|
የተሻሻለው
የፌዴራል
የስነምግባርና
የጸረ ሙሰና ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ ክፍል
አንድ ጠቅላላ
ክፍል
ሁለት
ክፍል
ሶስት
ልዩ ልዩ
ድንጋጌዎች አዋጅ
ቁ የተሻሻለው
የፌዴራል
የስነምግባርና
የጸረ ሙሰና ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ የኢትዮጵያ
መንግስትና ሕዝቦች
ሙስና እና ብልሹ
አሠራር የአንድን
አገር ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊ እና
ፖለቲካዊ እድገት
የሚገታ ተግባር
መሆኑን የተገነዘቡ
በመሆናቸው፣ አገሪቱ
የተያያዘችውን
የእድገት ጎዳና እና
የዲሞክራሲያዊ
ሥርአት ግንባታ
ለማፋጠንና
ቀጣይነት ያለው
እንዲሆን ሙስናን
እና ብልሹ አሠራርን
በቁጥጥር ሥር ማዋል
አስፈላጊ በመሆኑ፣
ለዚህም ሙስናንና
ብልሹ አሰራርን
ለመሸከም
የማይፈልግ እና
ይህንኑ በብቃት
ለመዋጋት ዝግጁ
የሆነ ሕብረተሰብ
መፍጠር አስፈላጊ
በመሆኑ፣ ሙስናንና
ብልሹ አሰራርን
ለመመርመር፣
ለመክሰስ
ለመቆጣጠርና
ለመከላከል መልካም
ሥነ ምግባር
በኀብረተሰቡ
ውስጥ እንዲስፋፋ
በማድረግ ሙስናንና
ብልሹ አሠራርን
በብቃት መዋጋት
እንዲቻል፣
የኮሚሽኑን
አሰራርና
እንቅስቃሴ
የግልጽነትና
የተጠያቂነት
መርሆዎችን
በሚገልጽ መልኩ
እንዲሁም ኮሚሽኑ
ሀላፊነቱን በተሻለ
ብቃት እንዲወጣ
በሚያስችለው መልኩ የኮሚሽኑን
ማቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል
በማስፈለጉ፣ የኮሚሽኑን
ስልጣንና ተግባር
ከኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ
ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ የወንጀል
ህግ ጋር በተጣጣመ
ሁኔታ ማሻሻል
በማስፈለጉ፣ ኮሚሽኑ
በከባድ የሙስና
ወንጀሎች ላይ
ትኩረት አድርጎ
እንዲንቀሳቀስ
ማድረግ አስፈላጊ
ሆኖ በመገኘቱ፣ ኮሚሽኑ
ከሌሎች አግባብነት
ካላቸው የምርመራና
የአቃቤ ህግ ተቋማት
ጋር ስለሚሰራበት
ሁኔታ ዝርዝር
ድንጋጌዎችን
መደንገግ
በማስፈለጉ፣ በሌሎችም
ግልጽነት
በሚያንሳቸው
አንዳንድ የአዋጁ
ድንጋጌዎች ላይ
ማሻሻያዎችን
ማድረግ
በማስፈለጉ፣ በኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ
ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ህገ
መንግስት አንቀጽ 55/1/
መሰረት የሚከተለው
ታውጆአል፡፡ ክፍል
አንድ ጠቅላላ 1.
አጭር
ርእስ ይህ
አዋጅ <<የተሻሻለው
የፌዴራል
የስነምግባርና
የጸረ ሙስና ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 433/1997 >>
ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡ 2.
ትርጓሜ የቃሉ
አገባብ ሌላ ትርጉም
የሚያሰጠው ካልሆነ
በስተቀር በዚህ
አዋጅ ውስጥ፣ 1.
<<ኮሚሽን>>
ማለት የፌዴራል
የሥነ ምግባር እና
የጸረሙስና ኮሚሽን
ነው፡፡ 2.
<<ኮሚሽነር
እና ምክትል
ኮሚሽነር>> ማለት
እንደቅደም ተከተሉ
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር
ወይም ምክትል
ኮሚሽነር ነው፡፡ 3. <<የመንግስት
መስሪያ ቤት>> ማለት
ሙሉ በሙሉ ወይም
በከፊል በመንግስት
በጀት የሚተዳደር
እና የፌዴራል
መንግስቱ ስራዎች
የሚከናወኑበት
ማናቸውም መስሪያ
ቤት ነው፡፡ 4. <<የመንግስት
የልማት ድርጅት>>
ማለት የመንግስት
ባለቤትነት ድርሻ
በሙሉ ወይም በከፊል
ያለበት ማናቸውም
የፌዴራል መንግስት
የልማት ድርጅት
ወይም የአክሲዮን
ኩባንያ ነው፡፡ 5. <<የመንግስት
ባለሥልጣን>> ማለት
የህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤትና
የፌዴሬሽን ምክር
ቤት አባሎች፣
ከሚኒስትር ደረጃ
በላይ የሆኑ
የፌዴራል መንግስት
ባለስልጣኖች፣
ሚኒስትሮች፣
ሚኒስትር
ዴኤታዎች፣ ምክትል
ሚኒስትሮች፣
ኮሚሽነሮች፣
ምክትል
ኮሚሽነሮች፣
የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ዳኞች፣
የብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት ምክር ቤት
አባሎች፣ ከክልል
ቢሮ ሃላፊዎች በላይ
ያሉ ባለስልጣኖች፣
የክልል መንግስት
ቢሮ ሃላፊዎች፣
የክልል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ዳኞች፣
የአዲስ አበባ
መስተዳድርና
የድሬዳዋ
መስተዳድር የምክር
ቤት አባሎች፣
ከመስተዳድሮቹ ቢሮ
ሃላፊዎች በላይ ያሉ
ባለስልጣኖች፣
የመስተዳድሮቹ ቢሮ
ሃላፊዎች እና
በተመሳሳይ ደረጃ
ላይ የሚገኙ
የፌዴራል፣ የክልል
እንዲሁም የአዲስ
አበባና የድሬዳዋ
መስተዳድር
ባለስልጣኖችን
ይጨምራል፡፡ 6.
<<የመንግስት
ሠራተኛ>> ማለት በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 5 ውስጥ
ከተጠቀሱት ውጭ ያለ
በፌዴራል ወይም
በክልል ወይም
በአዲስ አበባ
መስተዳድር ወይም
በድሬዳዋ
መስተዳድር
የመንግስት መስሪያ
ቤት ወይም የልማት
ድርጅት ውስጥ
ተሹሞ፣ ተመድቦ፣
ተቀጥሮ፣ በህዝብ
ተመርጦ የሚሰራ ሰው
ነው፡፡ 7.
<<የሥነምግባር
አውታሮች>> ማለት
በመንግስት
አስተዳደር ውስጥ
ምግባረ ብልሹ
ባህርያትን
በከፍተኛ ደረጃ
ለመቀነስ እና ሙያዊ
ብቃትን እና መልካም
ሥነምግባርን
ለማበረታታት
የሚያገለግሉ
ዘዴዎች፣ አካላት፣
ሥርአቶች ወይም
አስፈላጊ ሁኔታዎች
እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡ 8.
<<ከባድ
የስነምግባር መጣስ>> ማለት ከስራ
ሊያሰናብት የሚችል
የሥነምግባር ጥፋት
ነው፡፡ 9.
<<ከባድ
የሙስና ወንጀል>>ማለት ሀ.
ከፍተኛ
ስትራቴጂያዊ
ጠቀሜታ ባላቸው
የመንግስት መስሪያ
ቤቶችና የመንግስት
የልማት ድርጅቶች
ላይ የሚፈጸሙ
ከፍተኛ የገንዘብ
መጠንን ያካተቱ
የሙስና ወንጀሎች
ወይም፣ ለ.
የመንግስት
ባለሥልጣንን
የሚመለከቱ የሙስና
ወንጀሎች ወይም፣ ሐ.
በአገር
ሉአላዊነት፣
ኢኮኖሚ፣ ጸጥታ
እንዲሁም
በሕብረተሰቡ ኑሮ
ላይ ከፍተኛ ጉዳት
የሚያደርሱ ወይም
ሊያደርሱ የሚችሉ
የሙስና ወንጀሎች
ናቸው፡፡ 10.
<<የባንክ ሂሳብ>>
ማለት በባንክ
የተቀመጠ ገንዘብ፣
ወርቅና የመሳሰሉት
ውድ እቃዎች
እንዲሁም አንድ
ደንበኛ ከባንኩ ጋር
የሚያደርጋቸውን
ማናቸውንም
ግንኙነቶች/
T‰N²K>ñC
/ የሚያጠቃልል
ነው፡፡ 11.<<ሰው>>
ማለት የተፈጥሮ ሰው
ወይም በሕግ
የሰውነት መብት
የተሰጠው አካል
ነው፡፡ ክፍል
ሁለት
ስለኮሚሽኑ
መቋቋም እና
ሥልጣንና ተግባር 3.
የኮሚሽኑ
መቋቋም 1.
የፌዴራል
የሥነምግባር እና
የጸረ ሙስና ኮሚሽን/
ከዚህ በኋላ ኮሚሽኑ
እየተባለ የሚጠራ/
ራሱን የቻለ
የፌዴራል መንግስት
መሥሪያ ቤት ሆኖ
በዚህ አዋጅ መሰረት
ተቋቁሟል፡፡ 2.
የኮሚሽኑ
ተጠሪነት ለጠቅላይ
ሚኒስትሩ
ይሆናል፡፡ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 3 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ቢኖርም ኮሚሽኑ በሚመረምራቸው ወይም ክስ በሚመሰርትባቸው ወይም ክስ በመሰረተባቸው ጉዳዮች ላይ ከማንኛውም ሰው ወይም አካል ጣልቃ ገብነትና አመራር ነጻ ነው፡፡ 5.
ዋና
መስሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል፡፡ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በየክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን ሊያቋቁም ይችላል፡፡ 6.
የኮሚሽኑ
ዓላማዎች ኮሚሽኑ
የሚከተሉት
ዓላማዎች
ይኖሩታል፡፡ 1.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር የሥነ
ምግባር እና የጸረ
ሙስና ትምህርቶችን
በማስፋፋት የነቃ
እና ሙስናን ሊሸከም
የማይችል
ሕብረተሰብ
እንዲፈጠር ጥረት
ማድረግ፣ 2.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር የሙስና
ወንጀልን እና ብልሹ
አሠራርን
መከላከል፣ 3.
የሙስና
ወንጀልን እና ብልሹ
አሠራርን ማጋለጥ፣
መመርመር እና
መክሰስ፣ ኮሚሽኑ
የሚከተሉት
ሥልጣንና ተግባራት
ይኖሩታል፣ 1.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር
ስለሙስና ጎጂነት
የህዝቡ ንቃተ ህሊና
እንዲጎለብት
በማስተማር እና
መልካም ሥነምግባር
በሕዝብ አገልግሎት
እና በኀብረተሰቡ
ውስጥ እንዲስፋፋ
በማድረግ ሙስናንና
ብልሹ አሰራርን
መዋጋት፣ 2.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር
በመንግስት መ/ቤቶች
እና በመንግስት
ልማት ድርጅቶች
ውስጥ ለሙስናና
ለብልሹ አሰራር
የተጋለጡና ሊጋለጡ
የሚችሉ የአሰራር
ሥርአቶችን
በማጥናት ወይም
እንዲጠኑ በማድረግ
እንዲሻሻሉ
ማማከርና ማሳሰብ፣
የአሰራር ስርአቶቹ
የተሻሻሉ
መሆናቸውን
መከታተል እና
አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝም ተገቢ የሆነው
እርምጃ እንዲወሰድ
ወይም ውሳኔ
እንዲሰጥ አግባብ
ላለው አካል
በማሳወቅ ወይም
በማሳሰብ ሙስናን
የመከላከል፣
በሌሎች ሰዎች
ሲጠየቅ ተመሳሳይ
ምክርና ድጋፍ
የመስጠት፣ 3.
በመንግስት
መ/ቤቶች እና
በመንግስት ልማት
ድርጅቶች ውስጥ
ከባድ የሥነምግባር
መጣስ ስለመፈጸሙ
ጥቆማ ሲደርሰው
ወይም በቂ ጥርጣሬ
ሲኖረው የማጣራት
ወይም እንዲጣራ
የማድረግ እና
ተገቢው እርምጃ
እንዲወሰድ
የመከታተል፣ 4.
በመንግስት
መ/ቤቶች ወይም
በመንግስት ልማት
ድርጅቶች ወይም
ፌዴራል መንግስቱ
ለክልሎች ከሚሰጠው
ድጎማ ጋር በተያያዘ
በክልል መ/ቤቶች
በወንጀል ህግ እና
በሌሎች ሕጎች ውስጥ
የተመለከቱት
የሙስና ወንጀሎች
በመንግስት
ሰራተኞች ወይም
ባለስልጣኖች ወይም
በሌሎች ሰዎች
ስለመፈጸማቸው
ጥቆማ ሲደርሰው
ወይም በቂ ጥርጣሬ
ሲኖረው
የመመርመርና
የመክሰስ ወይም
እንዲመረመር ወይም
እንዲከሰስ
የማድረግ፣ 5.
ከሙስና
ወንጀል ጋር
በተያያዘ በቂ
ጥርጣሬ ሲኖረው በማናቸውም
ባንክ የሚገኝ
የተጠርጣሪዎች
የባንክ ሂሳብ
በኮሚሽነሩ ትእዛዝ
እንዲመረመር
የማድረግ፣ መረጃ
የማግኘት እና
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
በፍርድ ቤት ትእዛዝ
እንዲከበር
የማድረግ፣ 6.
ከሙስና
ወንጀል ጋር
በተያያዘ በምርመራ
ላይ ያሉ ሰዎች ሀብት
በፍርድ ቤት ትእዛዝ
እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ፣ በሙስና
ወንጀል የተገኘ
ለመሆኑ
የተረጋገጠን ወይም
በሙስና ወንጀሉ
ከተገኘው ጥቅም ጋር
ተመጣጣኝ የሆነ
ማናቸውንም ንብረት
ወይም ሀብት በፍርድ
ቤት ትእዛዝ
እንዲወረስና
በሐራጅ ተሸጦ ወይም
ሳይሸጥ ለመንግስት
ገቢ እንዲሆን
የማድረግ፣ 7.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር በህግ
በሚደነገገው
መሰረት የመንግስት
ባለስልጣኖችን እና
በህግ ሀብታቸውንና
የገንዘብ
ጥቅማቸውን
እንዲያስመዘግቡ
ግዴታ ያለባቸውን
የመንግስት
ሰራተኞች ሀብትና
የገንዘብ ጥቅሞች
መዝግቦ የመያዝ
ወይም ተመዝግበው
እንዲያዙ
የማድረግ፣ 8.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር ለሙስና
ወንጀል ጠቋሚዎችና
ምስክሮች የአካልና
የሥራ ዋስትና ጥበቃ
የሚሰጥበትን ሁኔታ
ማመቻቸት፣ በህግ
በሚወሰን መሰረት
ጥበቃ የመስጠት፣ 9.
ሙስናን
በመታገል እና
በመከላከል ረገድ
ጥሩ ውጤት ያስገኙ
ሰዎችን እና መ/ቤቶችን
አወዳድሮ ለሽልማት
የሚበቁበትን
ሥርአትና መለኪያ
የመዘርጋት፣
ሲጸድቅም ተግባራዊ
የማድረግ፣ 10.
የሕግ
አውጪና የዳኘነት
አካላትን ሳይጨምር
ለመንግስት መስሪያ
ቤቶችና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች
የሚያገለግሉ
የሥነምግባር
ደንቦች
መዘጋጀታቸውን
ማረጋገጥ ወይም
ማዘጋጀት እና
አፈጻጸማቸውን
የመከታተል፣ ከሕግ
አውጭ እና ከዳኝነት
አካላት ጥያቄ
ሲቀርብለት
በሥነምግባር ደንብ
አዘገጃጀት ረገድ
ምክር የመስጠት፣ 11.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር
የሥነምግባር
አውታሮችን
የማስተባበር፣ 12.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር የሥነምግባርን እና
ሙስናን በተመለከተ
ጥናትና ምርምር
የማድረግ እና
ተመሳሳይ ሥራዎችን
የመደገፍ፣
የኮሚሽኑን
አላማዎች ለማራመድ
የሚረዱ ሪፖርቶችን
እና ቴክኒካዊ
ጥናቶችን አሳትሞ
የማሰራጨት፣ 13.
አግባብነት
ካላቸው አካላት ጋር
በመተባበር የጸረ
ሙስና ህጎች
መከበራቸውን
የመከታተል እና
የማረጋገጥ
ስለአፈጻጸማቸው
የምክር አገልግሎት
የመስጠት፣ 14.
በመንግስት
መስሪያ ቤቶችና
የልማት ድርጅቶች
ውስጥ የስነምግባር
መከታተያ ክፍሎች
እንዲቋቋም ድጋፍ
የማድረግ፣ 15.
ለክልሎች
አስፈላጊውን
የምክርና የድጋፍ
አገልግሎት
የመስጠት፣ 16.
ተመሳሳይ
አላማ ካላቸው
አገራዊ፣
አህጉራዊና ዓለም
አቀፋዊ አካላት ጋር
ግንኙነትና ትብብር
የመፍጠር፣ 17.
የንብረት
ባለቤት የመሆን፣
ውል የመዋዋል፣
በራሱ ስም
የመክሰስና
የመከሰስ፣ 18.
በሕግ
የሚሰጡትን እና
ዓላማውን ከግብ
ለማድረስ የሚረዱ
ሌሎች ተግባራትን
የማከናወን፡፡ 8.
በሌሎች
አካላት ስለሚደረግ
የሙስና ወንጀል
ምርመራ 1.
ኮሚሽኑ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7
ንኡስ አንቀጽ 4
ከተሰጠው ሥልጣን
ውስጥ ከባድ ያልሆነ
የሙስና ወንጀልን
የመመርመር ጠቅላላ
ውክልና በሙሉ ወይም
በከፊል
እንደሁኔታው
ለፌዴራል ወይም
ለክልል የወንጀል
መርማሪ አካላት
ሊሰጥ ይችላል፡፡ 2.
በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 1 መሰረት
ውክልና ያልተሰጠው
ማንኛውም ወንጀልን
ለመመርመር ስልጣን
ያለው የፌዴራል
ወይም የክልል
መንግስታዊ አካል
በዚህ አዋጅ
በአንቀጽ 7 ንኡስ
አንቀጽ 4 በኮሚሽኑ
የስልጣን ክልል ስር
የሚወድቅ የሙስና
ወንጀል ለመፈጸሙ
ጥቆማ ሲደርሰው
ወይም በቂ ጥርጣሬ
ሲኖረው ምርመራ
መጀመር
ይኖርበታል፡፡
ሆኖም ስለተጀመረው
ምርመራ ለኮሚሽኑ
ሳይዘገይ
ያሳውቃል፡፡ 3.
በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 2
በተመለከተው
መሰረት ኮሚሽኑ
ሪፖርት ሲደርሰው ሀ.
ጉዳዩን እራሱ ወስዶ
ይመረምራል ወይም ለ.
ከባድ የሙስና
ወንጀልን ጨምሮ
ምርመራው ሪፖርት
ባደረገው የምርመራ
አካል ወይም በሌላ
አካል እንዲከናወን
ሊያደርግ
ይችላል፡፡ ዝርዝሩ
ኮሚሽኑ በሚያወጣው
መመሪያ
ይወሰናል፡፡ 4.
ኮሚሽኑ
በዚህ አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 2 መሰረት
በሚቀርብለት
ሪፖርት መሰረት
መልስ ሳይሰጥ ከቀረ
ምርመራውን
የጀመረው አካል
የተጀመረውን
ምርመራ በማጠናቀቅ
የምርመራ ፋይሉን
ክስ ለመመስረት
ስልጣን ላለው አካል
ያስተላልፋል፡፡ 5.
ኮሚሽኑ
በቀጥታ በሚደርሰው
ጥቆማ ወይም በሌላ
መልኩ በሚያገኘው
መረጃ መሰረት
የጀመራቸውን
የሙስና ወንጀል
ምርመራዎች በሌሎች
የምርመራ አካላት
እንዲመረመር
ሊያደርግ
ይችላል፡፡
ማንኛውም በዚህ
ንኡስ አንቀጽ
መሰረት የምርመራ
ፋይል የተላለፈለት
አካል ምርመራውን
ማከናወን
ይኖርበታል፡፡ 6.
በዚህ
አንቀጽ ከንኡስ
አንቀጽ 2 እስከ 5
በተመለከተው
መሰረት በሌሎች
የምርመራ አካላት
ስለሚከናወኑ
የሙስና ወንጀል
ምርመራዎች ሪፖርት
ስለሚደረግበት
ሁኔታ ኮሚሽኑ
ዝርዝር መመሪያ
ያወጣል፣
ለሚመለከታቸው
የምርመራ አካላት
ያሳውቃል፡፡ 9. በሌሎች የፍትህ አካላት የሙስና ወንጀል ክስ ስለመመስረት 1.
ኮሚሽኑ
ከአቃቤ ህግነት
ስልጣኑ ውስጥ
አግባብነት ላለው
የፌዴራል ወይም
የክልል አቃቤ ህግ
ወይም
የስነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋም
በሙሉ ወይም በከፊል
ውክልና ሊሰጥ
ይችላል፡፡ 2.
ከፌዴራል መንግስት
ለክልል መንግስታት
ከተሰጠ የበጀት
ድጎማ ጋር በተያያዘ
የክልል
የስነምግባርና ጸረ
ሙስና ተቋም ወይም
ስልጣን ያለው አቃቤ
ህግ ክስ መመስረት
ይችላል፡፡ ሆኖም
ኮሚሽኑ አስፈላጊ
ሆኖ ካገኘው
በማንኛውም ጊዜ
የክልሉን
የስነምግባርና ጸረ
ሙስና ተቋም ወይም
አቃቤ ህግ በመተካት
በክርክሩ ውስጥ
ሊገባ ይችላል፡፡ 10.
የኮሚሽኑ
አቋም ኮሚሽኑ፣ 1.
በጠቅላይ
ሚኒስትሩ
አቅራቢነት
በተወካዮች ምክር
ቤት የሚሾም አንድ
ኮሚሽነር 2.
በጠቅላይ
ሚኒስትሩ የሚሾም
አንድ ምክትል
ኮሚሽነር፣ እና 3.
ለስራው
አስፈላጊ የሆኑ
ሰራተኞች፣
ይኖሩታል፡፡ የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ ሙያዊ ነጻነቱን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ነጻ ሆኖ ይደራጃል፡፡ 1.
ኮሚሽነሩ
የኮሚሽኑ ዋና ሥራ
አስፈጻሚ በመሆን
የኮሚሽኑን ስራዎች
ያደራጃል፣
ይመራል፣
ያስተዳድራል፡፡ 2.
የዚህ
አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ /1/ አነጋገር
እንደተጠበቀ ሆኖ
ኮሚሽነሩ፣ ሀ.
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7
የተዘረዘሩትን
የኮሚሽኑን
ሥልጣንና ተግባራት
በሥራ ላይ ያውላል፣ ለ.
በዚህ አዋጅ
በተመለከተው
መሰረት እና
የፌዴራል ሲቪል
ሰርቪስ ሕግ
አጠቃላይ
መርሆዎችን መሠረት
በማድረግ በሚወጣው
የአስተዳደር ደንብ
መሠረት የኮሚሽኑን
ሠራተኞች
ይቀጥራል፣
ያስተዳድራል፣
ያሰናብታል፡፡ ሐ.
ኮሚሽነሩ በዚህ
ህግ የተመለከቱትን
ድንጋጌዎች፣
የፌዴራል ሲቪል
ሰርቪስ ሕግ
አጠቃላይ
መርሆዎችን መሰረት
በማድረግ
የኮሚሽኑን
የአስተዳደር ደንብ
አዘጋጅቶ ለጠቅላይ
ሚኒስትሩ
ያቀርባል፣
ሲፈቀድም በስራ ላይ
ያውላል፡፡ መ.
የኮሚሽኑን ዓመታዊ
የሥራ ፕሮግራም እና
በጀት አዘጋጅቶ
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ
ያቀርባል፣
ሲፈቀድም በስራ ላይ
ያውላል፡፡ ሠ.
ለኮሚሽኑ
በተፈቀደለት በጀት
እና ባዘጋጀው የስራ
ፕሮግራም መሰረት
የፋይናንስ ሕግን
ተከትሎ ገንዘብ ወጪ
ያደርጋል፡፡ ረ.
በሙስና ወንጀል
የተጠረጠሩ ሰዎችን
የኮሚሽኑ ሰራተኞች
በህግ መሰረት
ለመመርመር፣
ለመክሰስ ወይም
ለማሰር እንዲችሉ
ሥልጣን ይሰጣል፡፡ ሰ.
ምርመራው
በመከናወን ላይ ላለ
ጉዳይ አግባብነት
ያለው በሆነ ጊዜ
የማንኛውም ሰው
ወይም ድርጅት
የባንክ ሂሳብ
እንዲፈተሽ እና
አስፈላጊው መረጃ
እንዲሰበሰብ
ትእዛዝ ለመስጠት
ይችላል፡፡ ሸ.
ኮሚሽኑ ከሦሰተኛ
ወገኖች ጋር
በሚያደርጋቸው
ግንኙነቶች
ኮሚሽኑን
ይወክላል፡፡ ቀ.
የኮሚሽኑን ጠቅላላ
የስራ አፈጻጸምና
የሂሳብ ሪፖርት
አዘጋጅቶ ለጠቅላይ
ሚኒስትሩ
ያቀርባል፡፡ 3.
ኮሚሽነሩ
ለኮሚሽኑ ሥራ
ቅልጥፍና
በሚያስፈልግ መጠን
ሥልጣንና ተግባሩን
በከፊል ለኮሚሽኑ
ኃላፊዎች እና
ሠራተኞች በውክልና
ሊያስተላልፍ
ይችላል፡፡ 1.
ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ሀ.
የኮሚሽኑን
ተግባሮች በማቀድ፣
በማደራጀት፣
በመምራትና
በማስተባበር
ኮሚሽነሩን
ይረዳል፡፡
ሐ.
ኮሚሽነሩ
በማይኖርበት ጊዜ
እሱን ተክቶ
ይሰራል፡፡
2.
ምክትል ኮሚሽነሩ
ተጠሪነቱ
ለኮሚሽነሩ
ይሆናል፡፡
14.
የኮሚሽነሩና
የምክትል ኮሚሽነሩ
የሥራ ዘመንና
ከሥራ መነሳት 1.
የኮሚሽነሩና
የምክትል ኮሚሽነሩ
የሹመት ዘመን ለ6
አመት ይሆናል፣
ሆኖም አስፈላጊ
ሲሆን እንደገና
ሊሾም ይችላል፡፡ 2.
ኮሚሽነሩ ወይም
ምክትል ኮሚሽነሩ
ከዚህ በታች
በተመለከቱት
ሁኔታዎች ካልሆነ
በስተቀር
የተሾመበት የስራ
ዘመን ከማለቁ በፊት
ከፈቃዱ ውጭ ከስራው
አይነሳም፣
ሐ.
በህመም ምክንያት
ተግባሩን በተገቢው
ሁኔታ ማከናወን
የማይችል ሆኖ
ሲገኝ፣ የኮሚሽኑ ሰራተኞች የቅጥር፣ አስተዳደርና ስንብት ሁኔታ በዚህ አዋጅ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችና የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን አጠቃላይ መርሆዎች መሠረት በማድረግ በሚወጣው የአስተዳደር ደንብ መሠረት ይሆናል፡፡ 16.
ቃለመሀላ
ስለመፈጸም በኮሚሽኑ የተቀጠረ ማንኛውም ሰራተኛ ለፌዴራሉ ህገመንግስት ታማኝ በመሆን የተጣለበትን ህዝባዊ አደራና ሙያዊ ሀላፊነት ለመወጣት ቃለመሀላ ይፈጽማል፡፡ የቃለመሀላው ዝርዝር ይዘት በአስተዳደር ደንቡ ይወሰናል፡፡ 17.
የኮሚሽኑ
ሰራተኛ መብት 1.
ማንኛውም
የኮሚሽኑ ሰራተኛ
በመንግስት
በሚጸድቅ የደመወዝ
ስኬል መሰረት
ደመወዝ ያገኛል፡፡ 2.
የማንኛውም
ሰራተኛ ደመወዝ፣
ሐ.
በህግ በተደነገገው መሰረት
ካልሆነ በስተቀር
ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ
አይችልም፡፡ 3.
በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 2/ለ/ ወይም /ሐ/
መሰረት ከሰራተኛ
ደመወዝ በየወሩ
የሚቆረጠው
ከደመወዙ አንድ
ሶስተኛ
አይበልጥም፡፡ 4.
ማንኛውም
የኮሚሽኑ ቋሚ
ሰራተኛ በጡረታ ሕግ
መሰረት የጡረታ
መብት ይኖረዋል፡፡ 5.
የኮሚሽኑ
ሰራተኛ፣
ሐ.
በአስተዳደር ደንቡ
በሚወሰን መሰረት
ይግባኝ የማቅረብ
መብት ይኖረዋል፡፡
ሠ.
<<ጊዜያዊ ሰራተኛ
ከሆነና የደረሰው
ጉዳት ዘላቂ ከፊል
የመስራት ችሎታ
ማጣት ከሆነ
የሚከፈለው የጉዳት
ካሳ መጠን በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 5/መ/
በተመለከተው ክፍያ
ላይ የተመሰረተ ሆኖ
ከመስራት ችሎታ
ማጣቱ ደረጃ ጋር
ተመጣጣኝ
ይሆናል፡፡ ረ.
<<የደረሰበት ጉዳት
ከባድ የአካል ወይም
የመልክ መበላሸትን
ያደረሰ ከሆነ
የመስራት ችሎታ
ማጣትን
ባያስከትልም ለዚህ
አንቀጽ ድንጋጌዎች
አፈጻጸም
እንደዘላቂ ከፊል
የመስራት ችሎታ
ማጣት ይቆጠራል፡፡ >>
ሰ.
በትርፍ ጊዜው
ከስራው ጋር የጥቅም
ግጭት በማይፈጥር
ስራ ላይ መስሪያ
ቤቱን በማሳወቅ
ለመስራት
ይችላል፡፡ ዝርዝሩ
ኮሚሽኑ በሚያወጣው
መመሪያ መሰረት
ይወሰናል፡፡ 18.
ከግብር
ነጻ ስለመሆን በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከፈል የጡረታ አበል ወይም የጉዳት ካሳ ክፍያ ከግብር ነጻ ይሆናል፡፡ እንዲሁም በእዳ ሊከበር ወይም በማቻቻያነት ሊቀነስ ወይም ባለመብቱ ሊያስተላልፈው አይችልም፡፡ 19.
ከስራ
ስለማገድ 1.
የኮሚሽኑ
ሰራተኛ ከስራ ታግዶ
መቆየት ለስራው
አፈጻጸም ጠቃሚ ሆኖ
ከተገኘ ሰራተኛውን
ከአንድ ወር
ለማይበልጥ ጊዜ
ከስራና ከደመወዝ
አግዶ ለማቆየት
ይቻላል፡፡ 2.
የኮሚሽኑ ሰራተኛ
በወንጀል ወይም
በዲሲፕሊን ጥፋት
በህግ የተከሰሰ
እንደሆነና
ሲመሰከርበት ጥፋቱ
ከስራው
የሚያስወጣው መሆኑ
ሲገመት ከስራ ታግዶ
መቆየት አለበት፡፡ 20.
ስለይርጋ
ጊዜ 1.
ቀላል
የዲሲፕሊን ቅጣት
የሚያስከትል ጥፋት
የፈጸመ የኮሚሽኑ
ሰራተኛ
የምርመራውን ጊዜ
ሳይጨምር የፈጸመው
ጥፋት ከታወቀበት
ቀን ጀምሮ እስከ
ስድስት ወር እርምጃ
ካልተወሰደበት
በዲሲፕሊን ተጠያቂ
አይሆንም፡፡ 2.
ከባድ
የዲሲፕሊን ቅጣት
የሚያስከትል ጥፋት
የፈጸመ የኮሚሽኑ
ሰራተኛ የፈጸመው
ጥፋት ከታወቀበት
ቀን ጀምሮ በአንድ
አመት ጊዜ ውስጥ
በጥፋቱ ካልተከሰሰ
በዲሲፕሊን ተጠያቂ
አይሆንም፡፡ 3.
በዚህ
አንቀጽ ንኡስ
አንቀጽ 1 ወይም 2
በተመለከተው የጊዜ
ገደብ ውስጥ መወሰድ
የሚገባውን
የዲሲፕሊን እርምጃ
ሳይወስደው የቀረው
ሃላፊ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡ 21.
በጀት የኮሚሽኑ
በጀት በመንግስት
ይመደባል፡፡ 22.
የሂሳብ
መዛግብት 1.
ኮሚሽኑ
የተሟሉ እና
ትክክለኛ የሂሳብ
መዛግብት
ይይዛል፡፡ 2.
የኮሚሽኑ
የሂሳብ መዛግብት
እና ገንዘብ ነክ
ሰነዶች በፌዴራሉ
ዋና ኦዲተር
በየዓመቱ
ይመረመራል፡፡ ክፍል
ሶስት
ልዩ ልዩ
ድንጋጌዎች 23.
ስለኮሚሽኑ
የፖሊስነትና
የዐቃቤ ህግነት
ሥልጣን ስለመመርመርና
ስለመክሰስ
በወንጀለኛ መቅጫ
ሕግ ሥነሥርአትና
በሌሎች ሕጎች
ለፖሊስና ለዐቃቤ
ህግ የተሰጠ ሥልጣን
በዚህ አዋጅ ውስጥ
የተመለከቱ
ጉዳዮችን
በሚመለከት
ለኮሚሽኑ
ተሰጥቶአል፡፡ 1.
በየደረጃው
በሚገኙ የመንግስት
መሥሪያ ቤቶች እና ልማት ድርጅቶች
ውስጥ የሥነ ምግባር
ሁኔታን
የሚያስተባብሩ እና
ለየመስሪያ ቤቶቹ
የበላይ ኃላፊዎች
የሚያማክሩ
የሥነምግባር
መከታተያ ክፍሎች
ይቋቋማሉ፡፡ 2.
የሥነምግባር
መከታተያ ክፍል
ተጠሪነቱ
ለመንግስት መሥሪያ
ቤቱ ወይም
ለልማት
ድርጅቱ የበላይ
ሀላፊ ይሆናል፡፡ 3.
የስነምግባር
መከታተያ ክፍል
ሀላፊ ወይም
ሰራተኛን የመስሪያ
ቤቱ የበላይ ሀላፊ
በቅጥር፣ በእድገት
ወይም በዝውውር
ይመድባል፣ ለስራ
መደቡ
የሚያስፈልገውን
የትምህርትና የስራ
ልምድ እንዲሁም
የስነምግባር ሁኔታ
በሚመለከት
ከኮሚሽኑ ጋር
በመመካከር
ይወስናል፡፡ 4.
የስነምግባር
መከታተያ ክፍሉ
ከኮሚሽኑ ጋር
የሚኖረውን የስራ
ግንኙነት
በሚመለከት
በዝርዝር በደንብ
ይወሰናል፡፡ 25.
በኮሚሽኑና
በክልል ተቋሞች
መካከል ስለሚኖረው
የስራ ግንኙነት 1.
ሙስናን
መሸከም የማይችል
ህብረተሰብ
በመፍጠር እንዲሁም
ሙስናን
በመከላከል፣
በመመርመርና
በመክሰስ ኮሚሽኑ
ከክልል
የሥነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋሞች
ጋር በቅንጅትና
በተደጋጋፊነት
ይሰራል፡፡ 2.
የክልል
መስሪያ ቤቶች
በኮሚሽኑ
በሚሰጣቸው ውክልና
መሰረት የሙስና
ወንጀል ጉዳዮችን
ሲመረምሩና ሲከሱ
ተጠሪነታቸው
ለኮሚሽኑ
ይሆናል፡፡ 3.
ኮሚሽኑና
የክልል
የሥነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋሞች
ለጸረ ሙስና
እንቅስቃሴው ስኬት
በጋራ
ለሚያከናውኗቸው
ተግባራትና
የሚያከናውኗቸውን
ተግባራት አፈጻጸም
ለመገምገም
የሚወያዩበት የጋራ
ጉባኤ ሊያቋቁሙ
ይችላሉ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር
የጋራ ጉባኤውን
ይመራል፡፡ የጋራ
ጉባኤው፣
ሀ.
የጋራ የአሰራር
ውስጠ ደንብ
ያወጣል፡፡
ለ.
ሙስናን
በመከላከልና
በመመርመር
እንዲሁም መልካም
ስነምግባርን
በማስፈን የስራ
እንቅስቃሴዎችን
በመገምገም የልምድ
ልውውጥ
ያደርጋል፡፡
ሐ.
ስልጠናን
በሚመለከት የጋራ
አቅጣጫዎችን
ይቀይሳል፡፡
መ.
በኮሚሽኑ ወይም
በክልል
የሥነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋሞች
በሚቀርቡ ጥናቶች
ላይ ይወያያል፣
በጥናቶቹ መሰረት
ሊወሰዱ የሚገባቸው
እርምጃዎች
እንዲወሰኑ
ለሚመለከተው አካል
ያቀርባል፣
እንደሁኔታው
ይወስናል፣ በስራ
ላይ መዋላቸውን
ያረጋግጣል፡፡ 4.
ኮሚሽኑና
የክልል
የሥነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋሞች
የጋራ ጉባኤ
ያስተላለፋቸውን
ውሳኔዎች
መተግበራቸውን
በየበኩላቸው
ይከታተላሉ፡፡ 5.
የክልል
የሥነምግባርና
የጸረ ሙስና ተቋሞች
በክልላቸው ስላለው
የሙስና ወንጀል
ሁኔታ በሚመለከት
ሪፖርትና
ስታቲስቲክስ
በየጊዜው ለኮሚሽኑ
ያስተላልፋሉ፡፡ 26.
የሙስና
ወንጀልን
የማስታወቅና
የመተባበር ግዴታ 1.
የመንግስት
መስሪያ ቤቶችና
የመንግስት የልማት
ድርጅቶች በራሳቸው
የሚወስዱት
የአስተዳደር ወይም
የዲሲፕሊን እርምጃ
እንደተጠበቀ ሆኖ
ከባድ የስነምግባር
መጣስና የሙስና
ወንጀል የተፈጸመ
ለመሆኑ ጥርጣሬ
ሲኖራቸው ወዲያውኑ
ለኮሚሽኑ ወይም
ስልጣን ላለው
የምርመራ አካል
ሪፖርት የማድረግ
ግዴታ አለባቸው፡፡ 2.
ማንኛውም
የመንግስት
ባለስልጣን ወይም
የመንግስት ሰራተኛ
በመስሪያ ቤቱ
የሙስና ወንጀል
ተፈጽሞአል ወይም
ሊፈጸም በዝግጅት
ላይ ነው ብሎ
በሚጠረጥርበት ጊዜ
ለኮሚሽኑ ወይም
ስልጣን ላለው
የምርመራ አካል
የማስታወቅ ግዴታ
አለበት፡፡ 3.
ማንኛውም
ሰው ከኮሚሽኑ
ሥልጣንና ተግባር
ጋር በተያያዘ
ለሚጠየቀው
ትብብርና ድጋፍ
የመተባበር ግዴታ
አለበት፡፡
በተለይም ኮሚሽኑ
የሙያ ድጋፍን
በሚመለከት
ለሚያቀርባቸው
ጥያቄዎች
አግባብነት ያላቸው
የመንግስት መስሪያ
ቤቶችና የልማት
ድርጅቶች
አስፈላጊውን ድጋፍ
መስጠት
ይኖርባቸዋል፡፡ 4.
በዚህ
አዋጅ መሰረት
የሙስና ወንጀልን
ለመመርመር ስልጣን
ያለው ማንኛውም
መርማሪ
በማንኛውም ጊዜ
በፌዴራል ሆነ
በክልል የመንግስት
መስሪያ ቤት ወይም
የልማት ድርጅት
በመገኘት ለምርመራ
ስራው አግባብነት
ያላቸውን መረጃዎች
እንዲሰጠው ወይም
እንዲመለከት
መጠየቅ ይችላል፡፡
በማንኛውም
በፌዴራሉም ሆነ
በክልል የመንግስት
መስሪያ ቤት ወይም
የልማት ድርጅት ያለ
ሀላፊ ወይም ሰራተኛ
የሙስና ወንጀልን
ለመመርመር ስልጣን
ባለው መርማሪ
ሲጠየቅ
አስፈላጊውን መረጃ
የማሳየት ወይም
የማቅረብ ግዴታ
አለበት፡፡ 27.
ቅጣት በሌላ
ህግ የበለጠ
የሚያስቀጣ ካልሆነ
በስተቀር፣ 1.
ማንኛውም
ሰው ለኮሚሽኑ፣
ለፍትህ አካላት
ወይም ለመንግስት
መስሪያ ቤት ኃላፊ
ወይም
የመንግስት
ልማት ድርጅት ኃላፊ
ከሙስና ወንጀል ጋር
በተያያዘ መረጃ
ወይም ማስረጃ በሰጠ
ሰው ላይ ተጽእኖ
ለማድረግ ወይም
ጉዳት ለማድረስ
የሞከረ ወይም
ያደረሰ ወይም
ይህንኑ ሰው
ለመቅጣት የሞከረ
ወይም የቀጣ
እንደሆነ ከሶስት
አመት በማያንስ፣
ከአስራ አምስት
አመት በማይበልጥ
ጽኑ እስራት እና
ከስድስት ሺህ ብር
በማያንስ ከሃያ
አምስት ሺህ ብር
በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ 2.
ማንኛውም
የኮሚሽኑ ሀላፊ
ወይም ሰራተኛ በህግ
የተሰጠውን
ስልጣንና ሃላፊነት
ያለአግባብ
የተገለገለበት
እንደሆነ በዚያም
የተነሳ ያገኘው
ጥቅም መወረሱ
እንደተጠበቀ ሆኖ
ከአምስት አመት
በማያንስ ከአስራ
አምስት አመት
በማይበልጥ ጽኑ
እስራትና ከሶስት
ሺህ ብር በማያንስ
ከአስር ሺህ ብር
በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ 3.
ማንኛውም
ሰው ሆን ብሎ
ኮሚሽኑን ለማሳሳት
ወይም ሌላውን ሰው
ለመጉዳት ሐሰተኛ
ሪፖርት፣ ጥቆማ
ወይም መረጃ
ለኮሚሽኑ ያቀረበ
እንደሆነ ከአንድ
ዓመት በማያንስ
ከአምስት አመት
በማይበልጥ ጽኑ
እስራትና ከሶስት
ሺህ ብር በማያንስ
ከአስር ሺህ ብር
በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ 4.
ማንኛውም
ሰው የኮሚሽኑ
ሰራተኛ መስሎ
በመቅረብ የማታለል
ስራ የፈጸመ
እንደሆነ ከሶስት
አመት በማያንስ
ከአስር አመት
በማይበልጥ ጽኑ
እስራት እና
ከአምስት ሺህ ብር
በማያንስ ከአስራ
አምስት ሺህ ብር
በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ 5.
ማንኛውም
ሰው በዚህ አዋጅ
በአንቀጽ 26 ንኡስ
አንቀጽ 3 ወይም 4
በተደነገገው
መሰረት ኮሚሽኑን
ለመተባበር
እምቢተኛ የሆነ
እንደሆነ ከስድስት
ወር በማያንስ
ከአራት አመት
በማይበልጥ እስራት
እና ከአንድ ሺህ ብር
በማያንስ ከአምስት
ሺህ ብር በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ 6.
ማንኛውም
ሰው የኮሚሽኑን ሥራ
ያደናቀፈ ወይም
ለማደናቀፍ የሞከረ
እንደሆነ ከሁለት
አመት በማያንስ
ከአስር አመት
በማይበልጥ ጽኑ
እስራት እና
ከአምስት ሺህ ብር
በማያንስ ከሃያ ሺህ
ብር በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል፡፡ ወንጀሉ
የተፈጸመው ኃይልን
በመጠቀም የሆነ
እንደሆነ ቅጣቱ
በዚሁ ንዑስ አንቀጽ
የተደነገገው
ከፍተኛ ቅጣት
ይሆናል፡፡ 7.
የሙስና
ወንጀል ምርመራ
ሊጀመር ስለመሆኑ
ወይም በምርመራ ላይ
ስለመሆኑ ወይም
ጉዳዩ በምርመራ ላይ
መሆኑን እያወቀ
ስለተፈጸመው
ድርጊት ምርመራውን
ከያዘው ክፍል ፈቃድ
ውጭ መግለጽ፣
መጻፍ፣ ማሰራጨት
ከስድስት ወር
በማያንስ ከአራት
አመት በማይበልጥ
እስራት እና ከአንድ
ሺህ ብር በማያንስ
ከአምስት ሺህ ብር
በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ
ያስቀጣል፡፡ 8.
ማንኛውም
የመንግስት
ባለስልጣን ወይም
የመንግስት ሰራተኛ
በሚሰራበት መስሪያ
ቤት የሙስና ወንጀል
ስለመፈጸሙ እያወቀ
ሳያሳውቅ መቅረት
እስከ አምስት አመት
ቀላል እስራትና
እስከ አስር ሺህ ብር
መቀጮ ያስቀጣል፡፡ 9.
በዚህ
አንቀጽ በንኡስ
አንቀጽ 1፣3፣4፣5፣
እና 6 የተመለከቱት
ወንጀሎች በወንጀል
ህግ መሰረት ተጠያቂ
በሚሆን የሕግ
ሰውነት ባለው
ድርጅት በተፈጸሙ
ጊዜ የገንዘብ ቅጣቱ
አምስት እጥፍ
ይሆናል፡፡ 28.
የመሸጋገሪያ
ድንጋጌ አዋጅ ቁ 235/93 በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ተፈጽመው ምርመራቸው በሌሎች አካላት በጅምር ወይም በሂደት ላይ ያለም ሆነ የተጠናቀቁ ወይም በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉ የሙስና እና ከሙስና ጋር የተያያዙ የወንጀል ጉዳዮች በነበሩበት ሁኔታ ቀጥለው ውሳኔ ያገኛሉ፡፡ 1.
የፌዴራል
የስነምግባርና
የጸረሙስና ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 235/1993
በዚህ አዋጅ
ተሽሯል፡፡ 2.
ከዚህ
አዋጅ ጋር የሚቃረኑ
ማናቸውም ሌሎች
ሕጎች በዚህ አዋጅ
ውስጥ በተሸፈኑ
ጉዳዮች ላይ
ተፈጻሚነት
አይኖራቸውም፡፡ 1.
የሚኒስትሮች
ምክር ቤት ለዚህ
አዋጅ አፈጻጸም
ደንብ ሊያወጣ
ይችላል፡፡ 2.
ኮሚሽኑ
ይህንን አዋጅና
በዚህ አዋጅ መሰረት
የሚወጣውን ደንብ
ለማስፈጸም መመሪያ
ሊያወጣ ይችላል፡፡ 31.
አዋጁ
የሚጸናበት ጊዜ ይህ
አዋጅ ከጥር
25 ቀን
1997 ዓ.ም
ጀምሮ የጸና
ይሆናል፡፡ አዲስ
አበባ ከጥር
25 ቀን 1997 ግርማ
ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ
ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት
|
|||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||