ክፍል አንድ

ጠቅላላ

ክፍል ሁለት

ስለዋስትናና የፍርድ ቤት ስልጣን  

ክፍል ሶስት

ስለእግድ  

ንኡስ ክፍል አንድ

የንብረት ጠባቂ ስለመሾም

ንኡስ ክፍል ሁለት

ስለማሸግና የሀብት ዝርዝር ስለማዘጋጀት  

ክፍል አራት

ስለንብረት አወራረስ ሥነሥርአት

ክፍል አምስት

ቅድመክስ ዝግጅት

ክፍል ሰባት

የሙስና ድርጊትን ስለሚጠቁሙ ሰዎች ጥበቃ

ክፍል ስምንት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

አዋጅ ቁ 434/1997  

የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነሥርአት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ

የሙስና ወንጀል ትርጉምን፣ የክስ ሂደትና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ከወንጀል ህጉ ጋር በተጣጣመ መልኩ ማሻሻልና መደንገግ በማስፈለጉ፣

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ወይም የተከሰሱ ሰዎች በዋስትና ስለሚለቀቁበት ሁኔታ ዝርዝር ድንጋጌ መደንገግ በማስፈለጉ፣

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን ንብረት ስለማገድ፣ ስለማስተዳደርና ስለመውረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ማሻሻል በማስፈለጉ፣  

የጸረ ሙስና ልዩ ስነስርአትና የማስረጃ ህግ ድንጋጌዎችን ከሌሎች ህጎች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ማስተካከልና ማሻሻል በማስፈለጉ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 55/1 መሰረት የሚከተለው ታውጆአል፡፡

 

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1.                 አጭር ርእስ

ይህ አዋጅ <<የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁ 434/1997 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2.                 ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፣

1.    <<የሙስና ወንጀል>>ማለት በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ የተመለከቱት የሙስና ወንጀሎች ናቸው፡፡

2.    <<በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት>> ማለት በተከሳሽ ባለቤትነት ወይም ይዞታ ስር የሚገኝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሲሆን ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ከተከሳሹ በስጦታ የተሰጠ በአደራ የተቀመጠ እና የተሸሸገ፣ ማናቸውም በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ይጨምራል፡፡

3.   <<አግባብ ያለው አካል>>ማለት የሙስና ወንጀልን ለመመርመር እና/ ወይም ለመክሰስ ሥልጣን የተሰጠው አካል ነው፡፡

4.    <<የእግድ ትእዛዝ>> ማለት ተከሳሽ በንብረቱ ላይ ያለውን መብት እንዳይጠቀምበት የሚከለክል ትእዛዝ ሲሆን በማናቸውም መንገድ ለሌላ ሰው ማስተላለፍን፣ የመጠቀም መብት መስጠትንና ማስወገድን ይጨምራል፡፡

         5<<ሰው>>ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ    የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡

3.                 የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ አዋጅ በፌዴራልና በክልል ሥልጣን ስር በሚወድቁ የሙስና ወንጀሎች የምርመራና የክስ ሂደት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡  

ክፍል ሁለት

ስለዋስትና የፍርድ ቤት ስልጣን

4.                 በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ስለተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት

1.      በሙስና ወንጀል የተያዘ ሰው በዋስ እንዲለቀቅ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡ ሆኖም የተከሰሰበት ወንጀል ከአስር አመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል ከሆነ በዋስትና መልቀቅ አይቻልም፡፡

2.      በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰውን መርማሪው ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች የዋስትና ወረቀት በማስፈረም ወይም መያዣ በማስያዝ ሊለቀው ይችላል፤

h.      ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ለመፈጸሙ የሚያጠራጥር ከሆነ፣ ወይም

l.     የተያዘው ሰው ወንጀሉን ለመፈጸሙ የሚያጠራጥር ከሆነ፣ ወይም

. ተፈጸመ የተባለው ወንጀል በጽኑ እስራት የማያስቀጣ ከሆነ

3.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በዋስትና ወረቀት ያልተለቀቀ ተከሳሽ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ፍርድ ቤትን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

4.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በተከሳሹ ወይም በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት በተጠርጣሪው የሚቀርበውን በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ጥያቄን ፍርድ ቤቱ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች መፍቀድ አይችልም፡፡   

. ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ በዋስትና ቢለቀቅ ይጠፋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ወይም፣

. ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ በዋስትና ቢለቀቅ ማስረጃዎችን ያጠፋል ወይም ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ተብሎ ሲገመት፣

5.                 የዋስትና መብትን በማክበር ወይም በመከልከል በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ ይግባኝ

1.      በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ፍርድ ቤት ዋስትናን በሚመለከት በሚሰጠው ትእዛዝ ላይ ይግባኝ ማቅረብ ይቻላል፡፡

2.      ይግባኙ የቀረበው በዋስትና መለቀቁን ወይም የዋስትና ገንዘብ መጠኑን በመቃወም ከሆነ ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ እስኪወሰን ድረስ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔው ሳይፈጸም ይቆያል፡፡

3. ፍርድ ቤቱ በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው ወይም የተከሰሰው ሰው በዋስትና እንዲለቀቅ የወሰነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ መጠየቁን የሚያስረዳ የጽሁፍ ማስረጃ ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለማምጣት አግባብ ነው ብሎ በሚወስነው ጊዜ ውስጥ መርማሪው ወይም አቃቤ ህጉ ማስረጃውን ካላመጣ በቀር አስፈላጊው ስነስርአት ተሟልቶ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ እንዲለቀቅ በውሳኔው ላይ መግለጽ አለበት፡፡

6.                 የመንቀሳቀስ መብትን ስለመገደብ

ፍርድ ቤቱ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 4 ወይም 5 በተመለከተው መሰረት የዋስትና መብቱ በተከበረለት ሰው ላይ ከዚህ በታች ከተመለከቱት አንዱን ወይም ከአንድ በላይ  ትእዛዞች ሊሰጥ ይችላል፡፡  

. ከተወሰነ ክልል ውጭ እንዳይንቀሳቀስ፣

. ማስረጃ ሊያጠፋ በሚችልባቸው የተወሰኑ ቦታዎች እንዳይደርስ፣

. በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ አግባብ ላለው የምርመራ አካል ሪፖርት እንዲያደርግ፣

መ፣ወደውጭ አገር እንዳይወጣ፣

7.                 የሙስና ወንጀሎችን የማየት ስልጣን ስላለው ፍርድ ቤት

1.      አግባብ ባለው ሕግ መሰረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን እንዲታዩ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በፌዴራል መንግስት ስር የሚወድቁ የሙስና ወንጀሎችን በሚመለከት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን አለው፡፡

2.      አግባብ ባለው ሕግ መሰረት በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን እንዲታዩ የተደነገጉት ክሶች እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በክልል መንግስት ስር የሚወድቁ የሙስና ወንጀሎችን በሚመለከት የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን አለው፡፡

3.      ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ አስተዳደሮች ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት ስልጣን እንደሁኔታው አግባብ ባለው የፌዴራል ፍርድ ቤት የሚካሄድ ይሆናል፡፡  

ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የሚነሱ የመያዝ፣ የብርበራ፣ የቀነ ቀጠሮ፣ በማረፊያ ቤት የማቆየት፣ የዋስትና፣ የእግድ እንዲሁም ከምርመራ ጋር የተያያዙ ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች የሚታዩት የሙስና ወንጀሉን ክስ ለማየት ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡

ክፍል ሶስት

ስለእግድ

8.                 መርህ

1.      የዚህ አዋጅ አንቀጽ 10 እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተገኘ ማናቸውንም ንብረት ለማገድ ይችላል፡፡

2.      መርማሪ ወይም ዐቃቤ ህግ በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት እንዲታገድ በቃለ መሀላ በተደገፈ መረጃ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡

3.      ለእግድ የሚቀርብ ማመልከቻ የወንጀል ክስ ከተመሰረተ በኋላ ወይም የወንጀል ክሱ ከመመስረቱ በፊት ሊቀርብ ይችላል፡፡

9.                 ሌሎች ንብረቶች ስለሚታገዱበት ሁኔታ

1.      በሙስና ወንጀል የተገኘ ለመሆኑ መረጃ ባይቀርብም ምርመራ በተጀመረበት ወይም ክስ በቀረበበት የሙስና ወንጀል ተከሳሽ ያገኘው የማይገባ ጥቅም ወይም ያደረሰው ጉዳት ለመኖሩ በቃለ መሀላ ሲረጋገጥ በወንጀሉ ተገኘ ከተባለው የማይገባ ጥቅም ወይም ደረሰ ተብሎ ከሚገመተው ጉዳት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ በተከሳሽ ስም በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ወይም ንብረት ወይም በተከሳሽ ስም ያለ ንብረት እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ፣ እንዳይተላለፍ፣ ታግዶ እንዲቆይ በመርማሪ ወይም በአቃቤ ህግ አቤቱታ ሲቀርብ ፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

2.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት በሚሰጥ የእግድ ትእዛዝ የተጠርጣሪው በታገደው ንብረቱ የመጠቀም መብት አይነካም፡፡

10.             ስለማይታገዱ ንብረቶች

ለተከሳሹ የእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ንብረቶች በአንቀጽ 8 በተመለከተው መሰረት የእግድ ትእዛዝ አያርፍባቸውም፣ የእግድ ትእዛዝ ከማያርፍባቸው ውስጥ በተለይ የሚከተሉት ይገኙበታል፣

1.      ለተከሳሹና ለቤተሰቡ የዕለት አገልግሎት የሚጠቅሙ ልብሶች፣ የምግብ ማብሰያ የሆኑ የቤት ቁሳቁስ፣የመኝታ አልጋ፣ የአልጋ  ልብሶችና የብርድ ልብሶች፣

2.      ለራሱና ለቤተሰቡ ለዕለት ኑሮ ጠቃሚ የሚሆን ከሶስት ወር ያልበለጠ ስንቅ፣

3.      የተከሳሹንና የቤተሰቡን የእለት ኑሮ ለማሟላት የሚያገለግሉ ቀላል መሳሪያዎች፣

4.      ተከሳሹና ቤተሰቡ የሚተዳደሩበት ሌላ ንብረት የሌላቸው ሲሆንና የሚተዳደሩት ከታገደው ንብረት ከሚገኝ ገቢ ከሆነ መሰረታዊ ፍላጎትን ለማሟላት ለተከሳሹና   ለቤተሰቡ ፍርድ ቤቱ በቂ ነው ብሎ የሚገምተውን ያህል ገቢ፣

11.             የማመልከቻው ይዘት

1. የእግድ ትእዛዝ እንዲሰጥ የሚቀርብ በቃለመሀላ የተደገፈ ማመልከቻ፣

  1. የወንጀሉን ፍሬ ነገርና በየደረጃው የተወሰዱትን እርምጃዎች፣ ክስ ያልተመሰረተ ከሆነ ጉዳዩ የሚገኝበትን ደረጃ የሚያሳይ መረጃ፣

l.      የሚታገደው ንብረት ወይም ገንዘብ በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት መሆኑን የሚያሳዩ ወይም ተፈጽሞአል በተባለውና ምርመራ በተጀመረበት የሙስና ወንጀል አማካይነት ተጠርጣሪው ያገኘው የማይገባ ጥቅም ወይም የደረሰ ጉዳትን በሚመለከት አሳማኝ ምክንያቶች፣

. የንብረቶቹን ዝርዝርና አድራሻ፣

የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡

2.      የእገዳው ማመልከቻ እና የእግድ ትእዛዙን በመደገፍ የሚቀርቡ ጉዳዮች በተሟላና ግልጽ በሆነ ሁኔታ በቃለ መሀላው ውስጥ በዝርዝር መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

3.      የእግድ ትእዛዝ ከተሰጠ በኋላ በተጨማሪ የእግድ ትእዛዝ እንዲሰጥ የሚያስገድድ ሁኔታ የተፈጠረ እንደሆነ መርማሪው ወይም ዐቃቤ ህጉ ለፍርድ ቤት ተጨማሪ የእግድ ትእዛዝ እንዲሰጥ ማመልከት ይችላል፡፡

12.             የእግድ ትእዛዝ ስለመስጠት

1.      የዚሀ አዋጅ አንቀጽ 10 እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማመልከቻና ሰነዶች ከመረመረ በኋላ የእግዱን አስፈላጊነት ካመነበት የእግድ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡

2.      ተከሳሹ በሌለበት የእግድ ትእዛዝ ከተሰጠ መርማሪው ወይም ዐቃቤ ህጉ ትእዛዙንና የቃለ መሀላውን ግልባጮች ለተከሳሹና በትእዛዙ ስሙ ለተጠቀሰው ሌላ ሰው ያደርሳል፣ የእግድ ትእዛዙን ለሚመለከተው ለማናቸውም ሰው ያስታውቃል፡፡

3.      ፍርድ ቤቱ የተለየ ትእዛዝ ካልሰጠ በቀር ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ የእግድ ትእዛዝ የጸና ይሆናል፡፡

13.             ንብረት ጠባቂ ስለመሾም

ፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የሰጠበትን ንብረት አጠባበቅ በተመለከተ በዚህ አዋጅ ከአንቀጽ 17 እስከ 21 የተመለከቱት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

14.             አግባብ ያለው አካል ሀላፊነት

1. አግባብ ያለው አካል፣

          ንብረት ጠባቂው ንብረቱን በአግባቡ ማስተዳደሩን ይከታተላል፡፡

         ለ  lንብረት ጠባቂው ንብረቱን በአግባቡ አላስተዳደረም ብሎ ካመነ ምክንያቱን በመግለጽ መግለጫ ለፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት አግባብ ያለው አካል ያቀረበውን መግለጫ ተመልክቶ ፍርድ ቤቱ ተገቢ የመሰለውን ትእዛዝ ይሰጣል፡፡

15.              የእግድ ትእዛዝ ስለሚቋረጥበት ሁኔታ

1.      ፍርድ ቤቱ የውርስ ውሳኔ የሰጠ ከሆነ የእግድ ትእዛዙ ይቋረጣል፡፡

2.      ተከሳሹ በነጻ የተለቀቀ እንደሆነ የእግድ ትእዛዙ እንዲነሳለት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

3.      በዚህ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ 2 በተመለከተው መሰረት ለቀረበው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ አስተያየቱን እንዲሰጥ ይጠይቃል፡፡ አስተያየቱን ካዳመጠ በኋላ በቀረበው አቤቱታ መሰረት እግዱ እንዲነሳ ወይም እግዱ ሳይነሳ እንዲቆይ ሊወስን ይችላል፡፡

16.             የእግድ ትእዛዝ ስለማንሳት ወይም ስለማሻሻል

1.      የእግድ ትእዛዝ የደረሰው ወይም ትእዛዙን እንዲያውቅ የተደረገ ማናቸውም ሰው የእግዱ ትእዛዝ እንዲነሳለት ወይም እንዲሻሻል ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡

2.      በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የቀረበውን ማመልከቻና ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ከተቀበለው ለመርማሪው ወይም ለአቃቤ ህጉ እንዲደርሰው በማድረግ ምላሽ እንዲሰጥበት ያደርጋል፡፡

3.      የእግድ ትእዛዝ እንዲነሳ ወይም እንዲሻሻል የቀረበው አቤቱታ በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ያገኘው እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ሰጥቶ የነበረውን የእግድ ትእዛዝ እንዲሻሻል ወይም እንዲነሳ ሊያደርግ ይችላል፡፡

4.     ክዚህ በላይ በንኡስ አንቀጽ 3 በተመለከተው መሰረት ለመወሰን ተጣርቶ እንዲቀርብለት ፍርድ ቤቱ ባለሙያ ሊመድብ ይችላል፡፡  

ንኡስ ክፍል አንድ

የንብረት ጠባቂ ስለመሾም

17.             የንብረት ጠባቂ ስለሚሾምበት ሁኔታ

1.      ፍርድ ቤቱ የሚመችና ትክክለኛ መሆኑን የገመተ እንደሆነ የእግድ ትእዛዝ የተሰጠበትን ንብረት በተመለከተ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ትእዛዞች ለመስጠት ይችላል፣

. ንብረቱን ተቀብሎ የሚጠብቅ ሰው መርጦ መሾም፣

. ንብረቱን በይዞታ ወይም በአደራ አስቀማጭነት ወይም በጠባቂነት ለሌላ ሰው ሆኖ የያዘን ሰው ንብረቱን እንዲለቅ፣

 . የተለቀቀውን ንብረት ጠባቂው ተረክቦ በይዞታው ስር እንዲያደርግ፣ እንዲጠብቅና እንዲያስተዳድር ለማዘዝ፣

.ተቀባዩ የተረከበውን ንብረት ለመጠበቅ፣ ለማስተዳደርና ለማሻሻል የሚያስችለው ሥልጣን ለመስጠት፡፡

2.      ፍርድ ቤቱ ንብረት ጠባቂው ስለተቀበለው ንብረት የመክሰስ ወይም የመከሰስ መብት እንዲኖረው እንዲሁም ከንብረቱ የሚገኝ ኪራይ ትርፍ ወይም ሌላ ማንኛውም ገቢ ለመሰብሰብና የሰበሰበውንም ገንዘብ ጠቃሚ ለሚሆን ጉዳይ ለማዋል እንዲችል ወይም ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስሎ የታየውን ሌላ ስልጣን ሊሰጠው ይችላል፡፡

3.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 መሰረት ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ትእዛዝ ንብረት ጠባቂውን ለመሾም የሚያስፈልገውን ወጪ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘውም ሹመቱን ከመስጠቱ በፊት አስፈላጊው ማጣራት እንዲደረግ ማዘዝ ይችላል፡፡

4.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት በንብረት ጠባቂነት የሚሾመው የተፈጥሮ ሰው የሆነ እንደሆነ ይህ ሰው መልካም ሥነምግባና ችሎታ ያለው እንዲሁም ከተከሳሽ ጋር ዝምድና ወይም የጥቅም ግንኙነት የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡

5.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት በንብረት ጠባቂነት የሚሾመው የህግ ሰውነት ያለው ከሆነ ያለፉት ሶስት አመታት የሂሳብ አያያዙ ንጹህ መሆኑንና የጥቅም ግጭት አለመኖሩ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

6.      በዚህ አንቀጽ መሰረት ንብረት ጠባቂ የሚሆኑትን ለማሾም በመርማሪው ወይም በአቃቤ ህጉ ወይም በተጠርጣሪው ሊቀርብ ይችላል፡፡ ፍርድ ቤቱም እንደሁኔታው የሌላኛውን ተከራካሪ ወገን አስተያየት በመጠየቅ ይወስናል፡፡

18.             ስለንብረት ጠባቂው አበል ክፍያ

ለንብረት ጠባቂው ከተከበረው ንብረት ላይ የሚከፈለውን አበል በሚመለከት ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው  ጠቅላላ ወይም ልዩ ትእዛዝ ይወሰናል፡፡

19.             ንብረት ስለማረካከብ

በዚህ አዋጅ መሰረት የተከበረ ንብረትን ለንብረት ጠባቂው ለማረካከብ የሚወጣው ወጪ  ከተከበረው ንብረት ላይ በንብረት ጠባቂው አማካይነት ስለሚከፈልበት ሁኔታ  በፍርድ ቤት ይወሰናል፡፡

20.             ስለንብረት ጠባቂው ግዴታዎች

በዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 መሰረት የሚሾም ንብረት ጠባቂ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡

1.      እንዲያስተዳድር የተሾመበትን ንብረት በተመለከተ ኃላፊ ለመሆን የሚችል ዋስ ወይም መያዣ የመስጠት፣

2.      ፍርድ ቤቱ በሚወስነው ጊዜና የአቀራረብ ፎርም መሰረት የሂሳብ መግለጫ እየሰራ የማቅረብ፣

3.      ፍርድ ቤቱ በሚወስነው መሰረት የሚፈለግበትን ገንዘብ የመክፈል እና

4.      በራሱ ከባድ ቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ ባደረገው ጉድለት በተረከበው ንብረት ላይ ላደረሰው ጉዳት ሀላፊ ሆኖ የመክፈል፡፡

21.             የንብረት ጠባቂውን ግዴታ ስለማስከበር

1.      ንብረት ጠባቂው በራሱ ከባድ ቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ በንብረቱ ላይ ጉዳት ወይም ጉድለት ያደረሰ እንደሆነ የሚፈለግበትን ገንዘብ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ሊያዘው ይችላል፡፡  

ገንዘብ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ካዘዘው በኋላ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ጠባቂው ንብረቱ ተሽጦ ከሽያጩ ላይ የተገኘው ሀብት በቸልተኘነት ወይም ሆነ ብሎ ያደረሰው ጉድለት እንዲተካ ወይም ጉዳቱን ለመጠገን የሚያስፈልገውን ገንዘብ እንዲከፍል በማዘዝ ቀሪ ገንዘቡ እንዲመለስለት ለማድረግ ይችላል፡፡

ንኡስ ክፍል ሁለት

ስለማሸግና የሀብት ዝርዝር ስለማዘጋጀት

22.             መርህ

1.      ዕግድ የተሰጠበትን ንብረት አሽጎ መጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በዚህ ክፍል የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

2.      በፍርድ ቤት ትእዛዝ የተደረገውን እሽግ ፍርድ ቤቱ እንዲነሳ ካላዘዘ በቀር ማንም ሰው እሽጉን ለመቅደድ ወይም ለመክፈት አይችልም፡፡ በጉዳዩ ያገባኛል የሚል ወገን እሽጉ እንዲነሳለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡

23.             እሽግ እንዲደረግ ስለሚቀርብ ማመልከቻ

1.      መርማሪው ወይም ዐቃቤ ህጉ ንብረቱን ማሸግ አስፈላጊ መሆኑን በቃለ መሀላ ወይም በሌላ መንገድ በተረጋገጠ ማስረጃ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡

2.      የወንጀሉ ጉዳይ ውሳኔ ከማግኘቱ በፊት ፍርድ ቤት በራሱ አስተያየት ወይም ማመልከቻ ሲቀርብለት የማሸግ ትእዛዝ ለመስጠት ይችላል፡፡

3.      ፍርድ ቤት የማሸግ ትእዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ይህን ስራ ለመፈጸም ተገቢ የሆነ ሰው ከዚህ በኋላ ..አሻጊ.. በመባል የሚታወቅ መርጦ ይሾማል፡፡

24.             ስለመዝገብ

1.      አሻጊው በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት የእሽጉ ሥራ ከተፈጸመ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ የተገለጹትን ጉዳዮች የሚያመለክት የራሱ ፊርማ ያረፈበት እሽጉ የተደረገበት ቀንና ዓመተ ምህረት ያለበት መዝገብ ያዘጋጃል፡፡

. የፍርድ ቤቱ ትእዛዝና ትእዛዙ የተሰጠበት ቀንና ዓመተ ምህረት፣

. የታሸጉትን ነገሮች ዝርዝርና የሚገኙበትን ሥፍራ፣

. እንዲታሸጉ ከታዘዙት ውስጥ መገኘትና መታሸግ የሚገባቸው ሆነው ሳይገኙ የቀሩትን /የጎደሉትን/ ነገሮች ዝርዝር፣

. የታሸጉ ነገሮች ያሉበትን ቤት ወይም የሚገኙበትን ቦታ የሚጠብቀውን ወይም ለዚሁ ቤትና ስፍራ አላፊ የሆነ ሰው ካለ ስሙንና አድራሻውን፣

       2     የታሸጉ ንብረቶች የሚገኙበት ቤት ወይም ቦታ ቁልፍ ያለው ሲሆን አሻጊው መክፈቻዎቹን ለፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር ማስረከብ አለበት፡፡  

25.             ስለማይታሸጉ ነገሮች

1.      ከዚህ ቀጥሎ በተመለከቱት ንብረቶች ላይ የእሽግ ትእዛዝ አያርፍባቸውም

. በተፈጥሮአቸው የሚበላሹ ወይም ቶሎ የሚሻግቱና የሚበሰብሱ ሲሆኑ፣

. በመታሸጋቸው ምክንያት የሚበላሹ ወይም ቶሎ የሚሻግቱና የሚበሰብሱ ሲሆኑ፣

. ለባለንብረቱ አስፈላጊ የሆኑና ፍርድ ቤቱም አስፈላጊ መሆናቸውን ተረድቶ እንዳይታሸግባቸው ያዘዘ ሲሆን፣

2.      በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1/ሐ በተመለከተው መሰረት ፍርድ ቤቱ እንዳይታሸጉ ትእዛዝ የሰጠባቸውን ነገሮች ዝርዝር አሻጊው አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡

3.      በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት የእሽግ ትእዛዝ እንዲያርፍበት የተደረገው ንብረት በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ ተቀማጭ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል፡፡

26.             ስለኑዛዜዎችና ስለሌሎች የጽሁፍ ሰነዶች

1.      አሻጊው በሚያሽገው ነገር ውስጥ የኑዛዜ ጽሁፎች ወይም ቀድሞ የታሸጉ ነገሮች ወይም ሌሎች ሰነዶች ያገኘ እንደሆነ የነዚህኑ ጽሁፎች ዝርዝር አዘጋጅቶ ባንድ ላይ ጠቅልሎ በእሽጉ ውስጥ እንዲቀመጡ ካደረገ በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ ትእዛዝ እንዲሰጥበት ያዘጋጀውን ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል፡፡

2.      ፍርድ ቤቱም እነዚህ ሰነዶች ስለሚቀመጡበት ሁኔታና ስለአያያዛቸው ተስማሚ መስሎ የታየውን ውሳኔ ይሰጣል፡፡

27.             እሽግን ስለማንሳት

1.      እሽግ እንዲነሳ ማመልከቻ ሲቀርብ ወይም ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት እሽጉን ማንሳት ተገቢ መሆኑን ሲገምት ትእዛዙን በሚሰጥበት ጊዜ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ እንዲቀርቡ ያዛል፣ ባለጉዳዮቹም ቀርበው ያላቸውን ሀሳብ ለመግለጽ ይችላሉ፡፡

እሽጉ እንዲነሳ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ አሻጊው እሽጉን በማንሳት እሽጉ ሲከፈት የተገኙትን ነገሮች ዝርዝር አዘጋጅቶ ከፈረመባቸው በኋላ ቀኑንና ዓመተ ምህረቱን ጽፎ ያቀርባል፡፡

28             የንብረቶችን ዝርዝር ስለማዘጋጀት

1.      ትእዛዝ የተሰጠበትን ንብረት ዝርዝር እንዲዘጋጅና እንዲታወቅ ማስፈለጉን ፍርድ ቤቱ ሲረዳው ይህንኑ ዝርዝር ለማዘጋጀት ይችላል ብሎ የሚገምተውን ሰው /ከዚህ ቀጥሎ <<መዝጋቢ>>በመባል የሚታወቅ/ መርጦ የዚህኑ ንብረት ዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ይሰጣል፡፡

2.      መዝጋቢው ከሁለት የማያንሱ ምስክሮች ባሉበት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ላይ ተለይቶ የተገለጸውን የንብረት ዝርዝር ያዘጋጃል፡፡ ዝርዝሩም ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ነገሮች ይይዛል፡፡

. የንብረቱ ዝርዝር እንዲዘጋጅ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትእዛዝ እና

. የተመዘገቡትን ንብረቶች ትክክለኛ ዝርዝር ከዋጋቸው ግምት ጋር፡፡

3.      ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ከሰጠ የንብረቶቹ ዋጋ የሚገመተው በፍትሀ ብሄር ሥነሥርአት ሕግ አንቀፅ 131 በተመለከተው መሰረት በልዩ አዋቂ /ኤክስፐርት/ አማካይነት ይሆናል፡፡ ልዩ አዋቂው ባደረገው የዋጋ ግምት ዝርዝር መግለጫ ላይ ቀኑንና ዓመተ ምሕረቱን ጽፎና ፈርሞበት ከመዝጋቢው ራፖር ጋር ይያያዛል፡፡

የመዝጋቢው ራፖር የተጻፈበት ቀንና ዓመተ ምህረት ተሞልቶበትና ተፈርሞበት ለፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ ፍርድ ቤቱም በተለይ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው መዝገብ ውስጥ በፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር እንዲመዘገብ ካደረገ በኋላ ጉዳዩ ከሚመለከተው መዝገብ ጋር በማያያዝ አባሪ ሆኖ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡

ክፍል አራት

ስለንብረት አወራረስ ሥነሥርአት

29.             በፍርድ ቤት ንብረት እንዲወረስ ስለሚወሰንበት ሁኔታ

በሙስና ወንጀል ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በሙስና ወንጀሉ የተገኘ ተመጣጣኝ ንብረት እንዲወረስ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

30.             የመውረስ ውሳኔን ስለማዘግየት

1.      ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በወንጀል ድርጊቱ ጥቅም ማግኘት አለማግኘቱን ወይም ተመላሽ የሚሆነውን የንብረት መጠን ለመወሰን ተጨማሪ ማስረጃዎች ማግኘት አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የጥፋተኘነት ውሳኔ ከሰጠበት ቀን አንስቶ ከስድስት ወር ላልበለጠ ጊዜ ውሳኔውን ሊያዘገየው ይችላል፡፡

2.      በዚሀ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የመውረስን ውሳኔ ለማዘግየት የሚቻለው በዐቃቤ ህግ ጥያቄ ወይም በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ሊሆን ይችላል፡፡

31.             ንብረት እንዲወረስ ስለሚቀርብ ማመልከቻ

1.      ፍርድ ቤቱ ንብረት እንዲወረስ ካልወሰነ በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት መወረስ ጥያቄ በዐቃቤ ሕግ አመልካችነት ሊታይ ይችላል፡፡

2.      የንብረት መወረስ ጥያቄ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በኋላ ሊቀርብ ይችላል፡፡

32.             ንብረቱን ለማስመለስ ለሚመለከተው አካል ስለማሳወቅ

በሙስና ወንጀል የተገኘ ንብረት የአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ወይም የሌላ ግለሰብ ንብረት ወይም ገንዘብ ከሆነ ይኸው  የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ወይም ግለሰብ  በሙስና የተገኘውን ንብረት ወይም ገንዘብ እንዲመለስ በፍትሀ ብሄር ክስ እንዲመሰርት አግባብ ያለው አካል ሊያሳውቀው ይችላል፡፡ አግባብ ያለው አካል በመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት የሚመሰረተውን ክስ በሚመለከት ውጤቱን ይከታተላል፡፡

33.             ለፍርድ ቤት ስለሚቀርበው የማስረጃ ደረጃ

አንድ ሰው በሙስና የወንጀል ድርጊት ሳቢያ ጥቅም ያገኘ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ወይም ተመላሽ የሚሆነውን ገንዘብ መጠን መወሰንን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮችን ለማስረዳት የሚቀርበው የማስረጃ ደረጃ በፍትሐ ብሄር ክርክር ጊዜ እንደሚቀርበው የማስረጃ ደረጃ ይሆናል፡፡

34.             ተመላሽ ስለሚሆነው የንብረት ወይም የጥቅም መጠንና ንብረቱ ለመንግስት ገቢ ስለሚሆንበት ሁኔታ

1.      ተከሳሹ በሙስና ወንጀል ያገኘው ንብረትና በወንጀል ከተገኘው ንብረት ያፈራው ንብረት ወይም ተመጣጣኙ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

2.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 በተመለከተው መሰረት ተመላሽ የሚሆነው የንብረት መጠን ተከሳሹ ካገኘው ጥቅም ወይም ያገኛል ተብሎ ከሚገመተው ጥቅም ማለፍ የለበትም፡፡

3.      በፍርድ እንዲወረስ ውሳኔ የተሰጠበትን ንብረት ለመንግስት ገቢ ስለሚደረግበት ሁኔታ ዝርዝር አፈጻጸሙ በደንብ ይወሰናል፡፡

ክፍል አምስት

ቅድመክስ ዝግጅት

35.             መርህ

የሙስና ወንጀል ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ጭብጦችና የማስረጃው ዝርዝር ውስብስብ በመሆኑ ምክንያት የፍርድ ሂደቱን የሚያራዝመውና የሚያወሳስበው መስሎ ከታየውና በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 36 የተመለከቱትን አላማዎች ሊያሟላ ይችላል ብሎ ካመነ የቅድመክስ ዝግጅት እንዲከናወን ሊወስን ይችላል፡፡

36.             የቅድመክስ ዝግጅት ዓላማና ሂደት

1.      የቅድመ ክስ ዝግጅት አላማ የሚከተሉት ናቸው፡፡

. ለክሱ አወሳሰን ሊረዱ የሚችሉ ጭብጦችን ለመለየት

. ባለጉዳዮች ጭብጦቹን እንዲረዱ እገዛ ለማድረግ

. የክሱን ሂደት ለማፋጠን

. ፍርድ ቤት የክሱን አካሄድ ለመምራት እንዲያስችለው ለማገዝ

2.      በቅድመክስ ዝግጅት ሂደት ፍርድ ቤቱ

. የማስረጃ ተቀባይነትን በተመለከተ በሚነሳ ጥያቄ

. መደበኛው የክስ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ውሳኔ ሊያገኘ በሚገባው በማናቸውም የህግ ጥያቄ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል፡፡

37.             የዐቃቤ ህግ ግዴታ

ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህጉን፣

1.      በዚህ አዋጅ አንቀጽ 38 ሥር የተዘረዘሩትን በተመለከተ ለፍርድ ቤቱና ለተከሳሽ የጽሁፍ መግለጫ እንዲሰጥ፣

2.      ለክሱ ሂደት ሊረዱ የሚችሉ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ እና ክሱን ለመረዳት የሚያስችል ማቴሪያል ፍርድ ቤቱ በሚያዘው ፎርም መሰረት እንዲያዘጋጅና ለፍርድ ቤትና ለተከሳሽ እንዲሰጥ፣

3.      በእሱ አስተያየት ተቀባይነት ሊኖራቸው ይገባል የሚላቸውን ይዘታቸው እውነትነት ያላቸውን ሰነዶች እና ሌሎች ስምምነት ሊደረስባቸው ይችላሉ የሚላቸውን ጉዳዮች ለፍርድ ቤትና ለተከሳሽ በጽሁፍ እንዲያስታውቅ፣

4.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የቀረበውን የጽሁፍ መግለጫ የተከሳሽን ተቃውሞ መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ባመነበት መንገድ አንዲያሻሽል ሊያዘው ይችላል፡፡

38.             በዐቃቤ ህግ የሚቀርብ የጽሁፍ መግለጫ

በዚህ አዋጅ አንቀጽ 37 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የሚቀርብ የጽሁፍ መግለጫ የሚከተሉትን የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡

1.      ለክሱ መሰረት የሆኑትን መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች፣

2.      በአቃቤ ህግ አመልካችነት ፍርድ ቤት ሲፈቅድ የምስክሮችን ስም በምስጢር መያዝ ካላስፈለገ በስተቀር ለፍሬ ነገሩ የሚጠሩትን ምስክሮች፣

3.      ለፍሬ ነገሩ አግባብነት ያላቸውን ኤግዚቢቶች እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎች፣

4.      ዐቃቤ ህጉ ለክሱ መሰረት ያደረገውን የህግ ድንጋጌ፣

5.      ከዚህ በላይ ባሉት ንኡስ አንቀጾች ከተመለከቱት የሚመነጩ ወይም የተያያዙ ናቸው ብሎ ዐቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው፡፡

39.             የተከሳሽ ግዴታ

ዐቃቤ ህጉ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ከፈጸመ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ፣

1.      የመከላከያውን አጠቃላይ ነጥቦች ይዘት እና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ሊያነሳ ያሰባቸውን ጭብጦች በተመለከተ ለፍርድ ቤቱና ለዐቃቤ ሕግ የጽሁፍ መግለጫ እንዲሰጥ፣

2.      በቀረበው ክስ ላይ ያለውን ተቃውሞ ለፍርድ ቤቱና ለዐቃቤ ህግ የጽሁፍ መግለጫ እንዲሰጥ፣

3.      ለመከላከያው መሰረት ያደረጋቸውን የሕግ ነጥቦችና ማስረጃዎችን በተመለከተ ለፍርድ ቤቱና ለዐቃቤ ሕጉ የጽሁፍ መግለጫ እንዲሰጥ፣

4.      በዚህ አዋጅ አንቀጽ 37 ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት ዐቃቤ ህጉ ያቀረባቸውን ሰነዶችና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከአቃቤ ሕግ ጋር የሚስማማባቸው ነጥቦች ካሉ እንዲገልጽ፣ ያልተስማማባቸው ካሉ ምክንያቱን እንዲገልጽ ሊያዘው ይችላል፡፡

40.             ስለትእዛዝ ይግባኝ

በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 36 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ ይቻላል፡፡ ሆኖም በተሰጠው ውሳኔ ምክንያት መዝገቡ ካልተዘጋ በስተቀር የጉዳዩ መታየት አይቋረጥም፡፡

41.             ፍርድ ቤት መዝገቡን ስለሚዘጋበት ሁኔታ

በቅድመ ክስ ሂደት በአቃቤ ህግ የቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት የለውም ተብሎ የተወሰነ እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት የክስ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ አቃቤ ህጉ ሌሎች ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በተመሳሳይ ጉዳይ በድጋሚ ክስ ከማቅረብ አይከለከልም፡፡  

ክፍል ስድስት

ስለማስረጃ

42.              ማስረጃ ስለመጠየቅ

1.      አንድ መርማሪ ወይም አቃቤ ህግ አንድ ተጠርጣሪ በወንጀል ድርጊት ተጠቃሚ መሆኑን ወይም ከወንጀል ድርጊት የተገኘውን የጥቅም መጠን ወይም የሚገኘበትን ቦታ ለማወቅ አግባብ ያለው ሰነድ በእጁ ያለ ወይም የሚገኝበትን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ወይም አካል እንዲሰጠው ወይም እንዲያይ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡

2.      ፍርድ ቤቱ ጥያቄው አግባብነት ያለው ሆኖ ካገኘው ጉዳዩ የሚመለከተውን ሰው መጥራት ሳያስፈልግ በእጁ የሚገኘውን ወይም ይገኛል ተብሎ የሚጠረጠረውን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ በሚወስነው ቀን ውስጥ ሰነዱን ለመርማሪው ወይም ለዐቃቤ ህጉ እንዲሰጥ ወይም እንዲያሳይ ለማዘዝ ይችላል፡፡

3.      ፍርድ ቤቱ በሶስተኛ ሰው እጅ የሚገኝ ማስረጃ ለመርማሪው ወይም ለአቃቤ ህግ እንዲሰጥ ወይም መርማሪው ወይም አቃቤ ህጉ እንዲያየው ለማዘዝ ይችላል፡፡

43.             ግብረ አበርን ከክስ ነጻ ስለማድረግ

1.      በሙስና ወንጀል ተካፋይ የሆነ ሰው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ስለተፈጸመው ድርጊትና ስለተባባሪዎች ሚና ጠቃሚ ማስረጃ ከሰጠ በፌዴራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይም አግባብ ባለው አካል የበላይ ሃላፊ ውሳኔ ከክሱ ነጻ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

2.      ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ..ጠቃሚ ማስረጃ.. ማለት፣

h.      የቀረበው ማስረጃ ብቻውን በቀረበው የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኛነት ውሳኔ ለማሰጠት በቂ ከሆነ፣ ወይም

l.      ማስረጃው በመገኘቱ ሌሎች መረጃዎችንም ለማግኘት መሰረታዊ ፍንጭ ሆኖ የሚያገለግል ከሆነ ወይም

. የተገኘው ማስረጃ ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በመቀናጀት የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማሰጠት የሚያስችል ከሆነና ይኸው ማስረጃ ባለመካተቱ ወንጀሉን ለማረጋገጥ በሌላ መልኩ የተሰባሰበው ማስረጃ በቂ የማይሆን ነው ተብሎ ሲታመን፣ ነው፡፡

3.      ተጠርጣሪው ማስረጃውን በመስጠቱ ከክስ ነጻ የሚሆን ለመሆኑ ስልጣን ያለው ባለስልጣን በጽሁፍ ማረጋገጫ ይሰጠዋል፡፡ አግባብ ያለው አካል ከተጠርጣሪው የተገኘውን ማስረጃ በሰጠው ሰው ላይ በማስረጃነት ሊያቀርብ አይችልም፡፡

4.      ተጠርጣሪው በገባው ስምምነት መሰረት ማስረጃውን ካላቀረበ ወይም ተገቢውን ምስክርነት ካልሰጠ ስምምነቱን እንዳላከበረ ተቆጥሮ ያለመከሰስ መብቱ ይነሳል፡፡

5.      ከክስ ነጻ የተደረገ በሙስና ወንጀል ተካፋይ የሆነ ሰው የሚሰጠው የምስክርነት ቃል ክብደት ማንኛውም ምስክር ከሚሰጠው ምስክርነት እኩል ዋጋ አለው፡፡

6. በዚህ አንቀጽ መሰረት ከክሱ ነጻ የሚሆን በሙስና ወንጀል ተካፋይ የሆነ ሰው በወንጀሉ ያገኘው ንብረት ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

44.             ስለአስጠቂ ምስክር

1.      በዐቃቤ ህግ ወይም በመከላከያ ምስክርነት የቀረበ ማንኛውም ሰው በምስክርነት በተጠራበት ጉዳይ እውነቱን ለመናገር ባለመፈለግ ቀድሞ ከሰጠው የምስክርነት ቃል የሚቃረን የምስክርነት ቃል የሰጠ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ምስክሩን ያቀረበውን ወገን መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡

2.      ፍርድ ቤቱ መሪ ጥያቄ እንዲጠየቅ ከመፍቀዱ በፊት ተቃራኒ የምስክርነት ቃል የሰጠ መሆን አለመሆኑን ምስክሩን ይጠይቀዋል፡፡ ምስክሩ ተቃራኒ የምስክርነት ቃል መስጠቱን ከተቀበለ መሪ ጥያቄውን ይፈቅዳል፡፡

3.      ምስክሩ ተቃራኒ የምስክርነት ቃል መስጠቱን የካደ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ምስክሩ ተቃራኒ ቃል መስጠት አለመስጠቱን ይወስናል፡፡

45.             ስለኮምፒዩተር ሰነድ

በኮምፒዩተር በተገኘ ሰነድ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ በማስረጃነት ተቀባይነት የማይኖረው፣

1.      በኮምፒዩተር ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ምክንያት በሰነዱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ትክክለኛ አለመሆኑን የሚያሳምኑ በቂ ምክንያቶች መኖራቸውን ወይም

1.      ኮምፒዩተሩ ስራ ላይ ባልዋለባቸው ጊዜያት በተገቢው መንገድ የማይሰራ መሆኑን ወይም ኮምፒዩተሩ በስራ ላይ ባልዋለበት ወይም ከስራ ውጭ በሆነበት ጊዜ የሰነዱን አወጣጥ ወይም ይዘት የሚያፋልስ መሆኑን½¥úyT ሲቻል ነው፡፡

46.             ግንኙነትንና ደብዳቤን ስለመጥለፍ

1.      ለሙስና ወንጀል ምርመራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በስልክ፣ በቴሌኮሚኒኬሽንና በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚደረግ ግንኙነት እንዲሁም ደብዳቤ እንዲጠለፍ አግባብ ያለው አካል የበላይ ሀላፊ ማዘዝ ይችላል፡፡

2.      ለሙስና ወንጀል ምርመራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በካሜራ፣ ድምጽ መቅረጫ እና የመሳሰሉት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካይነት የተሰባሰቡ ማስረጃዎች እንደማንኛውም ማስረጃ የሙስና ወንጀል መፈጸሙን ለማስረዳት ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

3.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የሚሰጥ ትእዛዝ ለጠለፋው ምክንያት የሆነውን ወንጀል እና ጠለፋው የሚቆይበትን ጊዜ የሚጠለፈው የስልክ ግንኙነት ከሆነ ጠለፋው የሚመለከተውን የግንኙነት መስመር መግለጽ ይኖርበታል፡፡ አግባብ ያለው አካል የበላይ ሀላፊ በተለየ ሁኔታ ካልወሰነ በቀር ትእዛዙ የሚጸናው ከአራት ወር ላልበለጠ ጊዜ ይሆናል፡፡

47.             ስለመቅዳት

1.      ግንኙነት መቅዳትን በተመለከተ ትእዛዙን የሚፈጽመው አካል በእያንዳንዱ ጠለፋ የተቀዳውን እና ጠለፋው የተጀመረበትንና ያበቃበትን ሰአት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

2.      ትእዛዙ የተላለፈለት አካል በጠለፋ ከተቀዳው ውስጥ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ እውነቱን ለማወቅ የሚረዳውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ክፍል ሰባት

የሙስና ድርጊትን ስለሚጠቁሙ ሰዎች ጥበቃ

48.             ዓላማ

የጥበቃው አላማ

1.      የሙስና ወንጀል እንዲጋለጥ ለማበረታታት እና፣

2.      ጥቆማውን ያቀረበውን ሰው መብትና ጥቅም ተገቢው ግምት እንዲሰጥ ለማድረግ ነው፡፡

49.             ስለጥቆማ አቀራረብ

1.      የሙስና ድርጊት የጠቋሚውን ስም ተገልጾ ወይም ሳይገለጽ አግባብ ላለው አካል ሊቀርብ ይችላል፡፡

2.      አንድን ጥቆማ በአግባቡ አግባብ ላለው አካል ከደረሰ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ጥቆማውን እንደተቀበለው ይቆጠራል፡፡

50.             ከኃላፊነት ነጻ ስለመሆን

በሕግ፣ በቃለ መሀላ ወይም በስምምነት ማስረጃን በሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ ያለበት ማናቸውም ሰው ማስረጃውን አግባብ ላለው አካል በመስጠቱ ህጉን፣ ቃለ መሐላውን ወይም ስምምነቱን እንደጣሰ አያስቆጥረውም፡፡

51.             ጥቆማውን ስለሚቀበለው አካል

1.      አግባብ ያለው አካል ከማናቸውም ሰው የሙስና ድርጊትን በተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡

2.      አግባብ ያለው አካል ጥቆማውን እንደደረሰው በመዝገብ ውስጥ ማስፈር ይኖርበታል፡፡

3.      አግባብ ያለው አካል የደረሰውን ጥቆማ በተመለከተ፣

. ተጠሪ ለሆነው አካል አመታዊ ሪፖርት የማቅረብ

. በስም ጥቆማ ላቀረበ ሰው በጥቆማው ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ተገቢውን መረጃ የመስጠት

ሀላፊነት አለበት፡፡

4.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3/ለ መሰረት የሚሰጥ ማስረጃ ለማናቸውም ሰው ደህንነት የሚያሰጋ ወይም የወንጀሉን የምርመራ ሂደት የሚያደናቅፍ ከሆነ ማስረጃው መሰጠት የለበትም፡፡

52.             በመዝገብ ስለሚሰፍሩ ጉዳዮች

አግባብ ያለው አካል የሚደርሰውን ጥቆማ በተመለከተ ቢያንስ የሚከተሉትን መረጃዎች በመዝገብ ማስፈር ይኖርበታል፡፡

1.      የሚታወቅ ከሆነ የጠቋሚውን ስም

2.      የጥቆማውን ፍሬ ሀሳብ እና

3.      ጥቆማውን አስመልክቶ ስለተወሰደው እርምጃ

53.             የቂም በቀል እርምጃ ህገወጥ ስለመሆኑ፣

1.      ማንኛውም ሰው በሌላ በማንኛውም ሰው ላይ ጥቆማ አቅርቦአል ወይም ምስክርነት ሰጥቶአል ወይም ለማቅረብ፣ ለመስጠት አስቧል በሚል ጉዳት ማድረስ ወይም ለማድረስ መሞከር ወይም ማሴር ህገወጥ ድርጊት ነው፡፡

2.      እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኛውን ከቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችለው ስርአት መዘርጋት ይኖርበታል፡፡

54.             የቂም በቀል እርምጃን ስለማገድ

1.      የቂም በቀል እርምጃ የተወሰደበት ሰው ሰራተኛ ከሆነ በአስተዳደሩ የተወሰደበት እርምጃ እንዲታገድለት ለፍርድ ቤት ወይም አግባብ ላለው አካል አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡

2.      በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት ወይም አካል አቤቱታውን ወዲያውኑ በመቀበል የቂም በቀል እርምጃ መኖሩን ካረጋገጠ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆም ጊዜያዊ የእግድ ትእዛዝ መስጠት ይኖርበታል፡፡

3.      አግባብ ያለው አካል አግባብ ባለው ህግ መሰረት የቂም በቀል እርምጃ በወሰደው ሰው ላይ የወንጀል ክስ የመሰረተ እንደሆነ በቀረበው ክስ ላይ ውሳኔ  እስኪሰጥ ድረስ የእግድ ትእዛዙ እንደጸና ይቆያል፡፡

4.      በሚሰጠው የእግድ ትእዛዝ ቅር የተሰኘ ወገን አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ በፍርድ ቤት በቀረበው አቤቱታ የመጨረሻ ውሳኔ እሰኪሰጥ ድረስ ግን የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተፈጻሚ መሆን አለበት፡፡  

ክፍል ስምንት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

55.             ተፈጻሚነት ስላላቸው ህጎች

የወንጀል ሥነሥርአት ህግ፣ የፍትሀ ብሄር ሥነሥርአት ህግ፣ የወንጀል ህግና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ህጎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡

56.             ስለቅጣት

1.      ተከሳሹ ወይም የእግድ ትእዛዙ የሚመለከተው ሌላ ሰው ፍርድ ቤት የሰጠውን የእግድ ትእዛዝ ያላከበረ እንደሆነ ተከሳሹ ወይም ትእዛዙን ያላከበረው ሰው በፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ከሁለት አመት ባልበለጠ የእስራት ቅጣት እና ከብር አስር ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

2.      በወንጀል ህግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 22 ንኡስ አንቀጽ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ሆን ብሎ በንብረት ላይ ጉዳት ወይም ጉድለት ያደረሰ ወይም እሽጉን የቀደደ ወይም የከፈተ ከሶስት አመት በማይበልጥ እስራትና ከብር ሃያ ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

57.             መሸጋገሪያ ድንጋጌ

1.      የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ 1996 ስራ ላይ እስከሚውል ድረስ የሙስና ወንጀል ትርጉም በአዋጅ ቁ 236/93 የተመለከተው ይሆናል፡፡

2.      ተቃራኒ ማስረጃ ካልቀረበ በቀር፣ የሙስና ወንጀሎቹ የተፈጸሙት ያለአግባብ ሰውን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት መሆኑ በተደነገገ ጊዜ ክስ በተመሰረተበት የወንጀል ድንጋጌ የተመለከተው ግዙፋዊ ፍሬነገር መፈጸሙ  ከተረጋገጠ ድርጊቱ የተፈጸመው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራስ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት ወይም የሶሰተኛ ወገንን መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት እንደሆነ ይገመታል፡፡

58.             የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎች

1.      የጸረሙስና የልዩ ስነስርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁ 236/1993 እንደተሻሻለ  በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡

2.      ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሌሎች ሕጎች በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

59.             አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ ከጥር 25 ቀን 1997 ዓ.      ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

 አዲስ አበባጥር 25 ቀን 1997

ግርማ ወልደጊዮርጊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፕሬዚዳንት