| የኮሚሽኑ
የማቋቋሚያ
አዋጅ
እና
የፀረ-ሙስና
ልዩ
የሥነሥርዓት
እና
ማስረጃ
ህግ
እንዲሻሻሉ
ያስፈለገባቸው
ዋና
ዋና
ምክንያቶች
ኮሚሽኑ
አዋጆቹን
መሠረት
አድርጐ
ላለፉት
አራት
ዓመታት
ሲያከናውናቸው
ከቆያቸው
ተግባራት
በአገኘው
ተሞክሮ
በአዋጆቹ
ላይ
ማሻሻያዎች
መደረግ
እንዳለባቸው
የተረዳበት
ሁኔታ
ነበር፡፡
ይህም
በተቀረፀው
በመሆኑ
የሦስት
ዓመት
ስትራቴጂክ
እቅድ
ውስጥ
የአዋጆቹ
መሻሻል
እንደ
አንድ
ሥራ
በእቅዱ
ውስጥ
ተመልክቷል፡፡
እቅዱን
መሠረት
በማድረግም
አዋጆቹን
ለማሻሻል
በኮሚሽኑ
ደረጃ
ጥናት
የተካሄደበት
ሁኔታ
ነበር፡፡
እነኚህንም
ጥናቶች
መሠረት
በማድረግና
ሌሎች
ሁኔታዎችን
ግምት
ውስጥ
በማስገባት
አዋጆቹ
በሕግ
አውጭው
አካል
እንዲሻሻሉ
ሆነዋል፡፡

ለአዋጆቹ
መሻሻል
እንደ
አንድ
ምክንያት
የሚወሰደው
የአገሪቱ
የወንጀለኛ
መቅጫ
ሕግ
በመሻሻሉና
የኮሚሽኑንም
አዋጆች
ከዚህ
ከተሻሻለው
የወንጀል
ህግ
ጋር
ማጣጣም
በማስፈለጉ
ነው፡፡
ከዚህም
በላይ
የሙስና
ወንጀል
ትርጉምን፣
የክስ
ሂደቱንና
የማስረጃ
ጉዳይን
ከወንጀል
ሕጉ
ጋር
ማጣጣም
ተገቢ
ሆኖ
መገኘቱም
ለተደረገው
ማሻሻያ
ሌላው
ምክንያት
ነው፡፡
የዋስትና
ጉዳይን፣
ንብረት
የማገድና
ሌሎች
ግልፅ
ያልሆኑ
ድንጋጌዎችን
ለማስተካከል፣
ኮሚሽኑ
ከሌሎች
አካላት
ጋር
ያለውን
ግንኙነት
በግልፅ
ለማስቀመጥ
እንዲሁም
በሙስና
ወንጀል
የምርመራ
ሂደት
መረጃ
ለመግኘት
የሚያጋጥሙ
እንቅፋቶችን
ለማስወገድ
የአዋጆቹ
መሻሻል
አስፈላጊ
ሆኗል፡፡

የእነዚህ
አዋጆች
መሻሻል
የኮሚሽኑን
ሥራም
ሆነ
የፀረ-ሙስና
ትግሉን
በተሻለ
ሁኔታ
እንደሚያግዝ
ይታመናል፡፡
ከፖሊስ፣
ከፍ/ቤቶችና
ከሌሎች
መሰል
አካላት
ጋር
የሚኖረንን
የሥራ
ግንኙነት
ግልፅና
የተሳካ
እንደሚያደርጉት
ይታመናል፡፡
የተሻሻሉትን
አዋጆች
ይበልጥ
ውጤታማ
ለማድረግም
ኮሚሽኑ
ከአዋጆቹ
ጋር
የሚጣጣሙ
ደንቦችን
እና
መመሪያዎችን
ማውጣት
የአሠራር
አቅጣጫዎችን
መቀየስ
አስፈላጊ
በመሆናቸው
በዚህ
ረገድ
አንዳንድ
ሥራዎችን
እያከናወነ
ይገኛል፡፡
ከዚህ
አንፃር
የኮሚሽኑን
ሠራተኞች
የአስተዳደር
ደንብ
የማሻሻልና
ከሥነምግባር
መከታተያ
ክፍሎች
ጋር
የሚኖረውን
ግንኙነት
የሚወስነውን
ደንብ
የማዘጋጀት
እና
ሌሎች
ሥራዎች
ተጠቃሽ
ናቸው፡፡ |