News
The profile of the FEAC
Major objectives of FEAC
Amendment of the Proclamation
The revised establishment proclamation
The revised procedural proclamation
Directives and regulations
Principles and values
Annual Report
Publications
Vacancies
Contact Us
  proclamation pdf

የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር

ሁሉ ቢያብር ሙስናን ያስር

በአገራችን የፀረ-ሙስና ተቋማት ትብብር

የሙስና ቅኝት

  የሙስና ምንነት  

  የሙስና መገለጫዎች

  የሙስና መንስዔች

  yÑSÂ g#ÄèC  

  ሙስናን የመዋጊያ መንገዶች  

  ማጠቃለያ  

የሙስና ቅኝት በኢትዮጵያ  

  የቤተሰብ ቅኝት  

  የንግድ አካባቢ ቅኝት  

  የመንግሥት ባለሥልጣናት ቅኝት

  የመፍትሄ ሃሳቦች  

ለልጆች መልካም ሥነምግባር የወላጆች ሚና  

ግዴታን ይወጡ መብትን ያስከብሩ  

የሙስና ጉዳቶች  

የሥነምግባር መኮንኖች 

      ሥነምግባር መኮንን ተግባርና ኃላፊነት  

     ተጠሪነት  

በቤተሰብ ውስጥ ሊተገበሩ የሚገቡ የመልካም ዕሴቶች መገለጫዎች

   የቤተሰብን አቅምና ችግር መረዳት  

   ቤተሰብን በሥራ ማገዝ  

   ለቤተሰብ አባላት ተገቢውን ከበሬታ መስጠት  

   ማጠቃለያ  

ሙስናን የመከላከያ ስልቶች  

   ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት  

    ጠንካራ ሕግና አስፈፃሚ አካል እንዲኖር ማድረግ  

    የተጠያቂነት አሠራርን መዘርጋት  

    የሥነምግባር ደንብ ማዘጋጀት  

    ሥነምግባርን የሥራ አካል ማድረግ  

    ለሥራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር  

    የሥነምግባር መከታታያ ማዕከል ማቋቋም  

    ጠንካራ የሲቪል ማኅበረሰብ መፍጠር  

    ማጠቃለያ  

መብትን በገንዘብ አይግዙ  

የጥቅም ግጭትና ማስወገጃ መንገዶች  

ሦስት ዋና ዋና የጥቅም ግጭት መከሰቻ መንገዶች ይታወቃሉ  

      የውጭ ሥራ / Out side Employment   

      የገንዘብ ጥቅም / Financial Interest  

     ምድናመሥራት / Nepotism  

      የጥቅም ግጭት ማስወገጃ መንገዶች  

የመንግሥት ንብረት የሕዝብ ንብረት ነው  

የጥቆማ አቀራረብ ሥርዓት 

   ጠቋሚ ማን ነው?  

   ጠቋሚ የሚጠቁመው ምንድን ነው?  

   ከጠቋሚው የሚጠበቁ ነገሮች ምንድን ናቸው?  

   ጥቆማ እንዴት ይቀርባል?  

   ጠቋሚው ጥቆማውን ለኮሚሽኑ በምን መንገድ ሊያቀርብ ይችላል?  

   ከኃላፊነት ነፃ መሆን ማለትስ ምን ማለት ነው?  

   ጥቆማ ለመስጠት በሚከተሉት አድራሻዎች መጠቀም ይቻላል   

የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር

በመልማት ላይ ያሉ ሀገሮች የልማት ውጥን ለስኬት ለመብቃት ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የፋይናንስ እጥረት የፍላጐታቸውን ያህል በልማቱ ወማፊት ለመግፋት አያስችላቸውም፡፡ የአቅምን ያህል እያዘገሙ፣ ደግሞ ለዘመናት ሥር የሰደደውን ድህነት ለመቀነስም ሆነ ለማስወገድ አይታሰብም፡፡

በአንፃሩ ድሀ ሀገሮች ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ ከድህነት መውጣት ካልቻሉ፣ በአጭር ጊዜ የህዝቦቻቸውን የኑሮ ደረጃ ከፍፁም ድህነት ካልታደጉ መጪው ዕድላቸው አስፈሪ መሆኑ በብዙ ወገኖች የታመነበት እውነት ሆኗል፡፡

ይህም በመሆኑ በመልማት ላይ ያሉ ሀገሮች ከምንም በላይ ለልማት ቅድሚያ በመስጠት ድህነትን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን ሥልት ቀይሰዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መላው ዓለም ከጐናቸው ቆሟለ፡፡ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ተግባራዊ ለማድረግ የበለፀጉትም ሆነ ድሀ ሀገሮች በጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ይህ የልማት ፍላጐት እና ከድህነት የመውጣት ቁርጠኝነት ድህነትን ለማስወገድ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡ መንግሥታትም ሆኑ የሀገሮች መሪዎች በዚህ በኩል የመሪነት ድርሻቸውን ከተወጡ ህዝቦቻቸውን ለልማት ማነሳሳት፣ ለሀገር ዕድገት እና ብልፅግና ማሰለፍ አይሳናቸውም፡፡

በዚህ ምክንያት ብዙ ሀገሮች የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት ፊታቸውን ወደ ልማት አዙረዋል፡፡ ያላቸውን የተወሰነ የፋይናንስ አቅም በአግባቡ በመጠቀም መልማት እና ማደግ እንደሚቻል የሚያመላክት ውጤት አግኝተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የድሀ ሀገሮችን የልማት ጥያቄ የሚፈታተነው የፋይናንስ እጥረት ብቻ አይደለም፡፡ በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖሩ፣ የቴክኖሎጂ ኋላ ቀርነቱ... ከዚሁ ጋር ተያይዘው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች የድሀ ሀገሮችን የዕድገት እሩጫ በመግታት፣ የልማት ጉዞአቸውን ለማሰናከል ያላቸው ድርሻ ቀላል አይደለም፡፡

ነገር ግን ድሀ ሀገሮች ከፋይናንስ እጥረት፣ ከሰለጠነ የሰው ኃይል እጦት እና ከቴክኖሎጂ ኀኁላቀርነት... በተጨማሪ ሌሎች የፀረ-ድህነት ትግላቸውን ውጤት አልባ የሚያደርጉ ጠላቶች አሏቸው፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሥነምግባር ጉድለት እና ሙስና በዚህ በኩል ቅድሚያውን ይይዛሉ፡፡

እንደሚታወቀው መልካም አስተዳደር በጠፋበት እና ሙስና በተስፋፋበት ሁኔታ ልማት ይኖራል ተብሎ አይታመንም፡፡ ይህን አብዛኞቹ ድሀ ሀገሮች በተግባር አይተውታል፡፡ ሙስና ምን ያህል ወደ ኋላ እንዳስቀራቸው እና ድህነታቸውን በማባባስ የዕድገት ጉዟቸውን እንዳሰናከለባቸው ዛሬ ያሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ምስክር ነው፡፡

በእርግጥም ድሀ ሀገሮች ካለባቸው የፋይናንስ እጥረት በላይ ሙስና ብዙ ጉዳት አድርሶባቸዋል፡፡ ካላቸው ውስን በጀት ላይ እየተዘረፈ ወደ ግል ኪስ የሚገባው ገንዘብ ድህነታቸውን በማባባስ ጉዳት ላይ ጥሏቸዋል፡፡

በዚህም የተነሳ ዛሬ ሙስናን መዋጋት ያልቻለ ሀገር ከድህነት ለመውጣት በሚያደርገው ጉዞ ስኬት አልባ መሆኑ ገሀድ ሆኗል፡፡ ድሀ ሀገሮችም ሙስናን መቆጣጠር ከተሳናቸው የኢኮኖሚ እድገት፣ ልማት እና ብልፅግና ህልም ሆነው እንደሚቀሩ ተገንዝበዋል፡፡

ይህም እንደየሀገሮቻቸው ተጨባጭ ሁኔታ የፀረ-ሙስና ተቋማትን እንዲያቋቁሙ እና በሙስና ላይ ጠንከር ያለ ክትትል እና እርምጃ እንዲወስዱ አነሳስቷቸዋል፡፡ 

በሀገራችንም ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷል፡፡ ሙስና ልማትን ማደናቀፉ፣ ኢኮኖሚን ማዳከሙ፣ የህብረተሰቡን ጠቃሚ እሴቶችና ሞራል መጉዳቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የሥነምግባር እና የፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ተቋቁሟል፡፡

ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላም በሙስና የተዘፈቁ፣ የግል ጥቅማቸውን አስቀድመው የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ የዘነጉ ግለሰቦችን ጉዳይ በመመርመር፣ በማጣራት እና በመክሰስ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሙስናን መሸከም የማይችል ህብረተሰብ ለመገንባት የሥነምግባር ትምህርት በመስጠት ላይ ነው፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ የሚታዩ የሥነምግባር ጉድለቶችን እና የሙስና ድርጊቶችን ለመከታተል የሚያስችሉ ክፍሎችም ተከፍተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ሰሞኑን ደግሞ ዘንድሮ ከግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለሚመረቁ ከአምስት ሺ በላይ ተማሪዎች በሥነምግባርና በፀረ-ሙስና ላይ ያተኮረ ትምህርት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

ይህ ስልጠና ተመራቂዎቹ ወደ ሥራ ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት ስለ ሥነምግባርና ስለ ፀረ-ሙስና ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ በኩል ድርሻ ይኖረዋል፡፡ እራሳቸውን ከሙስና ድርጊት አርቀው ሥራቸውን በሥነምግባር ለማከናወንም ያግዛቸውዋል፡፡ ይህን መሰሉ ስልጠና ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና ለከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች መሰጠቱም በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል፡፡

በኮሚሽኑ የሚሰጠው የሥነምግባር ትምህርት ..ሲሾም ያልበላ..... የሚለውን አፍራሽ መልዕክት ያዘለ ተረት እየሰማ ያደገው ወጣት ትውልድ ላይ ማተኮሩም ጠቀሜታው የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙስናን የሚዋጋ፣ ጠንካራ የፀረ-ሙስና አቋም ያለው እና በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ ለሀገሩ ኢኮኖሚ እድገት የላቀ ድርሻ አለው፡፡ በመሆኑም ልማትን ለማፋጠን ድህነትን ለማቀነስ እና ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ እርከን ለመሸጋገር ሙስናን የመከላከሉ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ሁሉ ቢያብር ሙስናን ያስር

ከቤቴል (Ø..)

 የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በአዋጅ ተቋቁሞ ሥራ ሲጀምር በግልፅ የተረዳው ነገር ቢኖር የተሰጡትን ዓላማዎች በሚፈለገው መጠን ከዳር ለማድረስ በተናጠል የሚያደርገው ጥረት በቂ አለመሆኑን ነበር፡፡ በመሆኑም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተቀራርቦ መሥራቱ እጅግ አስፈላጊም ጠቃሚም መሆኑን አስቀድሞ በመገንዘብ ይህንኑ ለማከናወን የተቻለውን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን አቅጣጫ እንዲከተል ምክንያት የሆኑት በፀረ-ሙስና ትግል አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ አገሮች ተሞክሮና በዚህ ዙሪያ የተቀመሩት ንድፈ ሀሳቦች ናቸው፡፡

በመሆኑም በዚህ ረገድ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው እነዚህ ሁኔታዎች ማረጋገጫ ሆነዋል ማለት ይቻላል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ የተሰጡት ዓላማዎች የፀረ-ሙስናና የሥነምግባር ትምህርቶችን በህብረተሰቡ ውስጥ የማስፋፋት እና የማስረጽ፣ የሙስና ድርጊቶችን የመከላከል እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን የመመርመር እና አጥፊዎችን ለፍርድ ማቅረብ ናቸው፡፡

እነዚህን ዓላማዎች ከግቡ የማድረስ ሥራዎች ያልተቋረጠ እና ቁርጠኝነት የተመላበት እንቅስቃሴ ከመጠየቃቸውም በላይ እንደ ዓላማዎቹ ስፋት የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ ይፈልጋሉ፡፡

ኮሚሽኑ በዋናነት የተቋቋመው በአገሪቱ ውስጥ የሚኘውን የፀረ-ሙስና ትግል ለማስተባበር እና