለም አቀፍ የ"ኮስት" ሴክሬታሪያት አማካኝነት ትምህርታዊ ማብራሪያ እንደተሰጠ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ በተጨማሪም የኢኒሸቲቩ ጊዜ ከሚጠናቀቅበት እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 30/2010 በፊት የግንባታ ፕሮጀክቶችን የተመለከተ መረጃ ለሕዝቡ መድረስ በሚቻልበት ሁኔታና ለኢኒሸቲቩ ድጋፍ ሊያደርጉ ከሚችሉ አካላት ጋር ግንኙነት ለመፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሙከራ አባል አገራት ተሞክሮ በመነሳት ውይይት ተካሒዷል፡፡ ዓለም አቀፍ የአማካሪ ቡድኑ ሥራውን ከጀምረ ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርትም ቀርቦ የተገመገመና ውይይት የተካሄደበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአገራችን የኢኒሸቲቩን መርሆዎች ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር አዲሱ የኢትዮጵያ የግዥና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ማስፈፀሚያ መመሪያ ሲዘጋጅ ግዥ ፈፃሚ አካላት ተፈላጊውን መረጃ ለሕዝቡ ግልጽ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ድንጋጌ በብሔራዊ የ"ኮስት" ባለድርሻ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አማካኝነት እንዲካተት መደረጉን በተመለከተ ገለፃ መደረጉ ታውቋል፡፡ በመጨረሻም ተሰብሳቢዎቹ ከስድስት ወራት በኋላ ስብሰባ የሚካሔድበትን ቦታ በመወሰን የኢኒሸቲቩ የሙከራ ጊዜ ካለቀ በኋላ የ#ኮስት; እንቅስቃሴ በምን መልክ ዘላቂነት ሊኖረው እንደሚችል ውይይት ማካሄዳቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን በእንግሊዝ የዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (DFID) የገንዘብ ድጋፍ እና በዓለም ባንክ ቴክኒካዊ ድጋፍ እ.ኤ.አ. ሜይ 2008 የተጀመረው የ#ኮስት; ኢኒሸቲቭ ከአፍሪካ አገራችንን ጨምሮ ማላዊን፣ ታንዛኒያንና ዛምቢያን፣ ከሌላው ዓለም ደግሞ እንግሊዝን ጨምሮ ቬትናምን፣ ፊሊፒንስን እና ጓቴማላን በሙከራ አባል አገርነት በማቀፍ ለሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ተግባራዊ በመሆን ላይ የሚገኝ ኢኒሸቲቭ ነው፡፡ |
|
|
የኮሚሽኑ
የዘጠኝ
ወር የዕቅድ
አፈፃፀም ሪፖርት ለም/ቤቱ
የሕግና አስተዳደር
ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ቀረበ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2002 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀረበ፡፡ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ አሊ ሱለይማን መ/ቤቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ፣ በስነምግባር ትምህርትና በኮሚኒኬሽን ጉዳዩች፣ በሙስና ወንጀል መካከል ፣የሙስና ወንጀል ተጠርማሪዎችን በመርመር፣ በመክሰስና ፍርድ በመስጠት እንዲሁም በበጀትና በሰው ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በዚህ መሰረት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ኮሚሽኑ ያካሄደው መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት የማጥራት ሥራ መጠናቀቁንና ጥናቱን ተከትሎ የኮሚሽኑ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሥራ ሂደትን መሰረት በደረገ መልክ መዋቀሩን ገልፀዋል፡፡ አዲሱን አሰራር ለመተግበር የሚያስችሉ መመሪያዎች፣ ቅጾች እና የቲም ቻርተር ተከታታይ ውይይት ተካሂዶባቸውና ማስተካከያ ተደርጎባቸው ሥራ ላይ መዋላቸውንም አመልክተዋል፡፡ አዲስ በተዘጋጀው የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት መሰረት ወደ ትግበራ ለመግባት ከታህሳስ ወር 2002 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ የሰራተኛ ምደባ ተካሂዶ የሙከራ ትግበራ ተግባራዊ ሲሆን መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡ ክቡር ኮሚሽነሩ የሥነምግባር ትምህርትን በማስፋፋትና በኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተም ከተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች፤ የብዙሃን ማህበራት፣ የሙያ ማህበራት እንዲሁም ከክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ለተውጣጡ 788 ያህል ሰልጣኞች በሥነምግባር፣ በሙስና መካከል እና በሙስና ወንጀል ሕጎች ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሱማሌና በጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 29 የተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ለተዉጣጡ 3348 ሰዎች በሥነምግባር እና በሙስና መከላከል ዙሪያ ትምህርት መሰጠቱን አስገንዝበዋል፡፡ “ሥነምግባር” በሚል ስያሜ የሚታወቀው የኮሚሽኑ ሶስት መጽሔቶች እያንዳንዳቸው በ9000 ቅጅ፤ ሁለት ፖስተሮች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ10000 ቅጅዎች ታትመው ለሕብረተሰቡ እንዲደርሱ መደረጋቸውም ተመልክቷል፡፡ የፌደራል የመንግስት መ/ቤቶችንና የልማት ድርጅቶችን አሰራር ግልፅነት ያለው፤ ተጠያቂነትን ያረጋገጠ እንዲሁም ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የማይከፍት መሆኑን ለማረጋገጥ ኮሚሽኑ ባደረገው እንቅስቃሴ 31 ተግባራትን መሰረት ያደረጉ የአሰራር ስርአት ጥናቶች ተጠናቀው ለየተቋማቱ መላካቸው ተጠቅሷል፡፡ በተመሳሳይም በአምስት ተግባራት ላይ ረቂቅ የጥናት ሪፖርት መዘጋጀቱንና በአራት ተግባራት ላይ ደግሞ መረጃ የማሰባሰብና የማጠናከር ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልèል፡፡ የሙስና ወንጀልን በማጋለጥ፤ በመመርመርና በመክሰስ ረገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በጠቅላላው 1714 ጥቆማዎች ወደኮሚሽኑ ቀርበው መመዝገባቸውንና ከነዚህ መካከል 894 ያህሉ በኮሚሽኑ የሥልጣን ከልል ስር የሚወድቁ መሆናቸው መለየቱን፤ ቀሪዎቹ 820 ደግሞ ከኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ውጪ መሆናቸው መለየቱ ተጠቅሷል፡፡ በሌላ በኩል በ418 የምርመራ መዝገቦች ላይ ምርመራ መካሔዱንና ከእነዚህ ውስጥ 180 የምርመራ መዝገቦች ለዐቃቤ ሕግ የተላኩ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ የሙስና ወንጀል ክስን በተመለከተም በተጠቀሰው ጊዜ በቢሮ ዐቃቤ ሕግ 900 የምርመራ መዝገቦች የነበሩ መሆኑንም በእነዚህ ላይ የተለያየ ውሳኔ መሰጠቱን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ በችሎት አቃቤ ሕግ አማካኝነት በ38 መዝገቦች የቅድመ ክስ መግለጫና በ29 መዝገቦች የቅድመ ክስ መቃወሚያ መቅረቡን አስረድተው፣ የቅድመ ክስ ዝግጅት ውሳኔ ያልተሰጠባቸው መዝገቦች ብዛት 15 መሆኑንና የመደበኛ ክስ ክርክር ብይን የተሰጠባቸው መዝገቦች ብዛት ደግሞ 121 መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አስገንዝበዋል፡፡ ኮሽነሩ አክለውም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከጥቅምት ወር 2002 ዓ.ም ጀምሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈት ኮሚሽኑ ያከናወናቸውን ተግባራት እንዲሁም የሥነምግባር አውታሮችን ለማጠናከር የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን በዝርዘር አቅርበዋል፡፡ ኮሚሽኑ ከሐምሌ 1 ቀን 2001 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በነበረው የዘጠኝ ወር ጊዜ ከመደበኛ በጀት 10.58 ሚሊዮን ብር፣ ከዲሞክራቲክ ተቋማት ፕሮግራም (DIP/UNDP) ከተመደበለት በጀት 5.3 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15.9 ሚሊዮን ብር ሥራ ላይ መዋሉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ሪፖርቱን አስመልክቶ ከቋሚ ኮሜቴ አባለት ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች በኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያና መልስ እንደተሰጠ ለመረዳት ተችሏል፡፡ |
|
|
የሀብት
ማሳወቂያና
ማስመዝገቢያ ረቂቅ
አዋጅ ፀደቀ አዋጁ ማንኛውም ተlሚ ፣ ተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ በራሱና በቤተሰቡ ባለቤትነት ወይም ይዞታ ስር የሚገኝ ሀብትን እንዲሁም የራሱንና የቤተሰቡን የገቢ ምንጮች የማሳወቅና የማስመዝገብ ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ኮሚሽኑ የተlሚዎችን፣ የተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞችን ሀብት በራሱ ለመመዝገብ ወይም የምዝገባውን ሥራ እንደ አስፈላጊነቱ በሙሉ ወይም በከፊል የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንደሚያከናውኑ ውክልና የመስጠት መብት የተሰጠው ከመሆኑም በላይ የምዝገባ ሰነዶች ጠባቂ ሆኖ እንዲያገለግልና ሀብታቸውን ላስመዘገቡ ዜጎቸ የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ በአዋጁ ሀላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ አራት ክፍሎችና 26 አንቀፆች ያሉት ይህ የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ በክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎችን፣ በክፍል ሁለት ሀብትን ስለማሳወቅና ስለማስመዝገብ ፣ በክፍል ሦስት የጥቅም ግጭትን ስለማሰወቅና ስለማስወገድ እንዲሁም በክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን ያከተቱ አንቀፆችን የያዘ ነው፡፡ በአዋጁ መሠረት ማንኛውም ተlሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለበት ከስድስት ወራት በኃላ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ሀብቱን ማሳወቅና ማስመዝገብ እንዳለበትና ከዚያም በኃላ በየሁለት ዓመቱ ሀብቱን የማሳወቅና የማስመዝገብ ግዴታ ተግባራዊ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ የአዋጁ መፅደቅ የመንግስት የሥራ ኃላፊነትና የግል ጥቅም ሳይቀላቀሉ በየራሳቸው የሚመሩበትን ግልፅ ሥርዓት በመዘርጋት ሊፈጠር የሚችለውን የጥቅም ግጭት ለማስወገድ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡ |
|
|
አዲስ
አበባ/ ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ/
የፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት
1ኛ ወንጀል ችሎት
መጋቢት 23 እና 29 ቀን 2002
ዓ.ም በዋለው ችሎት
በሙስና ወንጀል
የተከሰሱ ሁለት
ግለሰቦች ላይ
የስድስት ወር እና
የእንድ ዓመት
የእስራት ውሳኔ
አስተላለፈ፡፡ ግለሰቦቹ
በተለያዩ
የመንግስት
መስሪያቤቶች ውስጥ
ይሰሩ የነበሩና
ከሥራቸው ጋር
በተያያዘ ጉቦ
በመቀበልና
ንብረትን ወስዶ
በመሰወር የሙስና
ወንጀሎች ተከሰው
ለፍርድ የቀረቡ
ናቸው፡፡ የፌደራል
የሥነምግባር እና
የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ዐቃቤ ህግ ክስ
እንደሚያስረዳው
መለሰ ቱራ ደበላ
የተባለው ተከሳሽ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ
ከተማ የመሬት
አሰጣጥ ቁጥጥር
ኦፊሰር የነበረና
የሥራ ኃላፊነቱን
ተጠቅሞ ማድረግ
የማይገባውን
ለማድረግ በማሰብ
ጥቅምት 16 ቀን 2002 ዓ.ም ቤት
ገዝቶ ስም በማዛወር
ላይ የነበረን
ኢንስፔክተር
ሙሉጌታ ዳምጠው
የተባለ ግለሰብ
በዝቅተኛ የስም
ማዛወር ክፍያ ስም
አዛውርለሃለሁ
በማለት 800.00/ ስምንት
መቶ/ ብር ጉቦ
ሲቀበል እጅ ከፍንጅ
ተይዞ ክስ
የተመሰረተበት
ነው፡፡ በሌላ
በኩል ሞገስ ታመነ
ወርቁ የተባለው
ሌላኛው ተከሳሽ
የማይገባ ጥቅም
ለራሱ ለማግኘት
አስቦ የመንግስት
ንብረት የሆነና
ከአዲስ አበባ
የመንገድ
ትራንስፖርት
ባለስልጣን መ/ቤት
ለጥበቃ
የተረከበውን ክላሽ
ጠመንጃ ከአንድ
ካርታና ከ24 መሰል
ጥይቶቹ ጋር ደብቆ
ለመሰወር ሲሞክር
በ16/07/2002 ዓ.ም በፖሊስ
ተይዞ በኮሚሽኑ
ዐቃቤ ህግ ክስ
ሊመሰረትበት
ችሏል፡፡ ተከሳሾቹም የተመሰረተባቸውን ክስ አምነው በመቀበላቸው ፍርድ ቤቱ አቶ መለሰ ቱራ ደበላ የተበለውን ተከሳሽ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲወስን አቶ ሞገስ ታመነ ወርቁ የተባለው ሌለኛውን ተከሳሽ ደግሞ በስድስት ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ |
|
|
በከባድ
የእምነት ማጉደል
የሙስና ወንጀል
የተከሰሰችው
ተፈረደባት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቢ ሕግ የመሰረተው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽዋ በእምግሬሽን እና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ውስጥ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ ሆና በምትሰራበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሷ ለማግኘት በማሰብ በተላያየ ጊዜ ከሰበሰበችው ብር 1,351,380 ውስጥ የገቢ ደረሰኞቸን በማለዋወጥ እና ቁጥራቸውን በማዛባት ብር 117,180 በማጉደሏ እንዲሁም 671 የሚሆኑ እና ብር 194,240 የሚገመት ደረሰኞችን ለመምሪያ የሂሳብ ክፍል ሳተስተላልፍ ደብቃ በማስቀረት በድምሩ ብር 311,420 ለግል ጥቅሟ በማዋል በመፈጸመችው ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ተከሳለች፡፡ በሌላ በኩል በቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 11 የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዋ/መምሪያ አባል እና በጥበቃ ሥራ ላይ ተመድቦ ይሰራ የነበረው ኮ/ል ዑመር አሊ ዩሱፍ የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ለመንግስት ሥራ ማከናወኛ የተረከበውን ትጥቅ አንድ ኮፍ ሰደፍ ክላሽ ጠመንጃ ፣ አምስት የጥይት ካዝና እና አንድ መቶ ሃምሳ ጥይት ወደ አዋሽ ሚሌ በመሄድ ማንነቱ ላልታወቀ ግለሰብ በብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ሽጦ ለግል ጥቅም በማዋል በፈፀመው በሥራ ተግባር ላይ የሚፈፀም የመውሰድ እና የመሰወር የሙስና ውንጀል ተከሶ በአንድ አመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረበባቸውን የሰው አና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ከላይ የተጠቀሰው ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡ |
|
|
የሙስና
ወንጀል የፈፀሙ
በእስራትና
በገንዘብ ተቀጡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቢ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የመሰረተው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ወ/ሮ አልማዝ ኪዳኔ ግደይ በቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር መምሪያ ማህደር አጣሪ ፣ ወ/ሮ ማህሌት አምሳሉ ደርሰህ የክፍለ ከተማው የንድፍ ሰራተኛ ፣ ገረማው ተስፋዬ መኩሪያ በቦሌ ክ/ከተማ የቀበሌ 14/15 የነዋሪዎች አገልግሎት ኃላፊ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት በሥልጣናቸው ያለአግባብ በመገልገል በግል ሥራቸው ከሚተዳደሩ አቶ ሀድራ ሀቢብ በክሪ እና የአልምብርሃን ተስፋዩ አለሙ ጋር በመመሳጠር በሀሰት በተዘጋጀ ካርታ መሬቱን በማስወሰድ ሌሎች እንዲጠቀሙ በማድረጋቸውና በመጠቀማቸው እንዲሁም ግለሰቦቹም ያለአግባብ በመጠቀማቸው በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል ወ/ሮ አልማዝ ኪዳኔ የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት አስተዳደር መምሪያ ማህደር አጣሪ ሆና በምትሰራበት ወቅት ለአቶ ያአለምብርሃን ተስፋይ ህገወጥ የስም ዝውውር በመፈፀም ፣ ወ/ሮ ማህሌት አምሳሉ ደርሰህ ደግሞ የተጭበረበረ ካርታ መሠረት በማድረግ የተሣሰተ የልኬት ሪፖርት በማቅረብ ፣አቶ ገረመው ተስፋዬ በበኩሉ ያለአግባብ የነዋሪነት መታወቂያ በመስጥት እና ግለሰቡ በህገወጥ መንገድ በአቶ ሀድራ ሀቢብ እንዲከወከል ሁኔታዎችን በማመቻቸት ለወንጀሉ መፈፀም ተባበሪ ሆነዋል፡፡ አቶ ያአለምብርሃን ተስፋዬ ደግሞ በሀሰተኛ ሰነድ የተዘጋጀን ካርታ በተወካዩ አቶ ሀድሪ ሀቢብ አማካይነት 40 ሺህ ብር በመሸጥ ህገወጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የዐቃቤ ሕግ ክስ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ ዐቃቢ ሕግ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻለቸው ፍ/ቤቱ መጋቢት 7 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት የአለለምብርሃን ተስፋዬ በ 4 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 6,000 ፣ አቶ ሀቢብ ሀድሪ በ 3 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 5,000 ፣ ወ/ሮ ማህሌት አምሳሉ በ3 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 1,000 ፣አቶ ገረመው ተስፋዬ በአንድ ዓመት እሥራትና በብር 300 እንዲሁም ወ/ሮ አልማዝ ኪዳኔ በአንድ ዓመት እሥራትና በብር 500 እነዲቀጡ ወስኗል፡፡ |
|
|
በእምነት
ማጉዳል የሙስና
ወንጀል የተከሳሱ በእሥራት
ተቀጡ አዲስ አበባ(ፌ.ሥ.ፀ.ኮ.) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 18 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሳሱ ሶስት ግለሰቦች ላይ በእሥረት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የፌደራል
የስነ-ምግባር እና
ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ዐቃቤ ሕግ ክስ
የሚያስረደው፤
ተከሣሾቹ፡- 1ኛ)
ኮን/ል ተሥፋዬ
ማንዴ መንገሻ፤ 2ኛ)
ታዬ ሀጠዩ ደረጀ፤
3ኛ) ልደቱ አበበ
ወ/ሰማያት በፈጸሙት
የሙስና ወንጀል
የተከሳሱ
ማሆናቸውን ሲሆን 1ኛ
ተከሣሽ ፖሊሰ
የነበረና ለክትትል
ሥራ የተረከበውን
ሽጉጥ ከአምስት
ጥይት ጋር በ2ኛ
ተከሣሽ አገናኝነት
ለ3ኛ ተከሣሽ በብር 7000
(ሰባት ሺህ ብር) ሽጦ በመሰወሩ፤
በዚህ ድርጊት 2ኛ
ተከሣሽ ብር 300(ሦስት
መቶ ብር) ጥቅም
በማግኘት፤ 3ኛ
ተከሣሽም ሽጉጡ
የመንግስት መሆኑን
እያወቀ ለሌለው
ግለሰብ በብር 8500
(ስምንት ሺህ
አምስት መቶ ብር)
ሽጫለሁኝ በማለት
በፈፃሙት እምነት
ማጉደል የሙስና
ወንጀል የተከሳሱ
ናቸው፡፡ የፌደራል
ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ
ወንጀል ችሎት ሦስቱ
ተከሣሶች ላይ
በኮሚሽኑ
የቀረበባቸውን
ማስረጃ መከላከል
ባለመቻለቸውና
ድርጊታቸውን
አምነው ጥፈተኞች
ነን በማለታቸው፤
የወንጀሉን
አፈፃፀምና የቅጣት
አስተያየቱን
በማገናዘብ 1ኛ
ተከሣሽ በአንድ
ዓመት እስራት፤ 2ኛ
እና 3ኛ ተከሣሾች
እያንዳንደቸውን በ6
ወር (ስድስት ወር)
እስራት እንዲቀጡ
ወሰኗል፡፡
በዚህ የእምነት ማጉዳል የሙስና ወንጀል የተሸጠ ሽጉጥም በህብረተሱ ጥቆማና ክትትል የተገኘ መሆኑን የዐቃቤ ህግ የክስ ምርመራ ያስራዳል፡፡ |
|
|
ሁለት መቶ ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ አዲስ አበባ(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመንግስት የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል መጋቢት 3 ቀን 2002 ዓ.ም ከሕጋዊ አስመጭ ነጋዴዎች ብር 200,000 ሲቀበሉ የደረሰባቸውን ሁለት የአዲስ አበባ ኤርፖርቶች ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል 1ኛ በኢትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ኤርፖርቶች ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፍተሻ ጀማሪ ኦፊሰር የሆነው ግለሰብ በመንግስት የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት ወደጎን በመተው ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት ህጋዊ ነጋዴዎቹ በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቧቸውን የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ትክክለኛ እና ህጋዊ መሆናቸውን እያወቀ ትክክለኛነታቻውን በመቃወም ነጋዴዎቹ ብር 300,000 ጉቦ እንዲከፍሉት ጠይቋል፡፡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጉምሩክ አስተላላፊ የሆነው ሁለተኛው ግለሰብ ደግሞ ነጋዴዎቹ የተጠየቁትን ገንዘብ እንዲከፍሉ በማደራደር እና በመስማማት ከጠየቀው ገንዘብ ውስጥ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እነዲከፍሏቸው ስምምነት ላይ በተደረሰው መሠረት ሁለቱም ግለሰቦች ብሩን በቼክ እና በጥሬ ብር ሲቀበሉ በኮሚሽኑ የምርመራ ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ ሊያዙ ችሎዋል፡፡ በሌላ በኩል የካቲት 27 ቀን 2002 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ባንክ ኦፊሰር የሆኑት ሁለት ግለሰቦች መንግስት የሰጣቸውን የሥራ ኃለፊነት ያለአግባብ በመገልገል ከልደታ ክፍለ ከተማ የልማት ተነሽ ከሆኑት አንድ ባለጉዳይ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) ሲቀበሉ በኮሚሽኑ የክትትል ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ ግለሰቦቹ ሊያዙ የቻሉት ከልደታ ክ/ከተማ በልማት ምክንያት ተነስተው በዕጣቸው መሰረት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ካሳ እንዲፈፀምላቸው በጠየቁበት ወቅት መንግስት ካስቀመጠው አሰራር ውጭ ህገ-ወጥ ጥቅም ለማግኘት ብለው ባለጉዳዩ ግለሰብ ብር 30,000 እንዲከፍላቸውና ለዚህም የተሸላ መሬት እደሚሰጡአቸው ቃል ገብተው ብር 25,000 ሲቀበሉ ስለተደረሰባቸው ነው፡፡ በመንግስት የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል በማስፈራራት እና በማታለል ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት የሚሞክሩ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ አሳልፎ በመስጠት ኮኮሚሽኑ ጎን ሆኖ እንዲታገላቸው ኮሚሽኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ |
|
|
በግብረአበርነት የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ተፈረደባቸው (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) አዲስ አበባ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 2 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በስልጣን ያለአግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል የፈፀሙት ገነት ማሞ ተምትሜ እና ዓለም ይትባረክ ወ/ማሪያም ከ 3 ዓመት እስከ 17 ዓመት በሚደርስ ፅኑ አሥራትና ከ 1 ሺህ እስከ 16 ሺህ በሚደርስ ገንዘብ እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቢ ሕግ ክስ እንደሚያስረደው ገነት ማሞ ተምትሜ የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሊዝ ክትትል ቡድን መሪ ፣ ዓለም ይትባረክ ገ/ማሪያም ደግሞ የክፍለ ከተማው ማህበራት ማደራጃ ተወካይ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት አስበው “ እሸት ፍሬ ቁጥር 2 ” ተብሎ የሚጠራ ህገ-ወጥ የጋራ የመኖሪያ ቤት ሕንፃ ህብረት ሥራ ማህበር በማቋቋም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሊዩ ስሙ ቤቴል ተብሎ በሚጠራ አከባቢ የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ያወጣውን የጋራ መኖሪያ ህንፃ ሕብረት ሥራ ማህበር መመሪያን በመጣስ ስፋቱ 864 ካሬ ሜትር የሚሆን ቦታ ማንነታቸው በግልፅ ላልታወቁ ግለሰቦች በሊዝ፣ በካርታ ቁጥር ሊዝ/ዕጣ/240/19188/00 አዘጋጅተው መስጠታቸው በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ገነት ማሞ ተምትሜ በ 17 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 16,000( አሥራ ስድስት ሺህ ብር) ፣ ዓለም ይትባረክ ደግሞ በ 3 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 1,000 (አንድ ሺህ) እንዲቀጡ ፍ/ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ |
|
|
የ
#ኮስት;
ባለድርሻ አካላት
የምክክር
አውደ-ጥናት ተካሄደ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በግዥ፣ በጨረታ አካሄድ፣ በውል አፈጻጸም፣ በዲዛይን አዘጋጃጀትና በመሳሰሉት ተግባራት ውስጥ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትንና ውጤታማነትን በማረጋገጥ ሙስናን ለመከላከል የሚንቀሳቀሰውና /Construction Sector Transparency Initiative (CoST)/ #ኮስት; በሚል ስያሜ የሚታወቀው ኢንሸቲቭ የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ-ጥናት የካቲት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል ተካሔደ፡፡ የምክክር አውደ-ጥናቱ ዓላማ በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ስለኢኒሽቲቩ ዓላማዎችና ተግባራት እንዲሁም በዘርፉ የሚፈፀም ሙስናን ለመከላከል መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ለተሳታፊዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው፡፡ የምክክር አውደ-ጥናቱን በንግግር የከፈቱት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እና በኢትዮጵያ የ#ኮስት; ሻምፕዮን ክቡር አቶ አሊ ሱለይማን እንደገለፁት የኮንስትራክሽን ዘርፉ በዓለም-ቀፍ ደረጃ ሰፊ የገንዘብ መጠን የሚንቀሳቀስበት ከመሆኑ አንፃር ከሌሎች ዘርፎች በላቀ ሁኔታ ለግዙፍ የሙስና ወንጀሎች የተጋለጠ መሆኑን ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩ አስገንዝበዋል፡፡ ደካማ አመራርና ግልፅነት የጎደለው አሰራር ዘርፉን ይበልጥ ለሙስናና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ እንደሚያደርገው የጠቆሙት ክቡር ኮሚሽነሩ፣ በሁሉም የግንባታ ፕሮጀክቶች የቀረፃ፣ የአፈፃፀምና የግምገማ ደረጃዎች የሚፈፀም ሙስና አላስፈላጊና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የማይገቡ፣ በስህተቶች የተሞሉ እንዲሁም አደገኛ የሆኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲቀረፁ በር የሚከፍት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ኢኒሸቲቩ እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ለመቅረፍና ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል ይቻል ዘንድ በመንግሥታት የሚካሄዱ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ባለድርሻ አካላትና በአጠቃላይ ህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸትን እንደ ዋነኛ አማራጭ የሚወስድ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ ፊሊፒንስ፣ ቬትናም፣ እንግሊዝ፣ ማላዊና ኢትዮጵያን በአባልነት የያዘው “ኮስት” ይህን አስቀድሞ የመከላከል ዓላማ ለማሳካት የመንግስት ግንባታና የመሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የታቀዱ ተግባራትንና የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም ህብረተሰቡ በዕቅዱ መሠረት የሚገመግምበትን ሁኔታ ማመቻቸትን እንደ አንድ የትኩረት አቅጣጫ የሚከተል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ክቡር ኮሚሽነሩ አክለውም መንግስት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለውን የሙስና መከላከል ሥራ በራሱ የተናጠል ጥረቶች ብቻ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ አከናውናለሁ የሚል እምነት እንደሌለው ገልፀው፣ ይህን ግዙፍ ተግባር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግና እንደሚገባ በጽናት እንደሚያምን ገልፀዋል፡፡ በምክክር አውደ-ጥናቱ ላይ የብሔራዊ ባለድርሻዎች ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ ተስፋዬ ያለው እና የብሔራዊ #ኮስት; ጽህፈት ቤት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ሐጎስ አብዲ አማካኝነት ጥናታዊ ጸሑፎች ቀርበው በተሳታፊዎቹ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ |
|
|
የሙስና ወንጀል የፈፀመው ተፈረደበት አዲስ አበባ(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 17 ቀን 2002 በዋለው ችሎት ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ፈፅሞ በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተከሶ የነበረው ታምራት ብርሃኑ በ 5 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 5,000 እንዲቀጠ ወሰነ፡፡ ፍ/ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ተከሳሹ ከ1997 እሰከ 1999 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ በላስልጣን ገንዘብ ሰብሳቢ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ በጉለሌ እና በጉርድሾላ ቅርንጫፎች በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ደረሰኝ ቁጥሮች ከሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ በድምሩ ብር 49,841.30 (ብር አርባ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ 30/100) የመንግስት ገንዘብ አጉድሎ በመገኘቱ በፈፀመው ከባድ የእምነት መጉደል የሙስና ወንጀል በመከሰሱ ነው፡፡ በመሆኑም ተከሳሹ በኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻሉ ከላይ የተጠቀሰው ቅጣት ተወስኖበታል፡፡ |
|
|
208 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመንግስት መሬት ያለአግባብ የወሰዱ ተፈረደባቸው አዲስ አበባ(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ)የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ መሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ግምቱ ብር 208 ሚሊዮን የሚገመት 120 ሺህ ካ.ሜ የከተማ ቦታ በመውሰድና በማስወሰድ ከከሰሳሳቸው 13 ተከሳሾች መካከል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ስምንቱ ተከሳሾች ከ7 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ 3 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው የመንግስት ሠራተኛ ከነበሩት ተከሳሾች 1ኛ ተከሳሽ ሙለሜ ረሽድ ሲራጅ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን የይዞታና መረጃ መምሪያ ሃላፊ፣ 2ኛ ተከሳሽ ለማ ደግፌ አባይነህ የኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ፣3ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ደሃብ ገ/ህይወት ብሩ በየካ ክ/ከተማ ማህበራት ማስፋፊያ ቡድን መሪ ፣ 6ኛ ተከሳሽ ሚፍታህ አብዱ የሱፍ በሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ቡድን መሪ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች በንግድ እና በድላላ ሥራ ለተሰማሩትና በቅደም ተከተል 9ኛ፣ 10ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ለሆኑት ቆንጂት ደስታ መኩሪያ፣ መኮንን ወለላው ካሣ፣ ዮሴፍ ጌትነት አበበ እና ሠለሞን ግርማ ማህተሙ ማስገኘት አስበው እንዲሁም በግል ሥራ የተሰማሩት ተከሳሾችም የመንግስትን ጥቅም ለመጉዳትና የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት አስበው በወንጀሉ በሙሉ ፍላጎታቸው በመሳተፍ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ በዚህ መሠረት ሙለሜ ረሽድ ሲራጅ ፣ለማ ደግፌ አባይነህ፣ ወ/ሮ ደሃብ ገ/ህይወት ብሩ እና ሚፍታህ አብዱ የሱፍ በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሆህተ ምሥራቅ፣ ታዳጊ ተክል፣ ገነት በር እና አዋሽ 85 የሚባሉትን ነባር የመኖሪያ ቤት ሥራ ማህበራት ፋይሎች ያለአግባብ የተለያዩ ጥቅሞችን በመቀበል በግል ሥራቸው ለሚተዳደሩ ዮሴፍ ጌትነት እና ሠለሞን ግርማ አሳልፈው በመስጠትና በማህበራቱ ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶች ተደራጅተው ወደ ፋይሉ እንዲመለሱ በማድረግ እንዲሁም ህጋዊ እንዲሆኑና በህጋዊ መንገድ እንዲስተናገዱ የተለያዩ ደብዳቤዎችን በመፃፃፍ ህገወጥ የሆነ ሽፋንና እገዛ ሰጥተዋል፡፡ ዮሴፍ ጌትነት እና ሰለሞን ግርማ ከ10ኛ ተከሳሽ መኮንን ወለላው ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብለው የአዋሽ 85 እና ገነት በር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ፋይሎች በመሸጥ፣ መኮንን ወለላው ደግሞ በዚህ መልክ ያገኛቸውን የሁለቱን ነባር ማህበራት ፋይሎች ያለአግባብ በማስወጣት፣በማህበራቱ ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሠነዶች ተደራጅተው ተመልሰው እንዲገቡና ወደሌላ ክ/ከተማ እንዲላኩለት በማድረግ በአዋሽ 85 ማህበር ስም ብር 33,283,776 (ብር ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ብር) የሚገመት 19,200 ካ.ሜ ፣ በገነት ማህበር ስም ደግሞ ብር 77,662,144 (ሰባ ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስድሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር) ግምት ያለው 44,800 ካ.ሜ የመንግስት መሬት በህገወጥ ማህበር ስም ያለአግባብ በመያዝ ለግል ጥቅሙ አውሏል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ግለሰቦች የመንግስት ሰራተኞች ከነበሩት ተከሳሾች የተቀበሉትን የሆህተ ምሥራቅ እና ታዳጊ ተክል የመኖሪያ ቤት ሥራ ማህበራት ፋይሎች ለ9ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ቆንጂት ደስታ በከፍተኛ ገንዘብ በመሸጥ፣እሷም በዚህ መልክ ያገኘችውን ሰነድ የመንግስት ሠራተኞችን በገንዘብ በመደለል ለህገወጥ ማህበራት ቦታ እንዲመቻችላት በማድረግ በሆህተ ምሥራቅ ማህበር ስም ብር 41,604,720(አርባ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ብር) ግምት ያለው 32,000 ካ.ሜ ፣ በታደጊ ተክል ማህበር ስም ደግሞ ብር 55,472,960 (ብር አምሣ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ) ግምት ያለው 24,000 ካ.ሜ የመንግስት መሬት ያለአግባብ በመውሰድ ለግል ጥቅሟ አውላለች፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻለቸው ፍ/ቤቱ የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ የነበረውን ሙላሜ ረሽድ ሲራጅ በሰባት ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 5,000፣ 2ኛ ተከሳሽ ለማ ደግፌ አባይነህ እና 3ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዳሃብ ገ/ህይወት እያንዳንዳቸው በ 8 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 6,000፣ 6ኛ ተከሳሽ ሚፍታህ አብዱ የሱፍ በ 7 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 3,000፣ 9ኛ ተከሳሽ ቆንጅት ደስታ በሁለት የተለያዩ ክሶች በ 8 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 20,000፣ 10ኛ ተከሳሽ መኮንን ወለላው ካሣ በሁለት የተለያዩ ክሶች በ 9 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 15,000፣ 11ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ዮሴፍ ጌትነት እና ሰለሞን ግርማ እያንዳንዳቸው በሁለት የተለያዩ ክሶች በ 10 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 6,000 እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡ |
|
|
የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ተፈረደባቸው አዲስ አበባ (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ)፡- የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸውን ተሞገስ ወልደመላክ በ 8 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 5ዐ,ዐዐዐ.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ነጋሽ ሰማን እና አንዋር ጀማልን ደግሞ እያንዳንዳቸው በ7 ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 4,ዐዐዐ.00 (አራት ሺህ ብር) እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚስረዳው 1ኛ ተከሳሽ ተሞገስ ወልደመላክ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ቡድን መሪ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት በግል ሥራ ከሚተዳደሩት ከነጋሽ ሰማንና ከአንዋር ጀማል ጋር በመመሣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የህብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀት እና አፈፃፀም መመሪያን በሚቃረን መልኩ አንደኛው ተከሳሽ ታህቢብ ቁጥር 2/13 በሚል ስያሜ በህገወጥ መንገድ በሁለቱ ግለሰቦች የተመሠረተው ማህበር ለህጋዊነት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ያላሟላ መሆኑን እያወቀ የማህበሩን የአባላት ዝርዝር የያዘ ቅፅ አፅድቆ ከሌሎች ህጋዊ ማህበራት ጋር እንዲካተት በማድረግ ለክፍለ ከተማው የመሬት አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ በህገወጥ መንገድ የተደራጀውን ማህበር በህጋዊ መንገድ እንደተደራጀ አድርጐ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይም ነጋሽ ሰማንና አንዋር ጀማል ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት አስበው የማህበሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊ/መንበር በመሆን ማህበሩ በአግባቡ ለመደራጀት የሚያበቃውን መስፈርት ሳያሟሉ በሕገወጥ መንገድ በማደራጀት ስፋቱ 1135.68 ካሬ ሜትር የሆነውን የመንግሥት ቦታ በቁጥር ሊዝ/ዕጣ/237/18829/ዐዐ፣ በ2/13/97 ዓ.ም በተዘጋጀ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አማካኝነት ወስደዋል፡፡ በዚህም ሁሉም ተከሳሾች መንግሥት በወቅቱ በነበረው የሊዝ መሸጫ ዋጋ ከቦታው ማግኘት የሚገባውን ብር 1,835,258.88 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሠላሣ አስምት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከሰማንያ ስምንት ሣንቲም) እንዲያጣ በማድረግ በመንግሥት ላይ ከፍ ያለ ጉዳት በማድረሳቸው፣ በመላ ሀሳባቸውና አድራጎታቸውም በሚያስከትለው ውጤት ተስማምተው አውቀውና ፈቅደው በግብረ አበርነት በፈፀሙት የስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰው ጥፋተኝነታቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ከላይ የተጠቀሰውን ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለመከላከል ባለመቻላቸው ጐሹ አንዱአለም ልመንህ በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ (ሃያ ሺህ ብር)፤ ባለቤቱ አስቴር አዘዘ ኃይሌ ደግሞ በ5 ዓመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጡ ዛሬ የካቲት 11/2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
የሙስና
ወንጀል የፈፀሙ
በእስራትና
በገንዘብ እንዲቀጡ
ተወሰነ አዲስ አበባ /ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ/ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የሂሣብ ሠራተኛ እና የሂሣብ ክፍል ኃላፊ ተወካይ የነበረውን ጐሹ አንዱአለም ልመንህን እና ባለቤቱን ወ/ሮ አስቴር አዘዘ ኃይሉን ከ 5 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ጐሹ አንዱዓለም በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከጳጉሜ 1 ቀን 1997 ዓ.ም እስከ ጥር 3ዐ ቀን 1998 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የሂሣብ ሠራተኛ እና የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ተወካይ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት ከትዳር ጓደኛው ጋር በመመሳጠር በተጭበረበረ መንገድ ብር 549,6ዐ9.92 (አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሁለት ሣንቲም) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ ወጪ አድርገው ወስደዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ጐሹ አንዱአለም እምነት ተጥሎበት በተመደበበት ሥራ ሲያገለግል በነበረበት ወቅት የፍርድ ባለመብት በነበሩት አቶ ቅጣው መሸሻ እና በፍርድ ባለዕዳዋ ወ/ሮ አልማዝ አየለ መካከል በነበረው የፍርድ አፈፃፀም ክርክር ጉዳይ መነሻነት የፍርድ ባለዕዳ ንብረት ተሽጦ ተራፊው ብር 544,977.52 (አምስት መቶ አርባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ብር ከሃምሣ ሁለት ሣንቲም) ለባለዕዳው እንዲመለስላቸው በፍርድ ቤት በተወሰነው መሠረት የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ አየለ የተጠቀሰውን ገንዘብ መጠን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መውሰዳቸውን እያወቀ ለትዳር ጓደኛው የባንክ ሂሳብ ቁጥር በመክፈት እና ለፍርድ ባለዕዳ ግለሰብ የሚከፈል በማስመሰል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፅፎ ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ኃላፊውን አሳስቶ ካስፈረመ በኋላ ከላይ የተጠቀሰው ብር መጠን በተዘጋጀው ቼክ ከፍርድ አፈፃፀም መምሪያ አካውንት ወጪ እንዲደረግ ለባንኩ በማቅረብና ገንዘቡ ወደኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ እንዲተላለፍ በማድረግ በሁለተኛዋ ተከሳሽ በአስቴር አዘዘ ኃይሉ አማካኝነት ገንዘቡ ወጪ ተደርጎ ሁለቱ ተከሳሾች ለግል ጥቅማቸው አውለውታል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለመከላከል ባለመቻላቸው ጐሹ አንዱአለም ልመንህ በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 2ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ (ሃያ ሺህ ብር)፤ ባለቤቱ አስቴር አዘዘ ኃይሌ ደግሞ በ5 ዓመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጡ ዛሬ የካቲት 11/2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ |
|
|
የሙስና
ወንጀል የፈፀሙ
ስድስት ግለሰቦች
ተፈረደባቸው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ክሮፓ ገ/ሊባኖስ ገ/መድህን በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት በፀሓፊነት፣ አበበች ተረፈ ከበደ እና መስፍን አስፋው ገብረየስ ደግሞ የክብር መዝገብ ምዝገባ ሠራተኞች ሆነው በሚሰሩበት ወቅት በተለያዩ ግዜያት ከአሰራር ውጭ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍች፣ የሞት የመሳሰሉትን ሠርቲፊኬቶች በግረአበሮቻቸው በሚቀርቡላቸው ስማቸው በማይታወቅ ግለሰቦች በመስራትና በማውጣት ለራሰቸውና ለግረአባሮቻቸው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡ ግብረአበር የሆኑት ሠለሞን እድሪስ አህመድ ፣ብርሃኑ አድማሱ ተገኝ እና ቸሩ መንገሻ ካሣ ደግሞ በዚህ መልክ ያገኟቸው የነበሩትን ሠርቲፊኬቶች የተለያየ ጥቅሞች በመቀበል ለጊዜው ላልታወቁ ግለሰቦች በከፋፈል በፈፀሙት ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በኮሚሽኑ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ፍ/ቤቱ አበበች ተፈራ እና መስፍን አሰፋ እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 500.00 (አምስት መቶ)፣ ሠለሞን እድሪስ፣ ብርሃኑ አድማሱ እና ቸሩ መንሻ እያንዳንዳቸው በሁለት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 600.00 (ብር ስድስት መቶ) እንዲሁም ክሮፓ ገብረሊባኖስ በሦስት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 300.00 እንዲቀጡ ወሰነባቸው፡፡ |
|
|
በስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል የተከሰሱ ተፈረደባቸው አዲስ አበባ(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 1 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት እራሳቸውን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የፖሊስ አባላት በማስመሰል ከአንድ ግለሰብ ብር 30,000.00(ብር ሰላሣ ሺህ) ለመቀበል ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት የፖሊስ አባላትና ሁለት ደላሎች እያንዳንዳቸው በሰባት ዓመት ፅኑ እሥራትና በብር 200.00(ብርሁለት መቶ )እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው 1ኛ ተከሳሽ ረዳት ሣጅን አየለ ከበደ ደሴ የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ፣ 2ኛ ተከሳሽ ረዳት ሳጅን ባንታየሁ ታደሰ ሰማው ደግሞ የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት የሙያ ሥነምግባራቸው ከሚጠይቀው ውጭ በደላላነት ከተሰማሩ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በቅደም ተከተል ፈይዱ ጀማል አወል እና ፀጋዬ ጅማ አጋ ጋር በመሆን የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና በግለሰብ ላይ ጉዳት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ረ/ሳጅን አየለ ከበደ የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሽጉጥ እና ካቴና በመያዝ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን ከአንድ ግለሰብ ቤት ድረስ በመግባት እኛ ፖሊሶች ነን የፍርድ ቤተ መያዣ ተዕዛዝ አለን በማለት ይዘቱ ያልታወቀ ወረቀት በማሳየትና በሽጉጥ በማስፈራራት በካቴና እጁን አስረው በመኪና ከወሰዱ ቦኃላ እኛ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፖሊሶች ነን በመሬት ጉዳይ ላይ በሙስና ስለምትፈለግ ወስደን እንዳናስርህ ከፈለክ ብር 30,000.00(ብር ሠላሳ ሺህ) አምጣ ብለው በሃይል በማስገደድ የብሩን መምጣት በመጠባበቅ ላይ እያሉ እጅ ክፍንጅ በመያዘቸው ተከ |